Get Mystery Box with random crypto!

አማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የተሟላ ድጋፍ ለማቅረብ መቸገሩ ተገለጸ! በአማራ ክልል | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

አማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የተሟላ ድጋፍ ለማቅረብ መቸገሩ ተገለጸ!

በአማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች፣ የተሟላ ድጋፍ ለማቅረብ መቸገሩን የክልሉ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።ኮሚሽኑ በአሁኑ ጊዜ በአማራ ክልል ከ850 ሺሕ በላይ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች መኖራቸውን ጠቅሶ፣ በተለይም ሕወሓት በፈጠረው ቀውስ የተነሳ ምግብ ነክ የሆኑና ምግብ ነክ ያልሆኑ ሰብዓዊ ድጋፎችን የሚሹ ከ8 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች እንዳሉ አስታውቋል።

ይህን ተከትሎም፣ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ የተሟላ ድጋፍ ማቅረብ እንዳልተቻለ ያነሳው ኮሚሽኑ፣ የትራንስፖርት ችግር፣ የጸጥታ ሁኔታ እንዲሁም የሩስያና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ የተፈጠረው የምግብ እጥረትና የዋጋ ቀውስ ዋነኛ እንቅፋቶች መሆናቸውን አስገንዝቧል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet