Get Mystery Box with random crypto!

ራያ እርቀው ሸሽተው ነበር ግን አሁን ተመልሰው እየመጡ ነው ፤ ብዛትም አላቸው ። የአተር ፣ የም | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

ራያ
እርቀው ሸሽተው ነበር ግን አሁን ተመልሰው እየመጡ ነው ፤ ብዛትም አላቸው ። የአተር ፣ የምስር ፣ የገብስና የበቆሎ ሰብል እየሰበሰብን ነው ። ማሳው ላይ እንዳናቆየው እየበሉ ጨረሱት ፤ ሰብስበን ስንከምር  እንዳይቃጠልባችሁ እያሉ ያስፈራሩናል ፤ በቀን መውቃት አንችልም ይወስዱታል ፤ በሌሊት ስንወቃም ለምንድነው በቀን መውቃት የማትችሉት እያሉ ይደበድቡናል ።
እንሰሳቶችንም አርደው ጨረሷቸው ፤ ይህ ብቻ አይደለም ወጣቶችንም እያፈኗቸው ነው ፤ የት እንደሚዎስዷቸው ግን አናቅም ፤  የጨነቀ ነገር ነው ያገኘነው !! በስቃይና በመከራ ውስጥ ነው ያለነው !!  አሁንም በህወሓት ቁጥጥር ስር ያሉ የራያ ቆቦ ቀበሌ አርሶ አደሮች የተናገሩት ነው።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet