Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ezmerejaet
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4
የሰርጥ መግለጫ

እንዴት አደርሽ ኢትዮጵያዬ ! 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2022-10-11 11:21:38 በኦሮሚያ ክልል የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ተጀመረ
****

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከ1-4 በሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የምገባ ፕሮግራም ዛሬ ተጀምሯል።

ከክልሉ ዘንድሮ በሁሉም የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 7.5 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመገብ ታቅዶ እየተሰራ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ በሁሉም ከ1-4 በሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የምገባ ፕሮግራም ተጀምሯል።

ብቃት ያለውን ዜጋ እንዲኖር የሕፃናት እድገት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።

ለምገባ ፕሮግራሙ ስኬታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡን ከኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.9K views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 10:48:58 ራያ
እርቀው ሸሽተው ነበር ግን አሁን ተመልሰው እየመጡ ነው ፤ ብዛትም አላቸው ። የአተር ፣ የምስር ፣ የገብስና የበቆሎ ሰብል እየሰበሰብን ነው ። ማሳው ላይ እንዳናቆየው እየበሉ ጨረሱት ፤ ሰብስበን ስንከምር  እንዳይቃጠልባችሁ እያሉ ያስፈራሩናል ፤ በቀን መውቃት አንችልም ይወስዱታል ፤ በሌሊት ስንወቃም ለምንድነው በቀን መውቃት የማትችሉት እያሉ ይደበድቡናል ።
እንሰሳቶችንም አርደው ጨረሷቸው ፤ ይህ ብቻ አይደለም ወጣቶችንም እያፈኗቸው ነው ፤ የት እንደሚዎስዷቸው ግን አናቅም ፤  የጨነቀ ነገር ነው ያገኘነው !! በስቃይና በመከራ ውስጥ ነው ያለነው !!  አሁንም በህወሓት ቁጥጥር ስር ያሉ የራያ ቆቦ ቀበሌ አርሶ አደሮች የተናገሩት ነው።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.9K views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 08:07:48
"በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለተፈታኞች ፍተሻ ሲደረግ የነበረው ብዙ ተማሪዎች ድልድዩ ላይ እንዲሰለፉ እና እንዲቆሙ ተደርገው ነው።" - የአይን እማኞች

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ኢንትራስ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ከዋናው ግቢ ወደ ቴክኖ ኢንስቲትዩት ግቢ የሚያሻግረው ድልድይ ላይ እንዳሉ ነበር ፍተሻ ሲደረግላቸው የነበረው። ተማሪዎቹን ሌላ ቦታ ላይ ፈትሸው ማሻገር ሲገባቸው ድልድዩ ላይ አስቁመው መፈተሻቸው ነው ከአይን እማኞች የተሰማው።

"ዩኒቨርስቲው ከሚገባው በላይ ተማሪዎች ድልድዩ ላይ ስለወጡ አደጋ መድረሱን እንደ ምክንያት መግለፁ ተገቢ አይደለም የዩኒቨርስቲው ህንፃ አስተዳደር አካላት ድልድዩ የሚችለዉን የጭነት መጠን ከግምት በማስገባት የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰድ ነበረባቸዉ" ሲሉ በአከባቢው የነበሩ የአይን እማኞች እና የተማሪ ወላጆች ገልፀዋል።

በአደጋው የተደናገጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማው ህዝብ፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች በሀዋሳ መንገዶች ላይ ሁኔታውን በጭንቀት እና ሀዘን ውስጥ ሆነው ሲከታተሉ ውለዋል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
6.3K views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 22:07:53
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው የድልድይ መሰበር አደጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የ258 ተማሪዎች ስም ዝርዝር።

በደረሰው አሳዛኝ አደጋ የተሰማንን ሀዘን እንገልፃለን

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
3.1K views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 21:01:27 ታሪካዊ ጠላት ስንል በመረጃ ነው

የግብፅ የመረጃ ተቋም ህወሓት ጦርነቱን እንዲገፋበትና ሦስተኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት እንዲያስተጓጉል 2 ሚልዮን ዶላር እንዳበረከተለትና በየ 45 ቀኑም 500 ሺ ዶላር ድጋፍ ሲያደርግለት እንደቆየ  ምስጢራዊ ሰነዶች አጋለጡ

የግብፅ ጠቅላላ የመረጃ አገልግልት (General Intelligence Service- GIS) ህወሓት ጦርነቱን እንዲገፋበት እንዲሁም የህዳሴ ግድቡ 3ኛው ዙር የውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት  የተለያዩ የሀገር ውስጥ ታጣቂ ኃይሎችን ስምሪት በመስጠት ሂደቱ እንዲስተጓጎል ከሀገሪቱ መንግሥት ተልዕኮ ተሰጥቶት ሲንቀሳቀስ እንደነበር ምስጢራዊ ሰነዶች አጋልጠዋል፡፡

የግብፅ ጠቅላላ የመረጃ አገልግልት (General Intelligence Service- GIS) ቦርድ ኃላፊ ብ/ጀነራል ሙታዝ ሙስጠፋ እና የአፍሪካ ላይዘን ኃላፊ ብ/ጀነራል ሙስጠፋ ማርዋን 2 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር በዲፕሎማሲያዊ  ሂደት ወደ ሱዳን ካስገቡ በኋላ በካርቱም ለሚገኙ የሽብር ቡድኑ ተወካዮች ማስረከባቸውን የሚያጋልጡ የሰነድ ማስረጃዎች የተገኙ ሲሆን፤ ህወሓት ጦርነቱን እንዲገፋበትና በኢትዮጵያ አለመረጋጋቱ እንዲቀጥል  በየ45 ቀኑ 500 ሺ የአሜሪካ ድላር ድጋፍ ሲደረግለት እንደነበረም ተረጋግጧል፡፡

ሱዳን እና ግብፅ ህወሓትን በመጠቀም የኢትዮጵያን ማዕከላዊ መንግሥትና አጠቃላይ ፖለቲካዊ ሁኔታውን  ለመቀየር ያላቸውን ፍላጎት ለማሳካት  ለአሸባሪ ቡድኑ የፋይናንስ፣ የሎጀስቲክ፣ የስልጠናና ሌሎችም የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በተለይም ግብፅ የሽብር ቡድኑ የመንግሥት ለውጥ ማምጣት ባይቻል እንኳን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎችን በማቀናጀት የህዳሴ ድግቡን የ3ኛው ዙር የውሃ ሙሌት እንዲያስተጓጉል ከፍተኛ ተስፋ አድርጋ የነበረ ሲሆን፤ የትግራይ ክልል ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮችም የገንዘብ ድጋፍ ከተደረገላቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ እንደሚያከናውኑ ተስማምተው እንደነበር ታውቋል፡

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.1K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 20:55:58
ትምህርት ሚኒስቴር የመጀመሪያው ቀን የ12ኛ ክፍል ፈተና ተጠናቆ ተማሪዎች ለቀጣዩ ቀን ፈተና እየተዘጋጁ መሆኑን አሳውቋል።

በዛሬዉ እለት የተጀመረዉ 12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዕለት ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የገለፀው ሚኒስቴሩ " ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከተፈጠረዉ አሳዛኝ ክስተት እና በመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ፈተና ሳይፈተኑ ከወጡ ተማሪዎች ሪፖርት ዉጪ አጠቃላይ ሂደቱ የተሳካ ነበር " ብሏል።

ፈተናው በመላው ሀገሪቱ ካሉት 130 የፈተና ጣቢያዎች በ128ቱ ጣቢያዎች ላይ ነበር ሲሰጥ የዋለው።

ትምህርት ሚኒስቴር የዛሬውን ፈተና ያጠናቀቁ ተማሪዎች በነገዉ እለት ለሚኖራቸዉ ፈተና ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጿል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.0K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 20:24:07 በዛሬው የአዲስ ነገር መረጃ የተንቀሳቃሽ ምስል መረጃዎቻችን

የራያ ቆቦ የብልፅግና አመራር ተገደለ እንዴት ?

የስለላ ድሮን ተመታ የት አካባቢ ይሆን?

ጥምር ጦሩ መቀሌን ለመያዝ የመንግስትን ውሳኔ እየተጠባበቀ ነው በየትኛው አቅጣጫ?

ሙሉ መረጃውን ይመልከቱ






4.5K views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 14:47:01
ህወሓት ሁሉም የትግራይ ተወላጆች እንዲዘምቱ አዲስ ጥሪ አቀረበ!!

በህውሀት ልሳን በሆነው በድምፀ ወያኔ ሚድያ ባስተላለፈው መልዕክት ሁሉም የክልሉ ተወላጆች ወደ ጦር ግንባር እንዲዘምቱ ትናንት እሁድ መስከረም 29/2015 ዓ.ም. አዲስ ጥሪ አቅርቧል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.7K views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 13:37:11
#Update

" እስካሁን ባለው የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ፤ ሁለት ከባድ ጉዳት እና ሌሎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና ላይ ይገኛሉ " - የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

ዛሬ ጠዋት የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናውን ግቢ እና የቴክኖሎጂ ካምፓስ ግቢን የሚያገኛኘው ድልድይ ተደርምሶ በደረሰው ጉዳት እስካሁን ባለው የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ እና ሁለት ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ይህን የገለፀው የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ነው።

የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሰጡት ቃል ፤ " እስከአሁን ባለው ሂደት በጉዳቱ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ፣ ሁለት ከባድ ጉዳት እና ሌሎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል " ብለዋል።

እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲከሰቱ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆችና ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ከሚመለከተው አካል ብቻ በማግኘት እንዲያረጋግጡና እንዲረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.8K views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 13:09:25
ለንፁሀን የአማራ ተወላጆች ሞት የኦሮሚያ እና የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ተጠያቂ ናቸው ሲል ባልደራስ አስታወቀ!

ላለፉት አራት ዓመታት በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ላለው “ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት” የብልፅግና ፓርቲ ተጠያቂ ነው ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ገለፀ።ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ “ከዚህ በፊት ሲከናወኑ እንደቆዩት ተግባራት ሁሉ በዚህ ሰሞንም ኦነግ ሸኔ በምስራቅ ሸዋ በመተሀራ አባድር 2ኛ ካምፕ 12 ወጣችን የገደለ ሲሆን፣ የአስራ አንዱ የግድያ ሰለባዎች ትላንት በአዲስ ዓለም መድኃኒያለም ቤተ ክርስቲያን የቀብር ስርዓታቸው በጅምላ ተፈፅሟል፡፡ ይህ የሚያሳየው የብልፅግና ኦህዴድ መንግስት በጨፍጫፊነቱና በጦረኛነቱ አማራን የማፅዳት ተግባሩ ከፍተኛ መሆኑን ማሳያ ነው” ብሏል።

ባልደራስ በመግለጫው ትኩረት ይደረግባቸው ያላቸው ነጥቦችም “በአማራ ተወላጆች ላይ ለዓመታት በተፈፀሙት የዘር ማጥፋት እና ማፅዳት ወንጀሎች የኦህዴድ/ ብልፅግና አመራሮች (ከላይ እስከ ታች) ያሉት ተጠያቂ እንደሚሆኑ እንዲረዱ፣ ብአዴን/የአማራ ብልፅግና በአማራ ተወላጆች ላይ ለሚፈፀመው የዘር ማጥፋት እና ማፅዳት ወንጀል በዝመታዉ ተባባሪ በመሆኑ በህግ ፊት ተጠያቂ እንደሚሆን እንዲገነዘብ” ብሏል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.5K views10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ