Get Mystery Box with random crypto!

ጃዋርመሀመድ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጃዋር መሐመድ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ አለ ያለ ያሉ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

ጃዋርመሀመድ

የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጃዋር መሐመድ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ አለ ያለ ያሉት‹‹የእርስ በርስ ጦርነት››ሊፈታ የሚችለው መሪዎች በጠረጴዛ ዙርያ በሚያደርጉት ድርድር ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አቶ ጃዋር ኅዳር 1፣ 2015 በገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ለመቋጨት የሰላም ስምምነት መፈረሙን አስታውሰው፤ ልክ እንደ ሰሜኑ ሁሉ በኦሮሚያ ያለው ‹‹የእርስ በርስ ጦርነት››ሰበቡ ፖለቲካዊ ልዩነት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ጃዋር በጽሑፋቸው ሰበቡ‹‹የፖለቲካ ልዩነት ነው››ያሉት ይህ ጦርነት፤መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለውም መሪዎቹ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው በጋራ ጉዳዮች ላይ ንግግር እና ድርድር በማድረግ ሲስማሙ ብቻ መሆኑንም አስፍረዋል፡፡

አቶ ጀዋር ይህ አስተያየት የመጣው ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀውና ኦነግ ሸኔ ሲል በሚጠራው ቡድን እና በመንግሥት ኃይሎች በቡድኑ መካከል ባለው ግጭት ንጹሐን ኢላማ ተደርገዋል የሚሉ መረጃዎች በወጡበት ወቅት ነው፡፡ አቶ ጃዋር፤ ባለፉት ሳምንታት በምዕራብ ሸዋ እና በምዕራብ ወለጋ የተለያዩ አካባቢዎች በአየር በሚሰነዘር ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን መገደላቸውን ገልጸዋል፡፡  አያይዘውም በጥቃቱ ሳቢያም ሚሊዮኖች መፈናቀላቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ነገርግን ስቃያቸው እውቅና ተነፍጎታል ብለዋል፡፡

አቶ ጃዋር "አልፎ አልፎ ሽፋን ይሰጡ የነበሩትም አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂውማን ራይትስ ዎች እንኳን ተስፋ የቆረጡ ይመስላሉ " ሲሉ ገልፀዋል።"እየመረጡ መጮህ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም አያመጣም። "ያሉት አቶ ጃዋር" ወይ ለአጠቃላይ ሀገራዊ የሰላም ሂደት እንሰራለን ወይም ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ሲቀጥሉ እንመለከታለን። " ብለዋል። ሼር

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet