Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ezmerejaet
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4
የሰርጥ መግለጫ

እንዴት አደርሽ ኢትዮጵያዬ ! 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-10-12 17:50:07
የአፈና ዜና

የአማራ ህዝባዊ ኃይል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥላሁን አበጀ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መታፈኑ ተገለፀ!

የአማራ ህዝባዊ ኃይል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጥላሁን አበጀ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መታፈኑን ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ ገልጿል።
ከአማራ ህዝብ የሕልውና ጥያቄ ይልቅ የእኛ በሰላም ወጥቶ መግባት እረፍት የሚነሳው የብአዴን ስብስብ ወንድማችን ጥላሁን አበጀ ን በዛሬው እለት አሳፍኖታል ሲል ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ በፌስቡክ ገፁ አጋርቷል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.8K views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 13:30:26
በአርባ ምንጭ ከተማ የሚኖሩ  የትግራይ ተወላጆች  አሸባሪ ህወሓት  የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ

አርባምንጭ ከተማ የሚኖሩ  የትግራይ ተወላጆች አሸባሪ ህወሓት  የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ  አካሄዱ።

ሰለፈኞቹ አሸባሪ ህወሓት  የትግራይ ህዝብን  አይወክልም ፣ የትግራይ ሕዝብ የለውጡ ተካፋይ ሊሆን ይገባል፣ በኢትዮጵያዊነቴ የማልደራደር ኩሩ ትግራዋይ ነኝ የሚሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@sheger_press
@sheger_press
1.8K views10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 11:53:47
"አማራነትን በጎጥ ተቧድኖ እየገዘገዙ፣ እንደ አማራ የሚመዘገብ ድል የለም" - ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ

የወልቃይት አማራ ሁሌም ትግል ላይ ነው። በአንድ እጁ ጠመንጃ፣ በሌላ እጁ ቀንበር ጨብጦ ነው የከረመው። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የዚህን አርበኛ ህዝብ ሰብል እንዳይሰበሰብ ዘመቻ መክፈት ትልቅ ሀጢያት ነው። ከወያኔ ጦርነትም ተለይቶ አይታይም። በአርበኛ ዘመነ ካሴ መታሰር የሚደሰቱ አማሮችም እንዲሁ የአማራ ጠላቶች ናቸው። አማራነትን በጎጥ ተቧድኖ እየገዘገዙ፣ እንደ አንድ አማራ የሚመዘገብ ድል የለም።

(ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ - ከሱዳን ተነስቶ ጥቃት የፈፀመውን ወራሪ ሀይል የወገን ሀይል ድል በማድረጉ የተደሰቱ ሆመራ ከተማ ነዋሪዎች ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተናገረው)

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
3.0K views08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 07:02:33
በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ እየተከናወነ የሚገኘውን የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ብሔራዊ ፈተና ተከትሎ በዛሬው እለት ግጭት እንደተከሰተ እና ጉዳት እንደደረሰ ማህበራዊ ሚድያ ላይ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል።

በስፍራው ካሉ ተማሪዎች እና የህክምና ባለሙያዎች ማምሻውን ያገኘሁት መረጃ እንደሚጠቁመው "ፈተናው በሌሎች የፈተና ጣብያዎች ተሰርቋል፣ ስለዚህ አንፈተንም" ያሉ ተማሪዎች ጠዋት ላይ ግቢውን ለቀው ወጥተዋል።

በዚህ ወቅት 4 ሰአት አካባቢ በተማሪዎች እና የፀጥታ አካላት መካከል በተከሰተ ግጭት አንድ ተማሪ ህይወቱን ያጣ ሲሆን ሌሎች ጥቂት ተማሪዎች እና የፀጥታ አካላት ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይህን ዶክተሮችም አረጋግጠውልኛል።

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ "ካልተኮራረጅን አንፈተንም፣ የፈተና አሰጣጥ ሥርዓቱን አናከብርም" ባሉ ሥነ-ምግባር በጎደላቸው ተማሪዎች የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ መስተጓጎሉን ገልጿል። ህይወቱን ስላጣው ተማሪ ያለው ነገርም የለም።

*በእንዲህ አይነት ወቅት ትክክለኛ መረጃ በተገቢው ፍጥነት ለህዝብ አለማድረስ ይባስ ሴራ ትንተናን ያስከትላል፣ ስለዚህ ይታሰብበት።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.2K views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 20:26:16
አቶ ጌታቸው ረዳ የድሮን ሰለባ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ምንጮች አመለከቱ።የመረጃው ምንጮች እንደተናገሩት ከሆነ ህውሃት አቶ ጌታቸውን አንስቻለሁ የሚለው ትናንት ምሽት መቀሌ ከተማ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ሠለባ መሆኑን ተከትሎ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።አቶ ጌታቸው በሚዲያ ከቀርቡ ቀናት ተቆጥረዋል።ማጣራቱ ይቀጥላል

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
6.5K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 19:49:11 ሽሬ

የሽሬ ምሽጎች ተደረመሱ...

የሽብር ቡድኑ የሽሬ ግንባር ምሽጎች ድርምስምሳቸው ወጣ! በመቀሌ ዙሪያ እየገነባ ያለውም ይደረመሳል! ወያኔ ራሱ በለኮሰው ጦርነት ያሉትን ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ እያጣ ነው። በተለይም በርካታ ልማት የሚሰራበትን  ጊዜውን፣ ገንዘቡን (የግብፅ ብር ቢሆንም) እና ጉልበቱን (የትግራይ ወጣት ተገድዶ የሰራው ቢሆንም) በመጠቀም በሽሬ/እንዳስላሴ ከተማ በዙሮች አጥሮ የሰራቸው ምሽጎች፤  በጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን በሚመራው ጥምር ጦር ስብርብራቸው መውጣቱን ምንጮች ገልፀዋል።

አንዳንዶቹ ምሽጎች እስከ 20 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው መሆናቸውንም ነግረውናል። በሌላ በኩልም፤ ከእነዚህ ምሽጎቹ ዶግ አመድ መሆን ያልተማረው ጁንታው፤ በመቀሌ ከተማ ዙሪያ የኮንክሪት ምሽጎችን በፍጥነት እየገነባ መሆኑን እነዚሁ ምንጮች ገልፀዋል። ሆኖም፤ ጀግኖቻችን በሽሬ ግንባር ሰርቶት በነበራቸው ምሽጎች ውስጥ እንደቀበሩት ሁሉ፤በመቀሌውም የኮንክሪት ምሽጎቹ ውስጥ መልሰው ይቀብሩታል። ያኔም የጁንታው መጨረሻ ይሆናል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
6.7K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 17:13:54
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለትን የመኪና ሽልማት ተረከበ

በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በ10 ሺሕ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለትን መኪና ዛሬ ተረክቧል።

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ ብቸኛው የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቱን ተከትሎ ከመንግስት የመኪና ሽልማት እንደተበረከተለት ይታወሳል።

ሽልማቱ በተለያየ ምክንያት ለሰለሞን እንዳልተሰጠው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን የመኪና ሽልማቱን ተረክቧል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
6.9K views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 17:10:20
መረጃ

ጌታቸው ረዳ በከባድ የጨጓራ ህመም (Chronic Constipation) እና የአንጀት መዘጋት (Intestinal blockage) ምክንያት ስራውን ለመስራት እንዳገደው ህወሃት አስታወቀ። ጌታቸው ረዳ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የህወሓት ቃል አቀባይ እንደነበር ይታወቃል፣ ሆኖም ዶክተሩ በዚህ ሁኔታ ስልጣን ላይ መቀጠል አይችልም ሲል ገልጿል። ማደናገሪያ ይሆን

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
6.7K views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 12:41:59 በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ዲግሪ በመሸጥ ላይ ተብሎ በአዲስማለዳ ጋዜጣ ለተሰራዉ ዘገባ ተቋሙ ይቅርታ ጠየቀ

አዲስ ማለዳ በቅጽ 4 ቁጥር 203 መስከረም 14/2015 እትሟ ‹በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪ በ20 ሺሕ ብር እየተሸጠ መሆኑ ተነገረ።› በሚል ርዕስ የፊት ገጽ ዜና ይዛ መውጣቱ ይታወሳል።

አዲስ ማለዳ ባወጣዉ ሰፊ ማብራሪያ ፤ ይህንን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲው በዜናው ላይ ቅሬታ እንዳለው ለጋዜጣዋ ዝግጅት ክፍል አሳውቋል ብሏል። ቅሬታው በዋናነት ‹ዜናው ሚዛናዊ አይደለም› የሚል ነበር። አዲስ ማለዳ ዘገባውን ሚዛናዊ ለማድረግ ተቋሙ በድረ-ገፁ ላይ ባስቀመጠው ስልኮች ላይ በተደጋጋሚ በመደወል የሚመለከታቸውን የሥራ ኃላፊዎች ለማነጋገር ጥረት አድርገናል ብሏል።

ነገር ግን ይህ ሙከራ እንዳልተሳካ በዜናው ላይ ገልጸናል ብሏል። በማብራሪያዉ ፤ ምንም እንኳን ዜናውን ለአንባብያን ለማድረስ በሚታወቅ የሚዲያ አሠራር ምክንያት የጊዜ እጥረት የነበረብን ቢሆንም፣ የተቋሙን አመራሮች ለማግኘት ተጨማሪ ጊዜ ወስደን በጉዳዩ ላያ ያላቸውን አስተያየት ማካተት ተገቢ እንደነበር እናምናለን ፤ ይህን ሳናደርግ ዜናውን ለአንባቢያን በማቅረባችን ዩኒቨርሲቲውንም፣ አንባቢያንንም ይቅርታ እንጠይቃለን ሲል አዲስማለዳ ጋዜጣ አስታውቋል።

በተጨማሪም፣ ጉዳዩ በዜናው ርዕስ ላይ እንደተገለጸው ዩኒቨርሲቲው አውቆ፣ ተቋሙ በዘረጋው ሥርዓት በኩል እውቅና ተሰጥቶት ትምርህታቸውን በተቋሙ የትምህርት ክፍሎች ውስጥ ገብተው ላልተማሩ ሰዎች 20 ሺሕ ብር ስለከፈሉ ብቻ ዲግሪ እየተሰጣቸው እንደሆነ የሚመስል አንድምታ ዜናው እንደፈጠረ ተረድተናል ያለ ሲሆን ነገር ግን በምርመራችን እንዳረጋገጥነው ይህ ስህተት ነው ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው ይፋዊ በሆነ መንገድ ሳያውቀውና እውቅና ሳይሰጠው በተቋሙ ሥም የሚዘጋጁ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን አንዳንድ ሰዎች 20 ሺሕ ብር በመክፈል እያሠሩ መሆኑን አዲስ ማለዳ በምርመራዋ አረጋግጣለች። የዜናችን ርዕስ ከዘገባው መሠረታዊ ጭብጥ በወጣ መልኩ ዩኒቨርሲቲው በ20 ሺሕ ብር ዲግሪ እየሸጠ እንደሆነ አንድምታ በሚፈጥር መልኩ መሠራቱ ስህተት ነዉ ብሏል።  አዲስማለዳ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣዉ ማብራሪያ ዩኒቨርሲቲውንም ሆነ አንባቢያንንም ይቅርታ እንጠይቃለን ብሏል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
6.6K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 12:26:50
አሸባሪው ህወሓት በቆቦ ከተማ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መግደሉን ዘጋርዲያን የዓይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ዘገበ

አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ዳግም ወረራ በፈጸመበት ወቅት በቆቦ እና አካባቢዋ በርካታ ንጹሃን ዜጎችን መግደሉን የዓይን እማኞችን ጠቅሶ ዘጋርዲያን የተሰኘው የእንግሊዙ ጋዜጣ አጋልጧል።

በሽብር ቡድኑ አማካኝነት መሳሪያ ባልታጠቁ 17 ንጹሃን ላይ ግድያ የተፈጸመው ከቆቦ ከተማ ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ ላይ መሆኑንም የዓይን እማኞቹ ለዘጋርዲያን ገልጸዋል።

አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል በቆቦ ከተማ ዳግም ወረራ በፈጸመበት ወቅት ይቃወሙኛል ብሎ ያሰባቸውን በርካታ ንጹሃን ዜጎችን መግደሉን የዜና ምንጩ ዘግቧል።

በነሃሴ ወር አሸባሪው ቡድኑ በቆቦ ከተማ ወረራ ባካሄደበት ወቅት በንጹሃን ዜጎች ላይ የግድያ ወንጀል ብቻም ሳይሆን የንብረት ላይ ዘረፋ መፈጸሙንም ነዋሪዎች ለዘጋርዲያን ተናግረዋል።

በአሸባሪ ቡድኑ የተፈጸመው የንጹሃን ግድያ ቤት ለቤት በተካሄደ አሰሳ  ጭምር እንደሆነ ሰባት የዓይን ምስክሮችን ጠቅሶ ዘጋርዲያ በዘገባው አስነብቧል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
6.1K viewsedited  09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ