Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ezmerejaet
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4
የሰርጥ መግለጫ

እንዴት አደርሽ ኢትዮጵያዬ ! 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-11-08 21:05:57 መቀሌ

ከስምምነቱ በኋላ የገበያው ሁኔታ!!

ጤፍ ከ16,000 ብር ወደ 7,000 ብር ወርዷል፣
መኮረኒ 25ኪሎ ከ4,500 ብር ወደ 2000 ቀንሷል፣
የመንግስት ስንዴ በኩልንታል ከ9,000 ወደ 3,500 ወርዷል።

ይህም ነጋዴው ከየመጋዘኖቹ በስጋት የተከዘኑ ሸቀጦችን ወደ ከተማ ገበያዎች በማውጣቱና የተወሰኑ ሸቀጦች መግባት መጀመራቸውን ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
2.9K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 18:26:31
የአርቲስት ዓሊ ቢራ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የአንጋፋው ከያኒ አሊ ቢራ ሥርዓተ ቀብር በትውልድ ቦታው ድሬዳዋ ከተማ ተፈፅሟል፡፡

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በለገሃሬ መስጊድ ጣሊያን ተፈፅሟል፡፡

በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ፣ አንጋፋና ወጣት አርቲስቶች እንዲሁም በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

   
@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.1K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 13:12:51 አማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የተሟላ ድጋፍ ለማቅረብ መቸገሩ ተገለጸ!

በአማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች፣ የተሟላ ድጋፍ ለማቅረብ መቸገሩን የክልሉ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።ኮሚሽኑ በአሁኑ ጊዜ በአማራ ክልል ከ850 ሺሕ በላይ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች መኖራቸውን ጠቅሶ፣ በተለይም ሕወሓት በፈጠረው ቀውስ የተነሳ ምግብ ነክ የሆኑና ምግብ ነክ ያልሆኑ ሰብዓዊ ድጋፎችን የሚሹ ከ8 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች እንዳሉ አስታውቋል።

ይህን ተከትሎም፣ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ የተሟላ ድጋፍ ማቅረብ እንዳልተቻለ ያነሳው ኮሚሽኑ፣ የትራንስፖርት ችግር፣ የጸጥታ ሁኔታ እንዲሁም የሩስያና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ የተፈጠረው የምግብ እጥረትና የዋጋ ቀውስ ዋነኛ እንቅፋቶች መሆናቸውን አስገንዝቧል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.0K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 11:54:18
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 9 አባላት ያሉት አዲስ የስራ አመራር ቦርድ አባላት ሹመት በዛሬው ዕለት አፅድቋል፡፡

በዚሁ መሰረት ምክር ቤቱ ብዝሃነትን እና የትምህርት ዝግጅትን መሰረት ያደረጉ ዕጩዎች ከቀረቡ በኋላ የስራ አመራር ቦርዱን ሹመት አፅደቋል፡፡

በዚሁ መሰረት
1. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የቦርድ ሰብሳቢ
2. አቶ መሳፍንት ተፈራ
3. ዶ/ር አብዱልዋሳ አብዱላሂ
4. አቶ ታረቀኝ ቡልቡልታ
5. አቶ ጃፋር በድሩ
6. ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ
7. አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም
8. ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል
9. ዶ/ር ሙና አቡበክር የኢቢሲ ስራ አመራር ቦርድ አባላት ሆነው ተሹመዋል፡፡

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.0K views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 08:40:26
የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአርቲስቱ ቤት ሽኝት እየተደረገለት ይገኛል

የክብር ዶ/ር አርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአርቲስቱ ቤት ሽኝት እየተደረገለት ነው፡፡ ዛሬ ለአንጋፋው አርቲስት ዓሊ ቢራ የጀግና የክብር ሽኝት እና ሥርዓተ ቀብር ይፈጸማል፡፡

አስከሬኑ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ እስጢፋኖስ፤ ከዚያም በሠረገላ ወደ ወዳጅነት አደባባይ ይመጣል።በወዳጅነት አደባባይ የጀግና ስንብት ከተደረገለት በኋላም ወደ ድሬዳዋ አስክሬኑ እንደሚሸኝም ነው የተገለጸው።
  

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
1.4K views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 07:16:42 #Nairobi በትግራይ ክልል ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማስጀመር መሆኑን የተደራዳሪ ልዑካን መሪዎች ተናገሩ

በትግራይ ክልል የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማስጀመር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሚሆን የኢትዮጵያ እና የህወሓት ተደራዳሪ ልዑካንን የሚመሩት አቶ ሬድዋን ሁሴን እና አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። ሁለቱ የልዑካን መሪዎች ይህን ያሉት፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ አማጽያን የጦር አዛዦች ዛሬ ሰኞ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ተገናኝተው ድርድር ከመጀመራቸው በፊት ባደረጉት ንግግር ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን በዚሁ ንግግራቸው “የቴሌኮም፣ የኢነርጂ እና የባንክ አገልግሎቶችን መልሰን ማገናኘት አለብን። ከዚያ በፊት [ግን] ሰዎቻችን በቅድሚያ ምግብ እና መድኃኒት ይፈልጋሉ። ይህን ለማፋጠን እየሞከርን ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። ሬድዋን ክልሎችን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች “በባለፉ ጉዳዮች ከመዘፈቅ ይልቅ” ተስፋ እንዲፈነጥቁ እና መጪውን ጊዜ በጸጋ እንዲቀበሉ መንግስታቸው እያበረታታ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ህወሓትን በመወከል የፈረሙት አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፤ “በስምምነታችን የተካተቱ ብዙ መደረግ ያለባቸው ነገሮች አሉ” ብለዋል። ከእነዚህ ተግባራት መካከል የአገልግሎቶች መጀመር አንዱ መሆኑንም አቶ ጌታቸው ገልጸዋል። የአገልግሎቶቹ ቁጥር ከፍ ሲል በተደራዳሪ ወገኖች መካከል የሚኖረው “መተማመን እና ግንኙነት አብሮ እንደሚጨምር”፤ “በሰዎች አዕምሮ ውስጥም ተስፋ እንደሚዘራ” የገለጹት አቶ ጌታቸው፤ “ለማስፈን እየሞከርን ያለውን ሰላም የበለጠ ያጠናክራል” ብለዋል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
2.2K viewsedited  04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 21:53:04 በአዲስ አበባ ከተማ ፒያሳና መርካቶ አከባቢዎች የሚገኙ የተመረጡ የወርቅ መሸጫ መደብሮች ውስጥ የሚገኙ የወርቅ ጌጣ ጌጦች ተሰብሰቦ ግለሰቦች በፀጥታ ኃይሎች ታሠሩ፡፡

ሰኞ ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ከወርቅ መሸጫ መደብሮቹ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች በሳምንቱ አጋማሽ፣ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ለተጨማሪ ምርመራ የጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ታውቋል፡፡ስለወርቅ መደብሮቹ ጥያቄ የቀረበላቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጄይላን አብዲ፣ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ በመሆኑ ዝርዝር መረጃዎችን መስጠት እንደማይችሉ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስት አቶ ፍቃዱ ድጋፌ በበኩላቸው፣ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በቅንጅት በተሠራ ሥራ ‹‹በሕገ ወጥነት›› የተያዘ ‹‹ብዛት ያለው›› ወርቅ ተሰብስቦ ወደ ባንኩ መምጣቱን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ወርቁ የተሰበሰበበትን ቦታ ‹‹ይኼ ነው ብለው›› መናገር እንደማይችሉ ገልጸው፣ ‹‹ከድሬዳዋ ሁሉ የመጣ አለ፣ ከመርካቶም ከሌላ ቦታም [ተሰብስቧል] ብለዋል፡፡

ሪፖርተር ፒያሳ ወርቅ መሸጫ መድበሮች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ባደረገው ቅኝት 26 መደብሮች ተዘግተው ተመልክቷል፡፡በመደብሮቹ ውስጥ የሚገኘው ወርቅ ሰኞ ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በተሰበሰበበት ጊዜ በታዛቢነት የተገኙ ግለሰቦች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በመደብሮቹ ውስጥ የሚገኘውን ወርቅ የሰበሰቡት የታጠቁ የፀጥታ ኃይሎች፣ የደንብ ልብስ የለበሱና ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች ናቸው፡፡


ወርቅ የመሰብሰብና ባለቤቶቹን ወደ ፖሊስ ጣቢያ የመውሰድ ተግባሩ የተፈጸመው በተለዩ የወርቅ መሸጫ ሱቆች ላይ መሆኑ የተሰማ ሲሆን፣ ወርቃቸው ያልተሰበሰበ መደብሮች በመደበኛ ሥራቸው ላይ ተሠማርተው ከደንበኞች ጋር ሲገበያዩ ተስተውሏል፡፡ ወርቃቸው የተሰበሰበ አብዛኛዎቹ መደብሮች ሙሉ ለሙሉ ሲዘጉ አንዳንዶቹ በመጠኑ መዝጊያቸው (ሻተር) ተከፍቶ ታይተዋል፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በፒያሳ የሚገኝ ወርቅ ቤት ባለቤትና የተሰበሰበው ወርቅ ዓይነትና ብዛት ሲመዘገብ በታዛቢነት የተገኙ ግለሰብ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ወርቁን የመሰብሰብ ሥራው የተሠራው ሲቪል በለበሱት ግለሰቦች ሲሆን፣ በመደብሩ ውስጥ ያለው ወርቅ መሰብሰብ ከመጀመሩ በፊት ከጎረቤት መደብሮች ታዛቢዎች ተጠርተዋል፡፡ ‹‹እያንዳንዱ ወርቅ እየተለካ ሲሰበሰብ እስከ ምሽት አራት ሰዓት ድረስ ቆይቻለሁ›› በማለት ወርቅ የመሰብሰብ ሥራው እስከ ምሽት መቆየቱን አስረድተዋል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው በታዛቢነት የተገኙ ሦስት ግለሰቦች እንደገለጹት፣ ወርቁን ከሰበሰቡት ግለሰቦችም ሆኑ አብረዋቸው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች ለመደብር ባለቤቶች የፍርድ ቤት ማዘዣ ወረቀትም ሆነ መታወቂያ አላሳዩም፡፡አንዲት ታዛቢ፣ በታዛቢነት በተገኙበት ወርቅ ቤት ውስጥ ስለወርቅ ሰብሳቢዎቹ ማንነት ለቀረበው ጥያቄ የተሰጠው ምላሽ ‹‹ከበላይ አካል ነው›› የሚል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በታዛቢነት የተቆጠሩ ሌላ ግለሰብ በበኩላቸው፣ የፀጥታ አካለቱ የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡ በመደብሩ ወስጥ የነበረው ወርቅ ከተሰበሰበ በኋላ ወርቁ ወደ ብሔራዊ ባንክ፣ የመደብሮቹ ባለቤቶች ደግሞ ወደ ‹‹ማረፊያ ቤት›› እንደሚሄዱ እንደተነገራቸው አስታውሰዋል፡፡ወርቃቸው ከመደብር ውስጥ የተወሰደ የመደብር ባለቤቶች ስለተጠረጠሩበት ጉዳይ የተደረገላቸው ገለጻ እንደሌለ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሁሉም ግለሰቦች አስረድተዋል፡፡

ሪፖርተር፣ በፒያሳ ወርቅ በተሰበሰበበት አንድ ወርቅ ቤት ውስጥ አግኝቶ ያነጋገራቸው አንድ ግለሰብ፣ የመደብሩ ባለቤት በቁጥጥር ሥር ውለው ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ እንደ ግለሰቡ ገለጻ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች ረቡዕ ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ለተጨማሪ ምርመራ 12 ቀን  የጊዜ ቀጠሮ ተፈቅዶባቸዋል፡፡
ሪፖርተር ከግለሰቦቹ በፍርድ ቤቱ ስለመቅረባቸው ቢያረጋግጥም ምን ያህል ቀን እንደተፈቀደባቸው ትክክለኛ መረጃ አላገኘም፡፡ የፌደራል ፖሊስም ጉዳዩ በፍርድ ቤት በመያዙ መረጃ መስጠት እንደማይችል አስታውቋል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስት አቶ ፍቃዱ፣ ባንኩ በሕገወጥ መልኩ የሚደረግ የወርቅ ሽያጭና ዝውውር ላይ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥያቄ ማቅረቡን አስታውሰው ‹‹[ተሰብስቦ ወደ ብሔራቢ ባንክ የገባው ወርቅ] በዚያ መሠረት እንደመጡ ነው ምናውቀው፤›› ብለዋል፡፡በአገሪቱ ውስጥ ወርቅ የመሰብሰብ ሥልጣን ያለው ብሔራዊ ባንክ መሆኑንና የሚነግዱ አካላት ወርቁን የሚገዙት ከባንኩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ አቶ ፍቃዱ፣ ‹‹ወርቅ ከእኛ ካልገዛ ማንም ሰው መያዝ አይችልም፣ ከእኛ ደግሞ የተገዛ ወርቅ የለም›› ካሉ በኋላ ‹‹የተያዘባቸው ሰዎች ከዚህ ካልገዙ ከየት እንደገዙ መግለጽ አለባቸው፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ መሆኑን አስታውሰውም ግለሰቦቹ ስለተሰበሰበባቸው ወርቅ ሕጋዊነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከሆነ እንደሚመለስላቸው ካልሆነ ግን የተያዘው ወርቅ እንደሚወረስ ገልጸዋል፡፡


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
3.9K views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 18:36:48
ጌታቸው ረዳ ሰላም ለትግራይ ህዝብ ስለሚያሻው ነው ተደራድረን ሰላም ያመጣነው። ህዝባችን ከምንም በላይ ሰላም ያስፈልገዋል።

ጌታቸው ረዳ ቲውተር አካውንት


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.4K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 16:16:19
በኢንዶኔዥያ 46 የተለያዩ ሴቶች ጋር ትዳር የመሰረተዉ ግለሰብ ለ88ኛ ጊዜ ሊሞሸር ነዉ

በኢንዶኔዥያ በምእራብ ጃቫ ነዋሪ የሆነዉ ካን የሩዝ ገበሬ ሲሆን አስገራሚ የህይወት ታሪክ አለው።የ61 ዓመቱ ሰዉ በህይወት ዘመኑ ነበአጠቃላይ 87 ጊዜ ያገባ ሲሆን ለ88ኛ ጊዜ ከቀድሞ ሚስቶቹ መካከል ከአንዷ ጋር በድጋሚ ለመሞሸር በዝግጅት ላይ መሆኑ ተነግሯል። ካን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያገባ በ14 ዓመቱ የነበረ ሲሆን በሁለት አመት ከምትበልጠው ልጃገረድ ጋር በወቅቱ ትዳር ይመሰርታል፡፡

ትዳራቸው ለ 2 ዓመታት ብቻ የቆየ ሲሆን በወቅቱ ታዳጊዉ ፍቺ እንደፈጸመ አዲስ ሚስት ከመፈለግ አላገደውም፡፡ለምንድን ነው የሚወዳቸውን ሴቶች ሁሉ ማግባቱን የቀጠለው በሚል ለካአን ለቀረበዉ ጥያቄ ሲመልስ ስለማከብራቸው ነው ብሏል።ለአንድ ሳምንት ብቻ የቆየ ትዳሩን ጨምሮ ለ87 ጊዜ ያህል ሲሞሸር 40 ያህሉ ህጋዊ በሆነ መንገድ ተፈራርሞ አግብቷል፡፡

87 ጊዜ ጋብቻ ቢፈጽምም 46 ሴቶችን ብቻ አግብቷል፡፡ይህ ሊሆን የቻለዉ ደግሞ አንዳንዶቹን ሶስት እና አራት ጊዜ በድጋሚ በማግባቱ የተነሳ ነዉ፡፡ካን ከቀድሞ ሚስቱ ጋር ለ88ኛ ጊዜ ጋብቻ ሊመሰርት መሆኑን ተከትሎ እንደተናገረዉ “ከተለያየን ረጅም ጊዜ ቢያልፈውም በመካከላችን ያለው ፍቅር አሁንም ጠንካራ ነው” ብሏል፡፡ የቀድሞ ትዳራቸው የፈጀው ለ 4 ወራት ብቻ እንደሆነ ተናግሯል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
1.6K views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 14:31:09
መረጃ!

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አመራሮችና እና የህወሀት ወታደራዊ አመራሮች በኬኒያ ናይሮቢ ከተማ ዛሬ ውይይት እያደረጉ ነው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የህወሓት ባለስልጣናት የትግራይ ታጋዮችን ትጥቅ መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየተወያዩ ነው። ስብሰባው አሁን እየተካሄደ ነው።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
2.6K views11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ