Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን በመንግሥት እና በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት ሳ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን በመንግሥት እና በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት ሳቢያ  ነቀምቴ ከተማን ከቤንሻንጉል ክልል አሶሳ ከተማ ጋር በሚያገናኘው መንገድ ላይ ትራንስፖርት መቋረጡን ዶይቸቬለ ዘግቧል። በመንገዱ ላይ መጓጓዣ የተቋረጠው፣ ታጣቂዎቹ በነቀምቴ ከተማ ላይ ባለፈው ዕሁድ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ ነው። በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ነጆ እና መንዲ በተባሉ ከተሞች ባንክና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት መዘጋታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል ተብሏል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet