Get Mystery Box with random crypto!

' ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖበት ያለመከሰስ መብታቸዉ ከተነሳ በኋላ መሆን ይገባዋል | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

" ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖበት ያለመከሰስ መብታቸዉ ከተነሳ በኋላ መሆን ይገባዋል " - ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ

በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምሥራቅ ምድብ ችሎት የወንጀል ችሎት ዳኛ የሆኑት ፦
1ኛ ዳኛ ደሳለኝ ለሚ፣
2ኛ ዳኛ ሙሀመድ ጅማ
3ኛ ዳኛ አብዲሳ ዋቅጅራ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሚሠሩበት ፍርድ ቤት በአዳማ ከተማ ኦሮሚያ ፖሊስ ተወስደው ታስረዋል።

ይህን ተከትሎ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እስራቱ ፈጽሞ ሕገወጥ እና በዳኝነት ነጻነት ላይ የተፈጸመ ጥቃት በመሆኑ በአስቸኳይ ከእስር ሊለቀቁና ድርጊቱ ተጣርቶ ተገቢው እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

ኢሰመኮ ስለጉዳዩ ባደረገው ማጣራት ዳኞቹ በሕግ የተሰጣቸው ልዩ ጥበቃ መብት በሕጋዊ መንገድ ሳይነሳ እና ዳኞች መሆናቸው ሳይገለጽ ከወረዳ ፍርድ ቤት ተሰጥቷል በተባለ የእስር ትእዛዝ ከሥራ ገበታቸው ላይ ተነስተው የታሰሩ መሆኑን ገልጿል። የእስር ትእዛዙን የሰጠው የወረዳ ፍርድ ቤት ታሳሪዎቹ ዳኞች መሆናቸውን እንደተረዳ የእስር ትእዛዙን የሻረ መሆኑን አሳውቋል፡፡

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ ዳኞቹ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አጥብቀው አሳስበዋል። ትላንት አርብ ኢሰመኮ እስሩን በተመለከተ መግለጫ እስካወጣበት አመሻሽ ድረስ ዳኞቹ በእስር ላይ ነበሩ ፤ ዛሬም ስለመፈታታቸው የተባለ ነገር የለም።

ዛሬ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዜዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ የዳኞቹ መታሰር " በጣም አሳሳቢ ነው " ብለዋል።

" በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት ሥስት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በአዳማ ከተማ መታሠራቸው በጣም አሳሳቢ ነው " ያሉት ወ/ሮ መአዛ ፥ " ዳኞች የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ " ብለዋል።

ወ/ሮ መአዛ ፤ ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖበት ያለመከሰስ መብታቸዉ ከተነሳ በኋላ መሆን እንደሚገባው አስገንዝበው " ስለተከሰተዉ ሁኔታ የበለጠ ለመረዳት እየሞከርን ነዉ። " ሲሉ ገልፀዋል።

" ከዚህ ቀደም እንደዚህ ያሉ ተመሳሳይ ድርጊቶች በአንዳንድ ክልሎች በዳኞች ላይ ሲፈጸሙ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የክልል ፍርድ ቤቶች ፕሌነም አውግዘው ውሳኔ አስተላልፈው ነበር ። " ሲሉ ወ/ሮ መአዛ አስታውሰዋል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet