Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ezmerejaet
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4
የሰርጥ መግለጫ

እንዴት አደርሽ ኢትዮጵያዬ ! 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2022-10-10 09:32:07 መረጃ

አሸባሪው ሕወሃት በሰሜን ትግራይ ከትናንት ማለዳ ጀምሮ "የተቀናጀ ወታደራዊ ጥቃት ተከፍቶብኛል" በማለት ከሷል።

ህወሃት በኤርትራ አዋሳኝ በሆኑት ራማ፣ ዛላንበሳ እና ጾረና በተባሉ ግንባሮች ነው ብሏል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
6.0K views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 09:28:46
የሀዋሳ ዩንቨርስቲ ዋናውን ግቢ ከቴክኖ ግቢ የሚያገናኘዉ ድልድይ ተደርምሶ ተማሪዎች ላይ አደጋ መድረሱን ተመልክተናል!

ጉዳቱ ምን ያህል እንደሆነ ባይታውቅም ፣ የተጎዱ ተማሪዎች ወደ ሀዋሳ ረፈራል ሆስፒታል እና ወደ ተለያዩ የህክምና ተቋማት ለእርዳታ እየተወሰዱ እንደሚገኙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
6.0K views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 07:18:36
መረጃ

ጁንታው ያኔ ደብቋቸው የነበረው የመከላከያ ሃብታችን መልሶ እጃችኝ እየገባ ነው!!

ጁንታው በስምንት ወራቱ የትግራይ ህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ደብቆት የነበረውና በድንቆቹ የኢትዮጵያ መከላከያ መሃንዲሶች እንዳይጠቀምበት ተደርገው የነበሩት ሚሳኤሎች፣ ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሮኬቶች፣ የራዳር መቆጣጠሪያዎች፣ ከባባድ የጦር መኪኖች፣ ታንኮች፣ መድፎች፣ ለመቁጠር ሳይሆን ለማየት የሚታክቱ የልዩ ልዩ መሳሪያዎች ተተኳሾች ተይዘዋል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
6.5K views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 20:18:02 በዛሬው የአዲስ ነገር መረጃ የተንቀሳቃሽ ምስል መረጃዎቻችን

የምክር ቤቱ አባል ለምን ታፈኑ ማንስ ናቸው ?
መከላከያ በአክሱም እና አዲግራት ዙሪያ ምን አጋጠመው ?
ስለ ድርድሩስ ምን አዲስ?

ሌሎችንም ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኝት ከታች ሊንኩን ተጠቀሙ







7.1K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 19:39:23
ጀግናው የኢትዮጵያ ጥምር ጦር በሽሬ ግንባር ህወሓት ይተማመንበት የነበረውን ምሽግ እየደረመሰ ወደፊት በመገስገስ ላይ ነው።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
7.2K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 08:53:35
በፌደራል መንግስት እና ህወሓት መካከል ሊካሄድ የነበረው ድርድር በሎጅስቲክስ ምክንያት ተራዘመ

በፌደራል መንግስት እና ህወሓት መካከል የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ የነበረው ድርድር በሎጅስቲክስ ምክንያት መራዘሙ ተገልጿል።

የአፍሪካ ሕብረት የሰሜን ኢትዮጵን ለማስቆም የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሆነ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት
የፌደራል መንግስት እና ህወሓትን በደቡብ አፍሪካ እንዲደራደሩ ለሁለቱም ወገኖች ጥሪ አቅርቦ ነበር።

ሕብረቱ ያቀረበውን ጥሪ ኹለቱም ወገኖች መቀበላቸውን እና በድርድሩ ላይ በሰየሟቸው ተደራዳሪዎች በኩል እንደሚሳተፉ መግለፃቸው ይታወሳል።

በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት የሚካሄደው ይህ ድርድር ነገ እና ከነገ በስቲያ እንዲካሄድ ፕሮግራም ተይዞለት የነበረ ቢሆንም፤ ይህ ድርድር ወደ ሌላ ጊዜ መተላለፉን የሮይተርስ ዜና ምንጭ የዲፕሎማሲ ምንጮቼ ነግረውኛል ሲል ዘግቧል።

በዘገባው ድርድሩ ወደ መቼ እንደተራዘመ ያልተገለጸ ሲሆን፤ የአፍሪካ ሕብረት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህወሓት ስለ ድርድሩ መራዘም እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
3.0K views05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 08:09:48
ሰበር

በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የአየር ቀጠና ለወታደራዊ የስለላ ስራ የኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሶ ለመግባት ሙከራ ያደረገ ሰው አልባ ድሮን በጀግናው የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዘመናዊ የአየር መቃወሚያ ተመቶ በእሳት እየነደደ ወደ ምድር ተከስክሷል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
3.3K views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 21:17:54
ከልጃቸው ጋር የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱት አዛውንት

አቶ አበራ ቦራ ይባላሉ። የስምንት ልጆች አባት ናቸው። ከጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ ነው የመጡት።

በ65 ዓመታቸው ከመጨረሻ ልጃቸው ጋር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተዋል።

"መምህር የመሆን የልጅነት ህልሜን ለማሳካት በቂ ዝግጅት አድርጌ ለፈተን ቀሪቤያለው" ሲሉ ይናገራሉ።

አዛውንቱ በቤተሰብ ኃላፊነት የተነሳ ለረጅም ጊዜ ያቋረጡትን ትምህርት በ2009 ዓ.ም ካቋረጡበት በመቀጠል ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመፈተን መድረሳቸውን ገልጸዋል።

የአዛውንቱ የመጨረሻ ልጅ ተማሪ ሳሙኤል አበራ በበኩሉ አባቴ “እድሜህ ገፍቷል ትምህርት ምን ይሰራልሃል“ የሚለውን ትችት ሳይቀበል ከእኛ ጋር እኩል በመማር እዚህ መድረስ መቻሉ ለበርካቶች ትምህርት ነው ሲል ለኢዜአ ተናግሯል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
2.6K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 20:58:49
ማሳሳቢያ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች!

ተፈታኞቻችን ወደ መፈተኛ ማዕከላት ገብተዋል፡፡ የተከለከሉ ነገሮችን ማንም ተፈታኝ ይዞ እንዳይገባ ከወረዳ ጀምሮ ገለጻ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም አካላዊ ፍተሻ ተደረጓል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተለያየ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም የተከለከሉ ነገሮችን በተለይም ተንቀሳቃሽ ስልክን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡ ድርጊቱ ከፍተኛ የፈተና ደንብ ጥሰት በመሆኑ ውሳኔው ከሁሉም ፈተና የሚሰረዙ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ከዚህ በኃላም የተከለከሉ ነገሮችን መፈተኛ ማዕከላት (የኒቨርሲቲ) ግቢ ውስጥ ማንኛውም ተፈታኝ ይዞ ቢገኝ ከሁሉም ፈተና የሚሰረዝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ገለጻውን ባለመቀበልና አካላዊ ፍተሻዎችን በማጭበርበር ስለፈጸመው ጉዳይ ተጨማሪ ህጋዊ ምርመራ የሚካሄድ ሲሆን እንደግኝቱም ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል፡፡

ፈተና የሁሉም ማህበረሰብ ሀብት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለፈተና ደህንነትና ፍትኃዊነት የበኩሉን አዎንታዊ ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
2.9K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 20:37:06
የወልዲያ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት የስዓት እላፊ ገደቦች ላይ ማሻሻያ አደረገ!

መስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር

የወልዲያ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት የከተማዋን አሁናዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ በጣላቸው የስዓት እላፊ ገደቦች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

የከተማዋ የፀጥታ ምክር ቤት ከዛሬ መስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ አስቀምጧቸው በነበሩ የስዓት እላፊ ገደቦች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

በዚህም መሰረት:-

1 የከተማዋን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ለእግረኛ ተቀምጦ የነበረውንየ 1 ስአት የስአት እለፊ ገደብ 2 ስአት በማድረግ ማሻሻያ አድርጓል።

2 ለተሽከርካሪ ተቀምጦ ሲተገበር የነበረውን 2 ስአት የስአት እላፊ ገደብ 3 ስአት በማድረግ ጥሏቸው በነበሩ የስአት እላፊ ገደቦች ላይ ማሻሻያ ማሻሻያ ማድረጉን የከተማዋ የፀጥታ ምክር ቤት አስታውቋል።

ማሳሰቢያ:- ከዚህ በፊት የከተማዋን ወቅታዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ በከተማዋ የፀጥታ ምክር ቤት የተቀመጡ ክልከላዎች ባሉበት የሚቀጥሉ ይሆናል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት

መስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም.

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
3.2K views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ