Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሰብዓዊ ድጋፍን በፍጥነት ለማድረስ እንዲቻል አራት ቡድኖች ተቋቁመው ወደ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሰብዓዊ ድጋፍን በፍጥነት ለማድረስ እንዲቻል አራት ቡድኖች ተቋቁመው ወደ ተግባር ተሸጋግረዋል

- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሰብዓዊ ድጋፍን በፍጥነት ለማድረስ እንዲቻል አራት ቡድኖች ተቋቁመው ወደ ተግባር መሸጋገራቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሣ በሰጡት መግለጫ በሰላም ስምምነቱ መሰረት ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻል በአፋር በኩል ካለው መንገድ በተጨማሪ ሌሎችም መከፈታቸውን ገልጸዋል።

የሰብዓዊ ድጋፉ በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆንም በአራት አቅጣጫ በኩል ድጋፉን የሚያስተባብሩ አራት ኮሚቴዎች ተቋቁመው ወደ ተግባር መግባታቸውንም ተናግረዋል።

የሰብዓዊ ድጋፉን በፍጥነት ለማድረስም በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልፀው በአሁኑ ጊዜም በተለያዩ ቦታዎች ተደራሽ በመሆን ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ከጥቅምት 20 ቀን እስከ 27 ድረስም በመጀመሪያ ዙር በሽሬ፣አክሱም ፣ ሰለክለካ እና በዚህ አቅጣጫ ለሚገኙ ሌሎች አካባቢዎች ለ108 ሺ ዜጎች ስንዴ እና አልሚ ምግቦች ድጋፍ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በአላማጣ በኩል ባሉ የተለያዩ አከባቢዎች በመጀመሪያ ዙር ለ287ሺህ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ መደረጋቸውን ጠቁመዋል።

በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው መሰረት ልማቶችን መልሶ ለመገንባት እና አገልግሎት ለማስጀመር መንግስት ቁረጠኛ
ነው ብለዋል።

በዚህም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ባልተጀመረበት አከባቢዎች ለማስጀመር እየተሰራ ነው ብለዋል።

አሁን ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ካገኙ ከተሞች በተጨማሪ በቅርቡ በርካታ አከባቢዎች ላይ ተደራሽ ለማድረግ የጥገና ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል።
@Ezmerejaet
@Ezmerejaet