Get Mystery Box with random crypto!

💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የሰርጥ አድራሻ: @join_maryam_amalajinet_telegram
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.51K
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ቻናል አላማ ስለ ድንግል ማርያም,ፃድቃን,መላእክት እና ሰማእይታት አማላጅነትና ገድል ተአምራታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን መመስከር ነው። ለህይወታችን ለሚገጥሙን ፈተናዎች አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ መልእክቶች ይገኙበታል።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-11-21 06:16:33 ሚካኤል ሆይ መብረቅን ለተጎናጸፈ መልአካዊ ረቂቅ ርእስህ ሰላም እላለሁ። ተፈጥሯቸው ከእሳት የሆነ የሰማያውያን የመላእክት ሠራዊት አለቃቸው የምትሆን ሚካኤል ሆይ በኃጢአት ተሰነካክዬ ወድቄ እንዳልፍገመገም አንተን ድጋፍ አድርጌአለሁና። ፍጹም የማዳንህን ትድግና በኔ ላይ ትገልጽ ዘንድ በስተቀኜ ቁመህ አለሁልህ በለኝ እንጂ በሩቅ ሆነህ አትመልከተኝ።
ሚካኤል ሆይ የችግረኛውን ሁሉ ጸሎት ፈጥነው ለሚሰሙ አዕዛኖችህ ሰላምታ ይገባል። የይቅርታ መልአክ ሆይ ችግሬን አቃልልኝ ጭንቀቴን አስወግድልኝ ምክርን ትለግሰኝ ጥበብንም ታስተምረኝ ዘንድ አባት እንዳደረኩህ አንተም ልጅ አድርገኝ።
መልክአ ቅዱስ ሚካኤል
እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ
998 views03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-19 06:46:26
፤ አቤቱ፥ አንተ ምሕረትህን ከእኔ አታርቅ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ።
፤ ቍጥር የሌላት ክፋት አግኝታኛለችና፤ ኃጢአቶቼ ያዙኝ፥ ማየትም ተስኖኛል ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።
፤ አቤቱ፥ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
፤ ነፍሴን ለማጥፋት የሚወድዱ ይፈሩ፥ በአንድነትም ይጐስቍሉ፤ በእኔ ላይ ክፋትን ሊያደርጉ የሚወድዱ ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይጐስቍሉም።
፤ እሰይ እሰይ የሚሉኝ እፍረታቸውን ወዲያው ይከፈሉ።
፤ አቤቱ፥ የሚፈልጉህ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፤ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ ዘወትር። እግዚአብሔር ታላቅ ይሁን ይበሉ።
፤ እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፥ ጌታ ግን ያስብልኛል፤ አንተ ረዳቴና መድኃኒቴ ነህ፤ አምላኬ ሆይ፥ አትዘግይ።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 40ቁ11.17)
1.9K views03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 12:45:42 + ለምን ትቀናለህ? +

በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር፡፡ የአጋንንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ፡፡ ተራ በተራ ወደ እርሱ እየሔዱ የፈተና ወጥመዳቸውን ዘረጉበት፡፡ በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ፡፡ አልተሳካም፡፡ በምግብም ሞከሩ ድል ነሣቸው፡፡ የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየ መንገድ እየተገለጹ አንዴ ሰው አንዴ መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም፡፡

አለቃቸው ይኼን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ፡፡ በጆሮው የሆነ ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ይህንን ጊዜ አጋንንቱ እያዩት መነኩሴው መንፈሳዊ ገጽታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት፡፡ በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት፡፡ እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ‘ከአንተ ጋር ያደገውና ከአንተ ጋር የተማረው ጓደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ’ ብዬ ነገርኩትና ወጣሁ፡፡ አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው አላቸው፡፡ አጋንንቱ በደስታ ጨፈሩ፡፡

ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ መጽሐፈ ቅዳሴ ሞትን ሲገልጸው ‘በሰይጣን ቅናት ወደ ዓለም የገባ’ ይለዋል፡፡ ሰይጣን በሰው ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን እንዲመኙ አድርጎ ዓለምን ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል ለሺህ ዓመታት ብዙዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት፡፡ መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው::

ቅናት እጅግ ክፉ ኃጢአት ነው፡፡ ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው:: ቅናት ግን በምታስተውል ነፍሱ ውስጥ የሚበቅል መርዝ ነው፡፡ ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር፡፡ የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ፡፡

ዮሴፍ የለበሳት ቀለምዋ ብዙ የሆነ ጌጠኛ ቀሚስ በወንድሞቹ ዘንድ የመረረ ጥላቻን አትርፋለት ነበር፡፡ አንዱ አጊጦ አምሮ ሲታይ ቢሞትና ቢገላገሉት ደስ የሚላቸው የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡

ዮሴፍም አርፎ አልተቀመጠም፡፡ እየሔደ ሕልሙን ይነግራቸው ነበር፡፡ ስለ ሕልሙም የበለጠ ጠሉት ይላል፡፡ ወዳጄ ሕልምህን ዝም ብለህ ለሰዎች አትዝራ፡፡ ሕልም ስልህ ተኝተህ የምታየውን ብቻ ማለቴ አይደለም፡፡ ራእይህን ፣ ተስፋህን ዕቅድህን ሲያውቁ የሚንገበገቡ የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡ ፍቺው ባይገባቸውም ባልተፈታ ሕልም ይጠሉሃል፡፡ ምንም ነገር ሳታደርግ እንኳን "ለምን አለምከው?" ብለው ጥርስ ይነክሱብሃል፡፡ ዮሴፍ ግን ይኼ ስላልገባው ነገራቸው፡፡ ወዳጄ አንተም ሕልምህን እንደ ዮሴፍ በየዋህነት የምትዘራ ከሆንህ እንግዲህ የዮሴፍ አምላክ ይጠብቅህ፡፡

ቅናት እጅግ ከባድ ነው፡፡ እረኛው ዳዊት ጎልያድን የገደለ ዕለት የተዘፈነለት መዘዘኛ ዘፈንም ነበረ፡፡ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ’ ብለው ዘፈኑለት፡፡ ይህች ዘፈን በሳኦል ጆሮ ስትደርስ ዳዊት ላይ ብዙ ጦር አስወረወረች፡፡ ሳኦሎች ሌላ ሰው ከእነርሱ በላይ ሲመሰገን የሰሙ ዕለት በቅናት ታውረው ገበታ ላይ ሳይቀር ሰይፍ ይመዛሉ፡፡

የጠፋው ልጅ ወንድምን አስበው፡፡ (ሉቃ 15:20) ወንድሙ ከጠፋበት ተመልሶ ደስታ ሲደረግ እርሱ ግን ከፍቶት ውጪ ቁጭ አለ፡፡ ወዳጄ ቅናት ከቤተ ክርስቲያንና ከእግዚአብሔር መንግሥት ያስወጣል፡፡ የሌላው ስኬት ካበሳጨህ እንደጠፋው ልጅ ወንድም ውጪ ቁጭ ብለህ አፈር እየጫርክ ‘እምቢየው አልገባም’ እያልክ እያልጎመጎምክ ትቀራለህ፡፡

ክርስቶስ ላይ አይሁድ ያቀረቡት ትችት ሁሉ ለሕግ ከመቆርቆር ሳይሆን ከቅናት ነበር፡፡ ጲላጦስ እንኳን ‘በቅናት አሳልፈው እንደሠጡት ያውቅ ነበር’ ይላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ቅናታቸውን በሌላ ነገር እንደ አይሁድ ሸፍነው ትችት ያቀርባሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ሕግ እንደተቆረቆሩ ፣ ለሥርዓቱ እንዳዘኑ መስለው ውስጣቸው ያለውን ቅናትና ጥላቻ ያንጸባርቃሉ፡፡

የሰንበት መሻር ፣ ለቄሣር ግብር መከፈል ፣ የመቅደሱ በሦስት ቀን ፈርሶ መሠራት እንዳንገበገባቸው እርር እያሉ ቢናገሩም እውነታው ግን ቅናት ነው፡፡ ‘የቤትህ ቅናት በላኝ’ እንዳለው ጌታ በየዘመኑ የሰዎች ቅናት ብዙ ንጹሐንን ትበላለች፡፡

ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆን አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን፡፡

ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለም፡፡ ካንተ ቀድሞም በትክክል አንተን የሆነ ሰው አልተፈጠረም ለወደፊትም አይፈጠርም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ያልሠራው ደግሞም የማይሠራው ምርጥ ዕቃው ነህና ራስህን ከሌላ ጋር አታወዳድር፡፡

ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ፡፡ ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተው ውስጥ ነው፡፡ ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ፡፡ መብለጥ ከፈለግህም አሁን ያለውን ራስህን ብለጠውና ሌላ ትልቅ አንተን ሁን፡፡

በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎችን ሰዎችንም ውደዳቸው፡፡ ከወደድሃቸው ‘ፍቅር አይቀናም’ና የእነርሱ ስኬት የደስታህ ምንጭ ይሆናል፡፡ የቅናት ስሜት ሲሰማህም ‘ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ’ ብለህ ለምነው፡፡

‘በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን’ ሮሜ 13፡13

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
5.6K views09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 12:41:34
ትህትና አንገትን ደፍቶ መሄድ አይደለም ከማንኛውም ነገር ሌላውን ማስቀደም ነው።
ትህትና ለታላላቆች መቀመጫ ወንበር መልቀቅ አይደለም፤ለታናናሾችም መቀመጫ ወንበር መልቀቅ ነው።
ትህትና አንገትን ማቅለስለስ አይደለም ልብን መስበር ነው።
ትህትና ለአምላክ ብቻ መገዛት አይደለም ለሰውም ራስን ማስገዛት ነው።
ትህትና ሰው ትሁት እንዲልህ ሰው ሰራሻዊ ራስን ዝቅ ማድረግ አይደለም፤ ተፈጥሮአዊ የሆነ ወዝ ሲኖርህ ነው።
ትህትና ፈጣሪ ሆኖ ሳለ ከሰው እንደተወለደው አምላክ ራስን ማውረድ ነው።
ትህትና ፈጣሪ ሆኖ ሳለ ከፍጡሩ ጋር ጓደኛ ሆኖ የተመላለሰውን አምላክ መምሰል ነው።
ትህትና ፈጣሪ ሆኖ ሳለ በጥፊ ሲመቱት የታገሰውን አምላክ መምሰል ነው።
ትህትና ፈጣሪ ሆኖ ሳለ ሊገድሉት በመስቀል ለሰቀሉት ጠላቶች ፍቅርን መስጠት ነው።
ትህትና ወልደ እግዚአብሔርን (ኢየሱስን) መምሰል ነው።
4.0K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-29 06:39:14
"ገብርኤል ሆይ! ከጭንቅና ከመከራ ለማውጣት የተላክህ መልአክ ነህና ሠለስቱ ደቂቅ በእሳት ጉድጓድ በተጣሉ ጊዜ ሁለቱ ክንፎችህን ጋርደህ ከመቃጠል እንዳዳንሃቸው እኔንም አገልጋይህን በረድኤትህ ኃይል አድነኝ።"
(መልክአ ገብርኤል)
5.6K views03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 07:16:15 16
#ድንግል_ሆይ የአንቺ ሥጋ ይገርመኛል ከሔዋን ተገኝቶ ከመላእክት ይልቅ ንፁህ ሆኗአልና፣ አፈር ነህ ከተባለው ከአዳም ተወልደሽ በሰማይ በአባቱ ቀኝ በተቀመጠው ንጉሥ በክርስቶስ ክቡር ሰውነት ላይ በተለየ ክብር ሆኖ በሰማያት ታይቷልና። ባለ ራዕይው ዮሐንስ ከአንቺ በነሳው ሥጋ ከተወጋው ቁስለቱ ጋር ወደ ሰማይ እንደወጣ ቢያየው እንዲሁ ይመጣል ብሎ በመፅሐፍ ነገረን። የወጉትም ሁሉ ያዩታል ተብሎ ተፃፈ። የታናሿ የአንቺ ገላ ሰማይ ለሚጠበው አምላክ ልብስ ሆነ። መሰወሪያው ከዚህ ነው የማይባለው ልዑል ሥጋሽን ለብሷልና ሥጋ ሆነ ተባለለት። ከባሕሪው እሳት የሆነውን እርሱን ሁሉ ዳሰሰው ሁሉ አቀፈው። መለኮታዊ ክብሩን በአንቺ ሥጋ ውስጥ ቢሰውረው የወደቀው ሰውም አምላክ ሆነ ተባለ። ይደንቃል።

#ደንግል_ሆይ መላእክት በቤተልሔም በአንቺ ላይ የሆነውን ቢመለከቱ ስብሐት ለእግዚአብሔር አሉ። ሌላ ምን ይባላል? የማይወርደው ከከፍታው ወርዶ ሲታይ በአድናቆት ስብሐት ነው እንጂ። ሰማይ ከክብሩ የተነሳ የምትጠበውን በአንቺ ክንድ ላይ ሲያዩት ምን ይበሉ? ኦ ማርያም በአንቺ የሆነውን ለመፃፍ የሚያስብ ቃለ ፀሐፊ ከፍቅሩ የተነሳ ብዕሩ በእንባ ስለሚርስ ስለ አንቺ እንዲህ ነው ለማለት ቃልና እቅም በማጣት ሠአሊ ለነ ብሎ ጽሑፉን ይዘጋዋል። አይችልምና።

#ልዑሉን_የወለድሽ_ልዕልት_ሆይ የአንቺ ሥጋ ከአቤል ይልቅ ተወደደ፤ ከደገኛው አብርሐም ይልቅ ከፍ አለ፤ ከንጉሱ ከዳዊት ይልቅ ሥጋሽ የተለየና የተመረጠ ሆነ ...ዳዊትም፦ ንጉስ ደም ግባትሽን ወደደ ብሎ ፃፈልሽ። ከእስራኤላውያን አባት ከያዕቆብ ድንኳን ይልቅ የአንቺ ሥጋ ተመረጠ። ሎጥ፦ መላእክትን ወደ ቤቴ ግቡ ቢላቸው በአደባባይህ እንሆናለን እንጂ አንገባም አሉት። ድንግል ሆይ የአንቺ ሥጋ ግን መላእክትን ለፈጠረ ጌታ ማደሪያ ሆነ። ለዚህ ቃል የለም ዝምታና አንክሮ እንጂ።

#ድንግል_ሆይ የአንቺን ሥጋ በመቃብር የለም በአብ ቀኝ እንጂ። አንዳንዶች ተነስታለች ለማለት ከበዳቸው። ለመሆኑ ልጅሽ አልዓዛርን ከመቃብር ያስነሳ መሆኑን አላነበቡ ይሆንን? የኢያዒሮስ ልጅን ታሪክ አልተመለከቱ ይሆን አንቺ ግን ወደ ሰማያት ከተነጠቁት ከሄኖክና ከኤልያስ ትበልጫለሽ።
ምልጃሽ ኢትዮጵያን ይታደግ
ለአለም ምህረት ይሁን
Memhr Abunu Mamo
የኪዳነምህረት ምልጃ አይለየን
10.0K views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 10:11:01 ሰው ከእግዚአብሔር ሲለይ ፦
ዓይኑ ያልተፈቀደውን ሁሉ ያያል።
ምላሱ ሰውን አራጅና አዋራጅ ትሆናለች።
ጀሮው የሰውን ኃጢአትና ገመና ሰሚ ይሆናል።
እጆቹ የሰውን ንብረትና አካል ዘራፊ ይሆናሉ።
እግሮቹ ነፍስንና ስጋን ወደሚያበላሹ ቦታዎች ይሮጣሉ።
ስጋው የዝሙት ፈረስ ይሆናል።
ልቡ የፍርሀትና የጭንከት ከበሮ ይመታል።
አእምሮው የአጋንንትና የሰይጣናት መስሪያ ቤት ይሆናሉ።
12.3K views07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 18:59:29
“ተወዳጆች ሆይ! ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ብቻ የምትሰሙ አትሁኑ፡፡ እነርሱን ለመምሰልም ተጣጣሩ እንጂ፡፡ ለጊዜው ብቻ የምታደንቋቸው አትሁኑ፡፡ ወደ ቤታችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቡናችሁ ውስጥም ዘልቀው እንዲገቡ አድርጉ፡፡ ዘወትር አስቧቸው፡፡ በልቡናችሁ ጓዳ እንዲገቡ አድርጓቸው፡፡
እናንተን ትተው ይሔዱ ዘንድ አትፍቀዱላቸው፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ዘወትር እያያችኋቸው ትበረታላችሁ፡፡
በእምነት ትጸናላችሁ፡፡ የለበሱትን የጽድቅ ጥሩር፣ የያዙትን ምግባረ ወንጌል፣ የእምነት ጋሻ፣ የመዳን ራስ ቁር፣ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ እየተመለከታችሁ ትበረታላችሁ፡፡”
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ )
15.8K viewsedited  15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 06:57:14 መለኩሴው ሴራጲዮን ከወገቡ ላይ ሀፍረት ለመክላት ያክል ልብስ ይለብሳል ፤ ሌላውን ርቃኑን ነው።
የተማረና አዋቂ ፤ ምሁር መለኩሴ ነው። የዚህን ዓለም ቅንጣት ጥሪት አይፈልግም። ራሱን ባሪያ አድርጎ ለሰዎች ይሸጣል። የገዙትን ሰዎች ቀስበቀስ አስተምሮ ያጠምቃቸዋል፡፡ ወደ ማያውቁት ወደ ሌላ ቦታ ይሄድና ሌላ ገድል ይሰራል።
ሰው ለማዳን ወደ ግሪክ ተጉዞ በአቴንስ ከተማ ሦስት ቀን ሙሉ ቁራሽ የሚሰጠው ሰው አጣ። ስንቅም ውሀም አይዝም።
በአራተኛው ቀን በጣም ስለ ተራበ ሕዝብ በበዛበት ቦታ ቆሞ "የአቴንስ ሰዎች ሆይ ፣ እርዱኝ" እያለ ጮኸ፡፡

ይህን ሲሰሙ ሕዝቡም ፈላስፋውም ወደ እርሱ ሄደው ፦
"ምን እንርዳህ ?" አሉት።
እርሱም ፦ "በትውልዴ ግብጻዊ ነኝ ። ሦስት ጨካኝ ባለ አራጣዎች እጅ ወደቅሁ ፣ ሁለቱ ብድራቸውን በሙሉ ስለ ተከፈሉ አሁን ትተውኛል ፤አንዱ ግን እስካሁን አንዱ አበዳሪ አልተወኝም፡፡" አለ፡፡

እርሱም ፦" ከወጣትነቴ ጀምሮ #ስስት ፣ #ሆድና #ዝሙት አስቸግረውኛል፡፡ ከሁለቱ አሁን ነጻ ሆኜአለሁ ፣ ።ስስት እና ዝሙትን አሸንፌያለሁ ፡፡ #ከሆድ ግን እስካሁን ነጻ መሆን አልቻልሁም፡፡
ከበላሁ አራተኛ ቀኔ ነው ፣ ሆዴም እያስጨነቀኝ ነው፡፡" አላቸው፡፡
ቀልድና ፌዝ መሰላቸውና ገንዘብ ሰጡት፡፡ የሰጡትን ገንዘብ ተቀብሎ ዳቦ ለሚሸጥ ሰው ሁሉንም ገንዘብ ጠቅሎ ሳይቆጥር ሰጠውና አንዲት ቁራሽ ዳቦ ብቻ ተቀብሎ መንገዱን ቀጠለ ፤ ወደዚያች ከተማም ዳግመኛ አልተመለሰም፡፡
ሴትንም ቢመለከት እንደ እናቱ ወይም እንደ እህቱ ይመለከታል። በህሊናው የዝሙትን ስሜት አጥፍቶታል። ስስትም ድል ስላደረገ የተሰጠውን ገንዘብ ሳያስቀር ሰጥቶ መንገዱን ቀጥሏል። ሌላ አዲስ የማዳንና የማስተማር ስራ ይሰራል።
2.1K views03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 10:55:25
‹‹በአንቺም ምሰሶዎች ቆሙ ሕንፃዋም ባንቺ ጸና ግድግዳዋም ባንቺ ተሠራ፡፡ ጠፈርዋም ባንቺ ተፈጠረ ፣ ዋልታዋም ባንቺ ተዋቀረ ጭምጭምታዋም ባንቺ ተጨመጨመ፡፡ ደጆቿም ባንቺ ተከፈቱ ፣ መቃን መድረኳም በልጅሽ ደም ተረጨ ፡፡ በአንድ ልጅሽ መስቀል ፍሬ ያፈራችው ቅድትስ ቤ/ክ ታመሰግንሻለች ፤ ከርኩሰቷም በሆድሽ ፍሬ ደም የነጻችው ፣ ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሣኤ የተጽናናችው ፣ የተዋረደች ስትሆን በድንግልናሽ ቡቃያ ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤ/ክ ታመሰግንሻለች፡፡ ቅድስት ድንግል ሆይ ምስጋናሽ በሁሉ መላ ውዳሴሽም በዓለም ዳርቻ ሁሉ ሰፈፈ የውቅያኖስ ባሕር በመደቡ የተወሰነ ነው ፣ የሐኖስም ባሕር እንደ መጠኑ ልክ አለው ያንቺ ምሥጋና ግን ልክ፣ወሰን፣ሥፍር፣ቁጥር፣ማለቂያ የለውም ፤ አዕምሮ ሊወስነው፣አንደበት ተናግሮ ሊፈጽመው አይችልም፡፡ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ ሁሉ ላንቺ ሆነ ፣ ሁሉ ስላንቺ ተፈጠረ፡፡ አዳም ከኅቱም ምድር የተፈጠረ አንቺን ያፈራ ዘንድ ነው፡፡ ሔዋንም ከአዳም ጎን የተፈጠረች አንቺን ትወልድ ዘንድ ነውና›› ፡፡ (አርጋኖን ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)
4.9K views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ