Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ezmerejaet
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4
የሰርጥ መግለጫ

እንዴት አደርሽ ኢትዮጵያዬ ! 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-11-02 16:51:10
"በታሪኳ ለጠላት ተንበርክካ የማታውቀው ወዳጃችን ኢትዮጵያ የወንበዴዎች ስብስብ በፈጠሩባት ችግር ስትታመስ በማየታችን በእጅጉ ብናዝንም ዛሬም ጠላቶቿን እያሸነፈች መሆኑን ለማየት በመቻላችን እጅግ ደስ ብሎናል።"
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫኬር

via ezmerejaet

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.5K viewsedited  13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 13:31:55 በምዕራብ ወለጋ ዞን እና አሶሳ ዞን አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጊያ መቀስቀሱ ተገለፀ!

በሰሞኑ በርካታ የወለጋና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አዋሳኝ አከባቢ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በርካታ ከተሞችን ኦነግ ሸኔ ተቆጣጥሯል።

በዚህም መሠረት፦
ከአሶሳ- ነቀምት v
ከነቀምት- ጊምቢ
ከጊምቢ- ነጆ
ከጊምቢ- ደንቢደሎ
ከነጆ- ቤጊ
ከቤጊ- አሶሳ እንዲሁም
** ከጉትን- ነቀምት እና እስከ ሐሮ ድረስ መንገዱ ዝግ በመሆኑ የሚመለከታቸው የመንግስት አካል በአስቸኳይ የመፍትሔ አካል እንዲሆኑ ኗሪዎች ጥሪ አቅርበዋል
via ezmerejaet

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
6.0K viewsedited  10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 12:26:33 የሰላም ንግግሩ መጨረሻ ዛሬ እንደሚሆን ይገመታል።
በዚህም ከሰአታት ብሆላ መግለጫ እንደሚሰጥ ሲጠበቅ የምስራቅ አፍሪካ ልዩ ልኡክ መሪ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የድርድሩን መግለጫ ሰጪ እንደሚሆኑ ተነግሯል ።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.9K viewsedited  09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 09:01:15
በቴሌቪዥን እና በሶፋ ከባንክ ገንዘብ መበደር ሊፈቀድ ነው።

ከዚህ ቀደም ከገንዘብ ተቋማት ለሚወሰድ ብድር በማስያዣነት የሚያገለግሉ የመኪና ሊብሬ አልያም የቤት ካርታ ይጠየቅበት የነበረው አሰራር መሰረታዊ የሚባል ለውጥ ተደርጎበት እንደ በግ ፣ ግመል ፣ በሬ ፣ ላም ፣ ፍየል ፣ ቴሌቪዥን ፣ ሶፋ እና ሌሎችም ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን በማስያዝ ገንዘብ ከባንክ አልያም ከቁጠባ እና ብድር ተቋማት መበደር የሚያስችል አሰራር ለመተግበር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አሳውቋል፡፡
via ezmerejaet

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
1.5K viewsedited  06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 08:49:06
አየር መንገዱ "ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ" ሽልማት 2022 ተሸላሚ ሆነ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን ሽልማት ከቢዝነስ ትራቭለር ሪደርስ አዋርድ ሲያገኝ ይህ ለተከታታይ ሦስተኛ ዓመት መሆኑን በይፉዊ የቲውተር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመስከረም ወር 2015 በለንደን SKYTRAX 2022 የአለም ምርጥ አየር መንገዶች ሽልማት ላይ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ በመባል መሸለሙ ይታወሳል። በዚሁ SKYTRAX ምርጥ የአለማችን 100 አየር መንገዶች ዝርዝር ውስጥም አስራ አንድ ደረጃዎችን በማሻሻል 26ተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ መቻሉ ተገልጿል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
1.6K viewsedited  05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 20:10:32
የደቡብ አፍሪካው የሰላም ንግግር “አራት ግቦች” እንዳሉት አሜሪካ ገለጸች

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና የህወሓት የሰላም ንግግር መራዘም፤ ሁለቱ ወገኖች “የተራራቀ” አቋም ይዘው ወደ ደቡብ አፍሪካ ማምራታቸውን እንደሚጠቁም የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቃባይ ተናገሩ። ቃል አቀባዩ ኔድ ፕራይስ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደው የሰላም ንግግር የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህወሓት “ልዩነታቸውን የሚወያዩበት እና በመካከላቸው ያለውን ርቀት ማጥበብ የሚቀጥሉበት እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

ቃል አቃባዩ ይህን ያሉት፤ ስምንተኛ ቀኑን ስላስቆጠረው የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የሰላም ንግግርን በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ትላንት ምሽት በሰጡት መግለጫ ነው። ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የተጀመረው የሰላም ንግግር እስከ እሁድ ጥቅምት 20 እንደሚቆይ የደቡብ አፍሪካ መንግስት አስታውቆ የነበረ ቢሆንም፤ ንግግሩ እስከ ትላንት ምሽት መቀጠሉን ከቦታው የወጡ ዘገባዎች አመልክተዋል።

የሰላም ንግግሩ እስከ ረቡዕ ድረስ ይቀጥላል መባሉ የሂደቱን አለመሳካት ያመልክት እንደሆነ የተጠየቁት ፕራይስ፤ ሁለቱ ወገኖች “የተራራቀ” አቋም ይዘው ወደ ደቡብ አፍሪካ ማምራታቸውን የሚጠቁም ነው ብለዋል። የሰላም ንግግሩ መራዘም ሁለቱ ወገኖች “አብረው ለመቀመጥ ፈቃደኛ ሆነው መቀጠላቸውንም አመላካች” ጭምር ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል። ፕራይስ በትላንቱ ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው፤ በኢትዮጵያ ተፋላሚ ወገኖች መካከል የሚደረገው የሰላም ንግግር አራት ግቦች እንዳሉት አስረድተዋል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.9K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 18:55:28
በኦሮሚያ ክልል ቱሉሞዬ በሚባል ስፍራ ማለትም ከአዳማ ወደ አሰላ በሚወስደዉ መንገድ ኢቴያ ከሚባል አነስተኛ ከተማ 17 ኪሜ እርቀት ላይ በእንግሊዝ መንግስት 'ማሪዎት''ግሩፕ እና የኬንያው ድርጅት በጋረ ግዙፍ የቁፋሮ ስራ የሚሰሩበት ቦታ ነዉ:: ትልቅ የሆነ የጅኦተርማል ክምችት እንዳለበትም
ይነገርለታል።
ታዲያ እሁድ እለት በ10 ሰአት በድንገት ተኩስ ይከፈታል ,ተኮሾቹ ኢለማቸዉን ወደ ካምፓኒዉ አድርገው ነበር የሚተኩሱት,በአካባቢውም ሸኔ ገባ የሚባል ረብሻ ተፈጠረ,ሰራተቹም እግሬ አዉጪኝ ብለዉ እግራቸው እንዳመራ ፈረጠጡ።
አሁን ላይ ኦነግ ሸኔ የአቴያን ገጠሩን ሙሉ ለሙሉ እንደተቆጣጠሩት ታዉቋሎ,ካምፓኒዉ ጋር ግን አልደረሱም
ኦነግ ሸኔ ግን የት ሲደርስ ነዉ በቃህ የሚባለው ??

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
354 views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 11:14:21
ድርድሩ ዛሬ ማክሰኞም ይቀጥላል

እሁድ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ይኸው የሰላም ንግግር ተራዝሞ ዛሬም ቀጥሎ እንደሚካሄድ ተሰምቷል።

ከዚሁ የሰላም ንግግር ጋር በተያያዘ ፤ የአፍሪካ ህብረት ንግግሩ የሚጠናቀቅበት ቀነ ገደብ እንዳልተቀመጠ ለኤኤፍፒ በሰጠው ቃል ገልጿል።የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ቃል አቀባይ ኤባ ካሎንዶ ፤ " በንግግሩ (በሰላም ንግግሩ) ላይ ቀነ ገደብ አልተቀመጠም " ብለዋል።

አንዳንድ የውጪ ሚዲያዎች ግን ድርድሩ እስከ እሮብ እንደሚቀጥል እና የጋራ መግለጫም እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
3.9K viewsedited  08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 07:56:27
የገዛ ቀጣሪዋን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ወንጀሉ የተፈጸመው ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 10:45 ሰዓት ሲሆን ቦታው ደግሞ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው አስኮ ሊዝ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።ተከሳሽ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ከምትሠራበት ከወ/ሮ ፋሲካ ተሾመ ቤት ሲሆን በመሃላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ሟችን በቡና ዘነዘናና በስለት የተለያዩ የሰውነት አካላቸው ላይ ጉዳት በማድረስ የመግደል ወንጀል ፈጽማለች።

ፖሊስ መረጃው ከህብረተሰቡ ከደረሰው በኋላ በአደረገው ብርቱ ፖሊሳዊ ክትትልና ምርመራ ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ከፈጸመች ከሦስት ቀናት በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሏን ገልጾ ምንም እንኳ የፖሊስ ተግባር ወንጀልን አስቀድሞ መከላከል ቢሆንም ተፈጽሞ ሲገኝም ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ተጠርጣሪዎችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚቻል ገልጿል።ህብረተሰቡ የቤት ሠራተኞችን ሲቀጥር በቂ ዋስትናም ማቅረብ እንዳለባቸው ጭምር ሊያስገድድ እንደሚገባ ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.3K views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 07:56:16 መርጌታ ይሃንስ ባሕላዊ  መዳኒት ቀማሚ የምነሰጣቸው አገልግሎቶች በጥቂቱ ።
1,  መፍትሔ_ሥራይ (የጠላት ድግምት መሻሪያ) 0908104860
2,  ለቡዳ
3,  ለቁራኛ
4, #መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5,  ለጋኔን
6, ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7, ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)
8,  ለፀር (ለጠላት)
9, ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10,  ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11,ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12, ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13, መስተፋቅር
14 ;ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15,ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16, ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17, የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18,ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19; መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20, መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21, ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22, ለልሳነ_ሰብእ
23, ለበረከት
24,ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25,ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26,ጸሎተ_ዕለታት
27,ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28, ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29, ለከበሮ
30,ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31, ለሙግት
32,ለሰላቢ
33,ለስንፈት ወሲብ
34,ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35, ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36,ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)
37, ለዱላ( ዱላ የማያስመታ)
38,መንስኤ_እስኪት (ለወንድ የመራቢያ አካሉ ለደከመ ላነሰ)
39,ህገ_ጠብቅ (የትዳር አጋራችን ወደሌላ እንዳይሄድ የሚያስር
እንዳይዘሙት የሚከለክል)
40, ለአይነ_ሰብእ (ከሰው አይን የሚጠብቅ)
41;ለአዙሪት
42; ለአስቸጋሪና ተመላላሽ ሲህር
43;ለሪህ በሽታ
44;የመገጣጠሚያ ህመም
45;ለጉልበት ድርቀት
46;የባት ህመም
47;የወገብ ህመም
48;የአንገትና ትከሻ ህመም
49;የከረመ ደረቅ ሳል
50;ለደም ግፊት
51;የሆድ መረበሽ
52;የከፋ የሆድ ድርቀት
53;በመኝታ ሽንት ለሚያመልጠው
54;የአእምሮ ጭንቀት፣ ድብርት፣         ከሰው  መገለል፣እንቅልፍ ማጣት
55; እንቅልፍ መብዛት
56;የተለየ የቆዳ ህመም
57;ክብደት ለመቀነስ
58;የእንቅርት በሽታ
59;ራስ ምታት ከሚከተሉት ህመሞች ጋ
60; አይን አካባቡ ውጥረት ካለ
61; የሳይነስ ህመም
62;የሆድ ድርቀትና የሆድ ህመም
63;የወር አበባ ችግር ካለ
64;የወገብ መንሸራተት ካለ
65;ውጥረትና የአእምሮ ጭንቀት
66;ለከፍተኛ ራስ ምታት
67;ማስታወስ፣ንቃት፣ተነሳሽነት ለሌላቸው
68;ለድምፅ መታፈን
69;ከአጫሽነት ለመላቀቅ
70;ራስን ስቶ በስቃይ ለሚኖር
0908104860 ይደውሉልን
3.9K views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ