Get Mystery Box with random crypto!

'እግዚአብሔር ጠላቶችህን ከእግርህ በታች ያስገዛልህ!' አቡነ አረጋዊ። የናግራን ሰማዕታትን በግ | 💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

"እግዚአብሔር ጠላቶችህን ከእግርህ በታች ያስገዛልህ!" አቡነ አረጋዊ።

የናግራን ሰማዕታትን በግፍ መገደል የመገልጽ ደብዳቤ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ኢትዮጵያው ንጉሥ ወደ ዐፄ ካሌብ ላኩለት፡፡ ዐፄ ካሌብም መልእክቱን ከተረዳ በኋላ ወደ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፣ ‹ፊንሐስ የተባለ አረማዊ የናግራን ክርስቲያኖችን ደም በከንቱ ያፈሰሰ፣ ቤተክርስቲያንን የመዘበረና ያጠፋ ፍጹም የእግዚአብሔር ጠላት ወደሚሆን ሄጄ እዋጋው ዘንድ ተዘጋጅቻለሁ፡፡ ስለዚህ አባቴ ሆይ! አንተም በበኩልህ ጸሎት አድርግልኝ፣ የጻዲቅ ጸሎት ትራዳለች፣ ኃይልንም ታሰጣለች፣ በጠላት ላይ ድልንም ታቀዳጃለችና› ሲል ላከበት፡፡

አባታችን አቡነ አረጋዊም ለንጉሡ ጭፍሮች ‹ወደ ጦሩ ግንባር ሂድ፣ እግዚአብሔር ጠላቶችህን ከእግርህ በታች ያስገዛልህ፣ ለአንተም ግርማ ሞገስ ይስጥህ፣ በሰላም ይመልስህ› ብለው መርቀው ሸኝተውታል፡፡ ዐፄ ካሌብም ወደ ናግራን ዘምቶ ከሓ'*ዲ*'ውን የአይሁድ ንጉሥ ፊንሐስን ከገደለውና ጦሩን ሁሉ ደምስሶ በማጥፋት የክርስቲያኖቹን ደም በሚገባ ተበቀለ፡፡ በአንጾኪያ፣ በእስክንድሪያ፣ በሮም፣ በቊስጥንጥንያና በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ ይህን ሲሰሙ በእጅጉ ተደሰቱ፡፡ ይህም የሆነው በ525 ዓ.ም ነው፡፡

ዐፄ ካሌብ ወደ አቡነ አረጋዊ "የእግዚአብሔርን ጠላት ሔጄ እዋጋው ዘንድ ተዘጋጅቻለሁና አባቴ በጸሎት አስቡኝ" በማለት መልእከት ሲልክባቸው እርሳቸውም የሰጡት መልስ "እግዚአብሔር ጠላቶችህን ከእግርህ በታች ያስገዛልህ!" የሚል ነበር። የእነ ዐፄ ካሌብ የእነ አቡነ አረጋዊ አምላክ የቅድስት ኢትዮጵያን ጠላቶች አጥፍቶ ትንሣኤዋን ያሳየን።

"እግዚአብሔር ደብረ ሃሌሉያ የተባለች ደብረ ዳሞን መርጧታልና ለአቡነ አረጋዊ ማደሪያው ትሆን ዘንድ ወዷታልና እርሷ ለዘለዓለሙ ማደሪያውና መሠወሪያው ናት" ቅዱስ ያሬድ ለደብረ ዳሞ የዘመረላት ዝማሬ ነው።

አቡነ አረጋዊ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብርሃኗ የሆነ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ እና ንጉሥ በዐፄ ገብረ መስቀል ሦስቱ ቅዱሳን አብረው ብዙ ታሪኮችን ፈጽመዋል፡፡ ገዳማትን ላይ በመዟዟር ቅዱስ ያሬድ ዜማን ሲያስተምር ንጉሡ ደግሞ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ ያስፋፉና ቋሚ መተዳደሪያ ይሰጡ ገዳማቱን ያጠናክሩ ነበር፡፡ አቡነ አረጋዊ ደግሞ አብረው ምኩስናን ያስፋፉ ነበር፡፡ ሦስቱም ይህን ተግባራዊ እንዳደረጉ ለማሳያ ይሆን ይሆን ዘንድ ቅዱስ ያሬድ 3 ዓመት ዝማሬ መዋሥዕት ያስተማረባትንና ዛሬም ድረስ ማስመስከሪያ የሆነችውን እጅግ ጥንታዊቷን ዙር አባ ጽርዓ አርያም አቡነ አረጋዊ ገዳም አንዷ ናት።

@ ከገድላት አንደበት