Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ezmerejaet
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4
የሰርጥ መግለጫ

እንዴት አደርሽ ኢትዮጵያዬ ! 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-11-07 13:56:21
ዘመነ ካሴ ለህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጠው!

ባለፍው ሳምንት አዲስ ክስ የተመሰረተበት ዘመነ ካሴ ለህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጠው።ዘመነ ካሴ ከዚህ በፊት በተከሰሰበት ወንጀል የባህር ዳር እና አካባቢው ፍርድ ቤት በነፃ ማሰናበቱ ይታወሳል። ነገር ግን “በከባድ የሰው መግድል መንጀል” የተከሰሰው ዘመነ ካሴ ዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም በባህር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቧል።ፍርድ ቤቱም የ15 ቀን የጊዜ ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱ ተጠናቋል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
2.9K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 11:48:48
ትኩረት - አምቦ ከተማ

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ቡድን ታጣቂዎች በነቀምቴ ከተማ ዙሪያ አድፍጦ  ከተማዋን ለመቆጣጠር ጥረት ባደረገበት መንገድ አምቦንም ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ያረጋግጣሉ።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.0K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 23:20:11
በድሀ የትግራይ ልጆች ደም የተጨማለቁ ደናቁርት በህዝቡ ስም ትግራይ ትዕስር እያሉ ዶላር መሰብሰብ አይቻልም ጉዳዩ በስምንት ተዘግቷል ተቋጭቷል።
እኔ አለሁ እዋጋለሁ የሚል ካለ ግን አሜሪካና አውሮፓ ቁጭ ብሎ ሳይሆን ጦርነቱን ማየት ያለበት በአካል ትግራይ መሬት ላይ ተገኝቶ መዋጋት ይቻላል አሜሪካ በርገር እየበሉ ግን ተዋጉልን የሚለው ፉከራና ቀረርቶ ግን አይሰራም
1.1K views20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 23:15:51
ጥቆማ

በቅርብ ጊዜ ትልቅ ተወዳጅነትን ያተረፈዉ እና ብዙ ተከታዮችን ያገኘው እንዲሁም “ወደ ቀድሞ ከፍታችን እንመለሳለን” በሚል  የሚዲያ ሽፋን ላልተዳረሰባቸዉ ድምፅ ለመሆን  የሸዋ ዜና አገልግሎት ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ #join        https://t.me/+0j24gRc38Gg2OGVk
1.1K views20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 20:29:19
አንጋፋው አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ጥቅምት 27/2015 (ዋልታ) አንጋፋው አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን አስታወቀ።

አርቲስት አሊ ቢራ ባጋጠመው የጤና እክል ምክንያት በአዳማ ጄነራል ሆስፒታል ለሳምንታት የሕክምና ክትትል ሲደረግለት መቆየቱ ታውቋል።

አርቲስቱ በ72 አመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ሲሆን በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ ከ50 ኣመታት በላይ አገልግሏል፡፡

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
3.2K views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 14:14:11
ጠ/ሚ አብይ አህመድ ግብፀ ሻርም አልሸይክ ገቡ ።

የመንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ግብፅ፣ ሻርም አል-ሼይክ ገብተዋል።
fbc

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.3K viewsedited  11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 09:00:22
ግልፅ ደብዳቤ ለፕ/ር መረራ እና ለC2FC ኮሚቴዎች

     ጉዳዩ፡-ለሰላም ጎዳናው ትብብራችሁን ስለመጠየቅ፣

በፕሪቶሪያ ህወሃት ትጥቄን ለሰላም እፈታለሁ ማለቱን ተከትሎ ኦፌኮ፣ ከኦሮሚያው ጨፍጫፊ ቡድን ጋርም ገዢው መንግስት የሰላም ስምምነት እንዲያደርግ በመግለጫ ጠይቋል።
ከኦፌኮ በተጨማሪ እንግሊዝ ውስጥ ተማክሎ በዬሃገሩ ህዋሳት በነበረው C2FC የተባለ ህቡዕ ፀረ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ስር ሉዓላዊነታችንን በፍርፋሪ የለወጡ ወገኖቻችንም ከኦፌኮ መግለጫ በተመሳሳይ ሲናገሩ ተስተውለዋል።
ኦፌኮ የአብይ መንግስት በኦሮሚያው ገዳይ ቡድን ላይ የድሮን ጥቃቱን አቁሞ ይደራደረው ማለቱ በክፉ የሚታይ አይደለም።
የሰላም ጥሪው ከውጤት እንዲደርስ ኦፌኮ  ሼኔ የሚገኝበትን በነካ እጁ ቢያመላክት መልካም ነው ስል እንደ ዜጋ ጥሪየን በግልፅ ደብዳቤ አድርሻለሁ።
ሠላም ለኢትዮጵያችን ለሁሉም የሰው ልጆች
   (#የዓባይልጅ)

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
2.5K viewsedited  06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 08:47:12 ከእኛ ጋር መስራት የምትፈልጉ ከ 20000 ሺህ በላይ ተከታይ ያላችሁ እንደዚሁም ጥሩ እይታ ያላችሁ የዜና ቻናል ባለቤቶች @abelo_neww ላይ አናግሩን
2.3K views05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 21:48:40 " ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖበት ያለመከሰስ መብታቸዉ ከተነሳ በኋላ መሆን ይገባዋል " - ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ

በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምሥራቅ ምድብ ችሎት የወንጀል ችሎት ዳኛ የሆኑት ፦
1ኛ ዳኛ ደሳለኝ ለሚ፣
2ኛ ዳኛ ሙሀመድ ጅማ
3ኛ ዳኛ አብዲሳ ዋቅጅራ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሚሠሩበት ፍርድ ቤት በአዳማ ከተማ ኦሮሚያ ፖሊስ ተወስደው ታስረዋል።

ይህን ተከትሎ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እስራቱ ፈጽሞ ሕገወጥ እና በዳኝነት ነጻነት ላይ የተፈጸመ ጥቃት በመሆኑ በአስቸኳይ ከእስር ሊለቀቁና ድርጊቱ ተጣርቶ ተገቢው እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

ኢሰመኮ ስለጉዳዩ ባደረገው ማጣራት ዳኞቹ በሕግ የተሰጣቸው ልዩ ጥበቃ መብት በሕጋዊ መንገድ ሳይነሳ እና ዳኞች መሆናቸው ሳይገለጽ ከወረዳ ፍርድ ቤት ተሰጥቷል በተባለ የእስር ትእዛዝ ከሥራ ገበታቸው ላይ ተነስተው የታሰሩ መሆኑን ገልጿል። የእስር ትእዛዙን የሰጠው የወረዳ ፍርድ ቤት ታሳሪዎቹ ዳኞች መሆናቸውን እንደተረዳ የእስር ትእዛዙን የሻረ መሆኑን አሳውቋል፡፡

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ ዳኞቹ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አጥብቀው አሳስበዋል። ትላንት አርብ ኢሰመኮ እስሩን በተመለከተ መግለጫ እስካወጣበት አመሻሽ ድረስ ዳኞቹ በእስር ላይ ነበሩ ፤ ዛሬም ስለመፈታታቸው የተባለ ነገር የለም።

ዛሬ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዜዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ የዳኞቹ መታሰር " በጣም አሳሳቢ ነው " ብለዋል።

" በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት ሥስት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በአዳማ ከተማ መታሠራቸው በጣም አሳሳቢ ነው " ያሉት ወ/ሮ መአዛ ፥ " ዳኞች የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ " ብለዋል።

ወ/ሮ መአዛ ፤ ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖበት ያለመከሰስ መብታቸዉ ከተነሳ በኋላ መሆን እንደሚገባው አስገንዝበው " ስለተከሰተዉ ሁኔታ የበለጠ ለመረዳት እየሞከርን ነዉ። " ሲሉ ገልፀዋል።

" ከዚህ ቀደም እንደዚህ ያሉ ተመሳሳይ ድርጊቶች በአንዳንድ ክልሎች በዳኞች ላይ ሲፈጸሙ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የክልል ፍርድ ቤቶች ፕሌነም አውግዘው ውሳኔ አስተላልፈው ነበር ። " ሲሉ ወ/ሮ መአዛ አስታውሰዋል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
1.8K views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 21:20:10
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መንግስት ከህወሓት ጋር ያደረገውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ የሁለት ወራት የግንባር ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮአቸው ተመለሱ።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከውጊያ ኮማንድ ፖስት ወደ መደበኛ ማዘዣ ቢሮአቸው ከተመለሱ በኋላም በመንግስት እና በህወሓት በተደረገው ስምምነት መሠረት በጥቂት ቀናት ወስጥ ከህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም
2.4K views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ