Get Mystery Box with random crypto!

ጥር 21 ድንግል ማርያም በ 64 አመቷ ያረፈችበት እለት የጥንት ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ እመቤታችን | 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

ጥር 21 ድንግል ማርያም በ 64 አመቷ ያረፈችበት እለት
የጥንት ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ እመቤታችን ዕረፍትና ትንሳኤ በዓይናቸው ያዩትንና የተማሩትን እንዲህ ይመሰክራሉ!
....................
1. # ኢቮድየስ_ዘአንጾኪያ (የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀመዝሙር) :- ይህ ታላቅ አባት ከጴጥሮስ ጋር አብሮ የነበረ፣ የድንግል ዕረፍትዋ በዓይኑ የተመለከተ፣ የትንሳኤዋም ሕያው ምስክር የሆነ ነው! ያየውምን ነገር በሙሉ "Homily on the Dormition of the falling asleep of Mary" በተባለው ክታቡ እንዲህ ይተርካናል!
...........
(ነሐሴ) ወር በአስራ ስድስተኛው ቀን ጠዋት በተመሳሳይ ምሽት በብርሃን ሰዓት፣ ጌታችን በታላቅ ክብር ወደኛ መጣ! ሰግደንም አመለክነው! ጌታም "ለምን ታዝናላችሁ?" ሲለን፣ አባቴ ጴጥሮስም "በእናትህና በሁላችን እመቤት ሞት፣ ከሞተችም ብኋላ ስጋዋን ስላላሳየሀን ነው" አለው! ጌታም ወደ መቃብሩ በመጣራት የድንግል እናቱን ስጋ በማስነሳት፣ ነፍስዋንም እንደገና ወደ ስጋዋ በማስገባት ልክ ቀድሞ በስጋ እንደምናውቃት በስጋ አየናት። መድኃኒታችንም ለስለስ ባለ ድምፅ "እነኋት ውድ እናቴን" አለን። ይህ የሁላችን እመቤት እና የወላዲተ አምላክ የሕይወትዋ መጨረሻው ይህ ነው በጦቢ(ጥር) ወር 21ኛ ቀን። ትንሳኤዋ ደግሞ በሜሶሪ (ነሐሴ) ወር በ16ኛው ቀን ነው> በማለት ከቀብሯ ተገኝቶ ትንሳኤዋን አይቶ ይመክረናል።
.............
2.ቅዱስ # ቴዎዶስዮስ_ዘእስክንድርያ (535 ዓ.ም)
አባታችን ቴዎዶስዮስ ስለ ትንሳኤዋ ሲንፕግረን <የነበሩበት ቦታ በእሳት ተሞላ። ጌታም በኪሩቤል ላይ ሆኖ የድንግልንም ነፍስ በእቅፉ በሰማያዊ ልብስ አጊጣ ይዟት ተገለጠ። ሐዋርያትም በፍርሐት ተሞልተው መሬት ላይ እንደ ሞቱ ሆኑ። እርሱ ፍርሐታቸውን አጥፍቶ እንዲህ አላቸው "እናንተ ደቀመዛሙርቴና ደናግል ሆይ፥ የእናቴን ክብር ታዩ ዘንድ ተነሱ።" እንዲህ ብሎም ወደመቃብሩ ጮሀ "ለእኔ መቅደስ የሆነሽኝ አንቺ ቅድስት ስጋ ሆይ፣ የእኔ የዘላለም ድንኳን የሆነችኝን ይህቺን ነፍስ ውሰጂ" ... ጌታ እነዚህን ቃላት ሲናገር መቃብሩ በዚያ ቅፅበት ተከፈተ... ከዚያም ብኋላ የከበረው የድንግል ስጋ ተነሳ፤ ነፍስዋንም አከበረቻት። ሁለት ወንድማማች ከተለያየ ሀገር እንድሚመጡ እንዲሁ ተባበሩ አንድም ሆኑ> ብሎ ወደ ትንሳኤዋ ይወስደናል።
.............
3.ቅዱስ # ዮሐንስ_ዘደማስቆ (675-749)
ይህ ቅዱስ አባትም <እርስዋ ልጅን ስትወልድ ድንግልናዋ እንደተጠበቀ እንዲሁ ስጋዋ ከሞትም ብኋላ ከመበስበስ የተጠበቀ ይሆን ዘንድ የተገባ ሆነ። ፈጣሪን በሕፃንነቱ በደረቷ እንዳቀፈችው እንዲሁ በመለኮታዊው ድንኳን (ሰማያዊ መቅደስ) ትኖር ዘንድ ተገባት! የእግዚአብሔር እናት የልጇ የሆነውን ነገር (ትንሳኤ) ታገኝ ዘንድ በፍጥረት ሁሉም የእግዚአብሔር እናትና አገልጋይ ተብላ ትመሰገን ዘንድ ሆነች> ይለናል።
.............
4.ቅዱስ # ጌርማነስ_ዘቁስጥንጥንያ (8ኛ ክ.ዘ)
ይህ አባት ደግሞ <አንቺኮ እንደ ተፃፈው በውበት የተገለጥሽ፣ ድንግል የሆነ ስጋሽም ቅዱስና ንጹሕ፣ መላውም የእግዚአብሔር ማደርያ ነው። ስለዚህም ጠቅልሎ አፈር ሆኖ ከመቅረት ነጻ ሆነ (ቀረ) ምንም እንኳን አሁንም ሰው ብትሆኚ ሥጋሽ ወደ ማይበሰብስ ሰማያዊ ሕይወት (አካል) ተቀየረ! አሁንም ስጋሽ በሕይወትና በክብር፣ ሳይጎድፍና ሳይጎድል በፍፁም ኑባሬ አለ!> እያለ ከእናቱ ከእናታችን ጋር ያወጋል። በአባቶቻችን እምነት ያፅናን!
.... የትንሳኤዋ በረከት ከወደቅንበት ኃጢኣት ያንሳን!