Get Mystery Box with random crypto!

ድንግል ሆይ ምስጋናሽ በሁሉ መላ ውዳሴሽም በዓለም ዳርቻ ሁሉ ሰፈፈ የውቅያኖስ ባሕር በመደቡ የተወ | 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

ድንግል ሆይ ምስጋናሽ በሁሉ መላ ውዳሴሽም በዓለም ዳርቻ ሁሉ ሰፈፈ የውቅያኖስ ባሕር በመደቡ የተወሰነ ነው ፣ የሐኖስም ባሕር እንደ መጠኑ ልክ አለው ያንቺ ምሥጋና ግን ልክ፣ወሰን፣ሥፍር፣ቁጥር፣ማለቂያ የለውም ፤ አዕምሮ ሊወስነው፣አንደበት ተናግሮ ሊፈጽመው አይችልም፡፡ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ ሁሉ ላንቺ ሆነ ፣ ሁሉ ስላንቺ ተፈጠረ፡፡ አዳም ከኅቱም ምድር የተፈጠረ አንቺን ያፈራ ዘንድ ነው፡፡ ሔዋንም ከአዳም ጎን የተፈጠረች አንቺን ትወልድ ዘንድ ነውና›› ፡፡
(አርጋኖን ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)