Get Mystery Box with random crypto!

ጄነራል ተፈራ ማሞ ወደ ውጭ እንዳይወጡ ተከለከሉ ጀነራል ተፈራ ማሞ ከላይ በመጣ ትዕዛዝ በሚል ለ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

ጄነራል ተፈራ ማሞ ወደ ውጭ እንዳይወጡ ተከለከሉ

ጀነራል ተፈራ ማሞ ከላይ በመጣ ትዕዛዝ በሚል ለህክምና ከሀገር ሊወጡ ሲሉ ከኤርፖርት እንዲመለሱ ተደርጓል።

የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ጀነራል ተፈራ ማሞ ትላንት ጥቅምት 30/2015 ዓም ምሽት አምስት ሰዓት ለነበራቸው በረራ  ቀደም ብለው ሁለት ሰዓት ላይ ደርሰው የነበረ ቢሆንም መውጣት አለመቻላቸው ተገልጿል።

ጀነራሉ ለህክምና ወደ እስራኤል ለማቅናት ትላንት ምሽት ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቢደርሱም ከላይ በመጣ ትዕዛዝ በሚል እንዳይሄዱ መከልከላቸውን ሮሃ ሚዲያ ከምንጮቹ ለማረጋገጥ መቻሉን ዘግቧል።

በመንግስትና በህወሃት መካከል ለሚደረገው ድርድር ጀነራሉን  ያካተተ የአማራ ሕዝብ ተደራዳሪ ልዑክ መቋቋሙን የአማራ ማኅበር በአሜሪካ ለዲፕሎማቶች በጻፈው ደብዳቤ ማሳወቁ ይታወሳል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet