Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን ለባእታ ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ 3 የብርኅን እናት የከበበሽ ዕንቁ ብርሃ | 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

እንኳን ለባእታ ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ
3
የብርኅን እናት
የከበበሽ ዕንቁ ብርሃን ከጨረቃ በላይ ይደምቃል ፣
የደምግባትሽ ጸዳል ከፀሐይ ያንፀባርቃል ።
ድንግል ሆይ ባህታውያን አለምን ጥለው መነኑ ፣
ከመቅደሱ ውስጥ ቢያገኙሽ በሀዘን ያሉት ተፅናኑ ።
መዓዛሽ የሚያረሰርስ የናርዶስ ሽቶ መጥመቂያ ፣
ለዘላለም የምትፈሺ የማየ ህይወት መፍለቂያ ፣
የድህነት መዝገብ ዶሴ የይቅርታ መጠየቂያ ፤
የአዲሲቷ ሠማይ ሚስጥር ያልተፈታሽ ድብቅ ቅኔ ፣
የአዳም ተስፋው ምልክት ነሽ ያወጣሽን ከኩነኔ ።
የመጎብኘት ምክንያት የሆንሽ የፍጥረት ሁሉ መዳኛ
የኖህ ቀስተ ዳመና የአርማው ቃል ኪዳን መገኛ ፣
የአልፋ ኦሜጋ ማደሪያ የሥላሴ መመስገኛ ፣
ማርያም ማርያም የምንልሽ እናታችን ነይ ወደ እኛ ።

ባዕታ ማርያም ሆይ ግና በልጅነትሽ አለምን ንቀሽ የአምላክ ማደሪያ ልትሆኚ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ
በንፅህናሽም መዓዛሽን የወደደ ወልድን ከመንበሩ
የሳብሽ በቅድስናሽም ለአዳም ተስፋ የሆንሽው
ትውልድ ሁሉ ብፅይት የሚልሽ እናቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ርስትሽ የምትሆን
የቃል ኪዳን ምድርሽን አስቢያት ። እኛ የአስራት ልጆቿንም ከጥፋት ሰውረሽ ከዚህ ዘመን ሞትና ፍጅት ለይተሽ በሠላምና በፀጥታ እናርፍ ዘንድ ከልጅሽ ከወዳጅሽ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኚልን ። አሜን አሜን አሜን ።
@ፍሠሐ ጽዮን
ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያግዝፉ
እንደ ዕብራዊያን ሴቶች በዋዛ በፈዛዛ
ያደግሽ አይደለሽም በንጽሕና
በቅድስና በቤተመቅደስ
ኖርሽ እንጅ
ባእታ ማርያም ምልጃዋ አይለየን አሜን