Get Mystery Box with random crypto!

💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የቴሌግራም ቻናል አርማ join_maryam_amalajinet_telegram — 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍
የሰርጥ አድራሻ: @join_maryam_amalajinet_telegram
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.51K
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ቻናል አላማ ስለ ድንግል ማርያም,ፃድቃን,መላእክት እና ሰማእይታት አማላጅነትና ገድል ተአምራታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን መመስከር ነው። ለህይወታችን ለሚገጥሙን ፈተናዎች አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ መልእክቶች ይገኙበታል።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-07-14 09:00:23
አቤቱ ፈጣሪያችን ቅድስት ስላሴ ሆይ ዘረኝነትን እየዘራ ክፋት ምቀኝነትን እየነዛ ወንድም ከወንድሙ ወገን ከወገኑ እንዳይስማማ የሚያደርገውን የአጋንት መንፈስ ፈጥነህ ከአገራችን ኢትዮጲያና ከአለም ሁሉ ላይ ነቅለህ አውጣ። አቤቱ አግኝቶ ከማጣት ወቶ ከመቅረት ሰውረን በጠላት መንጋጋ ከመውደቅም አድነን። አቤቱ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ላክ ዘመናችንን እንደቀድሞ አድስ።
አምላካችን ሆይ ሀገርን ከጥፋት ህዝብህን ከስደት አድን። የደነደነው ልባችንን ስበረህ በሰላም በፍቅር በአንድነት የምንኖርበት ምድር አድርግልን። በበረከትና በምህረትህ ዘውትር ጎብኘን። በእያንዳንዳችን ህይወት ውስጥ ገብተህ ኑሮአችንን ቀና ዘመናችንን ምቹ አድርግ።
ቅድስት ስላሴ ከክፉ ሁሉ ይሰውረን
4.6K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:55:53
ከዛፎች ሁሉ ጠማማው ዛፍ ተመርጦ የመጥረቢያ እጀታ ይሆናል። ስለት ተገጥሞለት ጓደኞቹን ዛፎች እየቆረጠ ይኖራል። እጀታው ሲያረጅ ስለቱ ወጥቶ እጀታው ወደ ምድጃ ይወረወራል። ይከስላል። አመድ ይሆናል።
ሰውም ልክ እንደ እጀታው መጨረሻ ላይ የእጁን ያገኛል።
....
ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤"
(ወደ ገላትያ ሰዎች 6:7)
13.5K viewsedited  16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:28:35
እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አመታዊ ክብረ በአል አደረሳችሁ
ሰኔ 30 መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የተወለደበት እለት ነው
...
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ጌታን ባጠመቅክበት ክቡራን እጆችህ ነብስና ስጋችንን እንዲሁም የወጣትነት ዘመናችንን በእጥፍ ባርክልን፤ ለሀገራችን ፍፁም ሠላምን ስጥልን አሜን
13.1K viewsedited  06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 19:12:03 አስር ጊዜ ከመጮኽ ይልቅ አንድ ጊዜ መጸለይ ዋጋ አለው።
ፈርኦንን ከነወታደሩ በቀይባህር ያሰጠመው የራሄል እንባ ነው። ቀይባህርን የከፈለው የሙሴ ጸሎት ነው።
ዳዊት ጎልያድን የገደለው አምላኩን ስለተማመነ ነው። ፍየል ነብር ሲያንቃት ትጮኻለች ። ጓደኞቿም ይጮኻሉ።
ስለጮኹ ነብሩ አይተዋቸውም። በገደላቸው ቁጥር ወኔ ይሰማዋል። ሌላ ይገድላል። ይጮኻሉ፤ ይሞታሉ ። አሁንም ይጮኻሉ ፤ይሞታሉ።
ከዚህ ለመዳን እንደ ራሄል ማንባት፣ እንደ ሙሴ መጸለይ፣ እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ማመን ይጠይቃል።
እግዚአብሔር እንባችንን ያብስልን
ከሱ ውጪ መፍትሄ የለንም
20.6K viewsedited  16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 07:34:03 አምላኬ፥ በቀን ወደ አንተ እጣራለሁ፥ አልመለስህልኝም፤ በሌሊትም እንኳ ዕረፍት የለኝም።
፤ በእስራኤል የተመሰገንህ አንተ ግን በቅድስና ትኖራለህ።
፤ አባቶቻችን አንተን ተማመኑ፥ ተማመኑ አንተም አዳንሃቸው።
፤ ወደ አንተ ጮኹ አመለጡም፥ አንተንም ተማመኑ አላፈሩም።
፤ እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም፤ የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ።
፤ የሚያዩኝ ሁሉ ይላግጡብኛል፤ ራሳቸውን እየነቀነቁ በከንፈሮቻቸው እንዲህ ይላሉ።
፤ በእግዚአብሔር ተማመነ፥ እርሱንም ያድነው፤ ቢወድደውስ ያድነው።
፤ አንተ ግን ከሆድ አውጥተኸኛልና፥ በእናቴ ጡት ሳለሁም በአንተ ታመንሁ።
፤ ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ላይ ተጣልሁ፤ ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ።
፤ ጭንቀት ቀርባለችና የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ።
መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 22ቁ 2-11
መልካም እለተ ሰንበት
15.2K viewsedited  04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 08:58:11 ꔰ ሰኔ ፳፩ = ሰኔ ጎለጎታ ወሕንፀተ ቤተክርስቲያን
እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ሰኔ ጎለጎታና ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን (ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ለታነጸበት) ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
‹‹ሰኔ ጐልጐታ፤ ችግር የምትፈታ፤
ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በዚህ ቀን ሰኔ ፳፩ ልጇን ወዳጇን ጎለጎታ በሚባል ቦታ ላይ እንበዋ እንደ ጅረት እስኪፈስ ድረስ ለኃጥአን ምሕረትን ለምናዋለች:: ጌታችንም ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል፡፡
ህንጸተ ቤተክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መታነጽ)
ታላቅ በዓል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሻሽ የመጣችና ሩቅ ብእሲ የመሠረታት ሳትሆን እራሱ ጌታችን አምላካችን በገዛ ደሙ የመሠረታት ናት፡፡ ሐዋ 20፡28፡፡ በዕለተ ዐርብ በዕፀ መስቀል ላይ ከጌታችን የፈሰሰውን ቅዱስ ደም ቅዱሳን መላእክት በብርሃን ፅዋ ቀድተው በዓለም ሁሉ
ረጭተውታል፡፡ ስለሆነም የጌታችን ወርቀ ደም በነጠበባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ይሠራባቸዋል፡፡
የብርሃን እናቱ ንግሥተ ሰማይ ወምድር
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ: በምልጃዋ: ከኃጥያትና ከበደል : ከመከራ ሥጋና ከመከራ ነፍስ ትጠብቀን: አሜን።
21.5K views05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 07:41:13 ፤ አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘላለም አልፈር።
፤ በጽድቅህ አስጥለኝ ታደገኝም፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድነኝም።
፤ በጠንካራ ቦታ ታድነኝ ዘንድ አምላክና መሸሸጊያ ሁነኝ፤ ኃይሌ መጠጊያዬ አንተ ነህና።
፤ አምላኬ፥ ከኃጢአተኛ እጅ፥ ከዓመፀኛና ከግፈኛም እጅ አድነኝ።
፤ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና።
፤ ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው።
፤ ለብዙዎች መደነቂያ ሆንሁ፤ አንተ ግን ብርቱ መጠጊያዬ ነህ።
፤ አፌን ምስጋና ምላ ሁልጊዜ ክብርህንና ግርማህን እዘምር ዘንድ።
፤ በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፥ ጕልበቴም ባለቀ ጊዜ አትተወኝ።
፤ ጠላቶቹ በላዬ ተናግረዋልና፤ ነፍሴንም የሚሹአት በአንድነት ተማክረዋልና፥ እንዲህም አሉ።
፤ እግዚአብሔር ትቶታል፤ የሚያድነው የለምና ተከትላችሁ ያዙት።
፤ አምላክ ሆይ፥ ከእኔ አትራቅ፤ አምላኬ ሆይ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 71 ቁ1-12
20.6K views04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 12:40:58
በሀገረ እግዚአብሔር / በቅድስት ምድር /
በእመቤታችን ርስተ ምድር በሆነችው በኢትዮጵያ የሰው ልጅ ደም እየፈሰሰ ነው ፡፡
ኢትዮጵያ ሹሙ እንደ ጠፋበት ንብ ህዝቡ ከተበታተነ ሰነበተ። የሰው ሕይወት የውሻ ሕይወት ያክል ተቆጥሮባታል ፡፡
አምላክ ከ 22ቱ ፍጥረታት ለይቶ አምላካዊ ክብሩን
የሰጠው የሰው ፍጡር እየሞተም እየገደለም ነው ፡፡ ሰው ሠውን እያደነ ነው ፡፡
ከሰው ሕይወት ይልቅ ስንዝር መሬት ትልቅ ከበሬታ አግንታለች። ሁሉም ነገ ጥሎት ለሚሄድ መሬት እየተስገበገበ ነው። በዚች ሀገር የጥይት
ባሩድ እየሸተተ ነው ፡፡ ህዝቡ ደስታውን ሳያጣጥም ጥቁር ደመና እየመጣበት ነው ፡፡ በዚች ሀገር ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለው አስታራቂ ሽማግሌ ይፈለጋል፡፡
ቅዱሳን የመነኑበት ምድር በእግዚአብሔር ቁጣ እንደ እስራኤላውያን ቤተ መቅደስ እንዳትሆን እንፈራለን፣የሙሴ ጽላት ያለባት ምድር የሶረያን እጣ እንዳታገኝ እንፈራለን። ምንግዜም ሰው ሲያጠፋ ሀገር ባድማ ትሆናለች፡፡
በፈረሱ የተማመነ ይጠፋል ይላል ነብዩ ዳዊት።
የፈርዖን ታሪክ እንዳይደገም እንፈራለን ፡፡ የሰው ደም ከባድ ነው። ትልቅ መከራ ያስከፍላል ፡፡ ሳጥናኤል ክፉ
ነው። ከላይ ከትዕቢት ተራራ ላይ ሰቅሎ ወደ ውርደት ሸለቆ ይፈጠፍጣል፡፡
ምን ይሁን ኢትዮጲያውያን እርስ
በርስ አዳኝና ታዳኝ ሆነው በደማቸው ይራጫሉ ፡፡
አንደበቱ ቅባ ቅዱስ የተቀባ መሪ እቺ ሃገር ትፈልጋለች።
16.4K views09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 07:21:38
አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህ ። የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ ። ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ።"
(መልክአ ሚካኤል)
18.6K views04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 07:18:05
አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።
፤ አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማፅኛለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ።
፤ አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።
፤ አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት።
፤ በምሕረትህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥ እኔ ባሪያህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው።
መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 143 ቁ 8-12
17.4K views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ