Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ezmerejaet
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4
የሰርጥ መግለጫ

እንዴት አደርሽ ኢትዮጵያዬ ! 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-11-11 09:28:39
ትኩረት #Share ይደረግ የኤልያስ መሰረት መልዕክት ነው።

#ኦሮሚያ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በመንግስት እና በታጣቂዎች መሀል ውጊያ እየተካሄደባቸው ባሉ አካባቢዎች ንፁሀን ዜጎች ለሞት፣ መቁሰል፣ መፈናቀል እና መራብ እየተዳረጉ ነው።

በተለይ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በተደረጉ ውጊያዎች እና የአየር ጥቃቶች በርካቶች ህይወታቸውን እንዳጡ እና እንደቆሰሉ የደረሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የ11ኛ ክፍል ተማሪ ልጃቸውን ያጡ አባት እንዲሁም በአየር ጥቃት ከ15 በላይ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን የቀበሩ አንድ የሀይማኖት አባት (ሁለቱም ከ ቢላ ከተማ) ይህን በስልክ አረጋግጠውልኛል።

ጉዳዩን የአለም አቀፍ ሚድያ ችላ ብሎታል፣ የሀገር ውስጥ ሚድያው ረስቶታል፣ መንግስትም መረጃ እየሰጠበት አይደለም። ታጥቆ የሚዋጋው በፍላጎቱ ሊሆን ይችላል... በንፁሀን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ግን ሁላችንንም ሊያሳስብ ይገባል።

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ ለነበረው ጦርነት የተገኘው መፍትሄ ወደ ኦሮሚያ ክልልም እንዲዘልቅ ጥረት ማድረግ ይገባል፣ ህዝብ እያለቀ ነው።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.8K views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 07:37:53
ጃዋርመሀመድ

የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጃዋር መሐመድ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ አለ ያለ ያሉት‹‹የእርስ በርስ ጦርነት››ሊፈታ የሚችለው መሪዎች በጠረጴዛ ዙርያ በሚያደርጉት ድርድር ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አቶ ጃዋር ኅዳር 1፣ 2015 በገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ለመቋጨት የሰላም ስምምነት መፈረሙን አስታውሰው፤ ልክ እንደ ሰሜኑ ሁሉ በኦሮሚያ ያለው ‹‹የእርስ በርስ ጦርነት››ሰበቡ ፖለቲካዊ ልዩነት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ጃዋር በጽሑፋቸው ሰበቡ‹‹የፖለቲካ ልዩነት ነው››ያሉት ይህ ጦርነት፤መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለውም መሪዎቹ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው በጋራ ጉዳዮች ላይ ንግግር እና ድርድር በማድረግ ሲስማሙ ብቻ መሆኑንም አስፍረዋል፡፡

አቶ ጀዋር ይህ አስተያየት የመጣው ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀውና ኦነግ ሸኔ ሲል በሚጠራው ቡድን እና በመንግሥት ኃይሎች በቡድኑ መካከል ባለው ግጭት ንጹሐን ኢላማ ተደርገዋል የሚሉ መረጃዎች በወጡበት ወቅት ነው፡፡ አቶ ጃዋር፤ ባለፉት ሳምንታት በምዕራብ ሸዋ እና በምዕራብ ወለጋ የተለያዩ አካባቢዎች በአየር በሚሰነዘር ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን መገደላቸውን ገልጸዋል፡፡  አያይዘውም በጥቃቱ ሳቢያም ሚሊዮኖች መፈናቀላቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ነገርግን ስቃያቸው እውቅና ተነፍጎታል ብለዋል፡፡

አቶ ጃዋር "አልፎ አልፎ ሽፋን ይሰጡ የነበሩትም አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂውማን ራይትስ ዎች እንኳን ተስፋ የቆረጡ ይመስላሉ " ሲሉ ገልፀዋል።"እየመረጡ መጮህ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም አያመጣም። "ያሉት አቶ ጃዋር" ወይ ለአጠቃላይ ሀገራዊ የሰላም ሂደት እንሰራለን ወይም ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ሲቀጥሉ እንመለከታለን። " ብለዋል። ሼር

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.8K views04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 21:49:13
#ቤንሻንጉል!

ከአሶሳ ወደ ህዳሴ ግድብ መሄጃ በሲርባ ወረዳ በህዳሴ ግድብ ቃንቁር ካምፕ በሚባል የቤህነን አማፅያን  በወሰዱ እርምጃ ብያንስ 3 በላይ የፀጥታ ሃይሎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። አሶሳ ከተማ ከወትሮ በተለየ አኳሃን ቁጥራቸው ከነዋሪው በማይተናነስ ኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል እና የመከላከያ ሃይል ብዛት ተጨናንቃለች።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
2.2K viewsedited  18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 21:44:11
ጥቆማ

በቅርብ ጊዜ ትልቅ ተወዳጅነትን ያተረፈዉ እና ብዙ ተከታዮችን ያገኘው እንዲሁም “ወደ ቀድሞ ከፍታችን እንመለሳለን” በሚል  የሚዲያ ሽፋን ላልተዳረሰባቸዉ ድምፅ ለመሆን  አንኳር መረጃ ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ #join        https://t.me/+WN84qy0V9SkcQiQB
https://t.me/+WN84qy0V9SkcQiQB
2.4K views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 21:15:52 #ሼር

ኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን በሰዲ ጫንቃ ወረዳና በሀዋገላን ወረዳ በተለምዶ ቄጦ ሠፈራ ጣቢያ የሚኖሩ ንፁሃን የድረሱልን ጥሪ እያስተላለፉ ነው።በውስጥ በተደጋጋሚ እየደረሱኝ ያሉት መረጃዎች እንደሚየመለክቱት በመደር 3፣16፣20 እና 21 የሚኖሩ ህዝቦች የወረዳው አስተዳደር ሽሹ ከቤታችሁ እንዳታድሩ ሸኔ ገብቶ አዳሩን እንዳይጨርሳችሁ በማለት አስጠንቅቆናል በዚህም ምክንያት ቤት ንብረታችንን ትተን እየወጣን ነው ብለወል።ጭንቅ ላይ ናቸው።ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር አድርጉት

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
2.8K viewsedited  18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 20:26:54
እስራአል ዳንሳ በጥይት ተመታ

ሐዋርያው እስራአል ዳንሳ ከአዲስ አበባ 590 ኪሜ የምትገኘው በኦሮሚያ ክልል የምትገኘው ነጌሌ ቦረና ኮንፍረስ አገልግሎ ሲመለስ ለአዲስ አበባ 140 ኪሜ ርቀት ያላት መቂ ከተማ  አካባቢ ሲደርስ ባልታወቁ የታጠቁ ሰዎች በአካባቢው በከፈቱት የተኮስ ሩምታ በሐዋርያ እስራኤል ዳንሳ ላይ እግሩ ላይ በጥይት ተመቷል።

መቂ አካባቢ በታጠቁ ሰዎች በተከፈተው ተኮስ የሞቱ ሰዎች እና በርካታ መኪናዎች ተቃጥለው ነበር ።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
3.6K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 18:40:47
ባለቤቱን ገድሎ ሊያመልጥ የነበረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ

በትላንትናው ዕለት ቱሉዲሚቱ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ ከባለቤቱ ጋር በነበረው ግጭት ምክንያት ባለቤቱን ገድሎ ሊያመልጥ የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ሴቶች እና ህጻናት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽ እና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በረከት በቀለ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት፤ ግለሰቡ ከባለቤቱ ጋር በትዳር አብረው የቆዩና ኹለት ልጆችን ያፈሩ ሲሆን፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ቢሆንም የውጪ አገር ዜግነት ያለው መሆኑ ገልጸዋል፡፡

በወቅቱ በንብረት ውርስ ክፍፍል ምክንያት በመካከላቸው ጸብ ተፈጥሮ የነበረ መሆኑን የገለጹት በረከት፤ ተጠርጣሪው ወንጀሉን ፈፅሞ ሊያመልጥ ሲሞክር በቁጥጥር ሥር መዋሉንም ለሬዲዮ ጣቢያው ጨምረው ተናግረዋል፡፡
 

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.2K views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 15:23:34
ጄነራል ተፈራ ማሞ ወደ ውጭ እንዳይወጡ ተከለከሉ

ጀነራል ተፈራ ማሞ ከላይ በመጣ ትዕዛዝ በሚል ለህክምና ከሀገር ሊወጡ ሲሉ ከኤርፖርት እንዲመለሱ ተደርጓል።

የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ጀነራል ተፈራ ማሞ ትላንት ጥቅምት 30/2015 ዓም ምሽት አምስት ሰዓት ለነበራቸው በረራ  ቀደም ብለው ሁለት ሰዓት ላይ ደርሰው የነበረ ቢሆንም መውጣት አለመቻላቸው ተገልጿል።

ጀነራሉ ለህክምና ወደ እስራኤል ለማቅናት ትላንት ምሽት ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቢደርሱም ከላይ በመጣ ትዕዛዝ በሚል እንዳይሄዱ መከልከላቸውን ሮሃ ሚዲያ ከምንጮቹ ለማረጋገጥ መቻሉን ዘግቧል።

በመንግስትና በህወሃት መካከል ለሚደረገው ድርድር ጀነራሉን  ያካተተ የአማራ ሕዝብ ተደራዳሪ ልዑክ መቋቋሙን የአማራ ማኅበር በአሜሪካ ለዲፕሎማቶች በጻፈው ደብዳቤ ማሳወቁ ይታወሳል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.0K views12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 15:18:24 በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን በመንግሥት እና በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት ሳቢያ  ነቀምቴ ከተማን ከቤንሻንጉል ክልል አሶሳ ከተማ ጋር በሚያገናኘው መንገድ ላይ ትራንስፖርት መቋረጡን ዶይቸቬለ ዘግቧል። በመንገዱ ላይ መጓጓዣ የተቋረጠው፣ ታጣቂዎቹ በነቀምቴ ከተማ ላይ ባለፈው ዕሁድ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ ነው። በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ነጆ እና መንዲ በተባሉ ከተሞች ባንክና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት መዘጋታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል ተብሏል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.6K views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 13:14:11 በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሰብዓዊ ድጋፍን በፍጥነት ለማድረስ እንዲቻል አራት ቡድኖች ተቋቁመው ወደ ተግባር ተሸጋግረዋል

- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሰብዓዊ ድጋፍን በፍጥነት ለማድረስ እንዲቻል አራት ቡድኖች ተቋቁመው ወደ ተግባር መሸጋገራቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሣ በሰጡት መግለጫ በሰላም ስምምነቱ መሰረት ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻል በአፋር በኩል ካለው መንገድ በተጨማሪ ሌሎችም መከፈታቸውን ገልጸዋል።

የሰብዓዊ ድጋፉ በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆንም በአራት አቅጣጫ በኩል ድጋፉን የሚያስተባብሩ አራት ኮሚቴዎች ተቋቁመው ወደ ተግባር መግባታቸውንም ተናግረዋል።

የሰብዓዊ ድጋፉን በፍጥነት ለማድረስም በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልፀው በአሁኑ ጊዜም በተለያዩ ቦታዎች ተደራሽ በመሆን ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ከጥቅምት 20 ቀን እስከ 27 ድረስም በመጀመሪያ ዙር በሽሬ፣አክሱም ፣ ሰለክለካ እና በዚህ አቅጣጫ ለሚገኙ ሌሎች አካባቢዎች ለ108 ሺ ዜጎች ስንዴ እና አልሚ ምግቦች ድጋፍ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በአላማጣ በኩል ባሉ የተለያዩ አከባቢዎች በመጀመሪያ ዙር ለ287ሺህ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ መደረጋቸውን ጠቁመዋል።

በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው መሰረት ልማቶችን መልሶ ለመገንባት እና አገልግሎት ለማስጀመር መንግስት ቁረጠኛ
ነው ብለዋል።

በዚህም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ባልተጀመረበት አከባቢዎች ለማስጀመር እየተሰራ ነው ብለዋል።

አሁን ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ካገኙ ከተሞች በተጨማሪ በቅርቡ በርካታ አከባቢዎች ላይ ተደራሽ ለማድረግ የጥገና ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል።
@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.1K viewsedited  10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ