Get Mystery Box with random crypto!

ትኩረት #Share ይደረግ የኤልያስ መሰረት መልዕክት ነው። #ኦሮሚያ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በመን | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

ትኩረት #Share ይደረግ የኤልያስ መሰረት መልዕክት ነው።

#ኦሮሚያ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በመንግስት እና በታጣቂዎች መሀል ውጊያ እየተካሄደባቸው ባሉ አካባቢዎች ንፁሀን ዜጎች ለሞት፣ መቁሰል፣ መፈናቀል እና መራብ እየተዳረጉ ነው።

በተለይ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በተደረጉ ውጊያዎች እና የአየር ጥቃቶች በርካቶች ህይወታቸውን እንዳጡ እና እንደቆሰሉ የደረሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የ11ኛ ክፍል ተማሪ ልጃቸውን ያጡ አባት እንዲሁም በአየር ጥቃት ከ15 በላይ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን የቀበሩ አንድ የሀይማኖት አባት (ሁለቱም ከ ቢላ ከተማ) ይህን በስልክ አረጋግጠውልኛል።

ጉዳዩን የአለም አቀፍ ሚድያ ችላ ብሎታል፣ የሀገር ውስጥ ሚድያው ረስቶታል፣ መንግስትም መረጃ እየሰጠበት አይደለም። ታጥቆ የሚዋጋው በፍላጎቱ ሊሆን ይችላል... በንፁሀን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ግን ሁላችንንም ሊያሳስብ ይገባል።

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ ለነበረው ጦርነት የተገኘው መፍትሄ ወደ ኦሮሚያ ክልልም እንዲዘልቅ ጥረት ማድረግ ይገባል፣ ህዝብ እያለቀ ነው።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet