Get Mystery Box with random crypto!

በኢንዶኔዥያ 46 የተለያዩ ሴቶች ጋር ትዳር የመሰረተዉ ግለሰብ ለ88ኛ ጊዜ ሊሞሸር ነዉ በኢንዶኔ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

በኢንዶኔዥያ 46 የተለያዩ ሴቶች ጋር ትዳር የመሰረተዉ ግለሰብ ለ88ኛ ጊዜ ሊሞሸር ነዉ

በኢንዶኔዥያ በምእራብ ጃቫ ነዋሪ የሆነዉ ካን የሩዝ ገበሬ ሲሆን አስገራሚ የህይወት ታሪክ አለው።የ61 ዓመቱ ሰዉ በህይወት ዘመኑ ነበአጠቃላይ 87 ጊዜ ያገባ ሲሆን ለ88ኛ ጊዜ ከቀድሞ ሚስቶቹ መካከል ከአንዷ ጋር በድጋሚ ለመሞሸር በዝግጅት ላይ መሆኑ ተነግሯል። ካን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያገባ በ14 ዓመቱ የነበረ ሲሆን በሁለት አመት ከምትበልጠው ልጃገረድ ጋር በወቅቱ ትዳር ይመሰርታል፡፡

ትዳራቸው ለ 2 ዓመታት ብቻ የቆየ ሲሆን በወቅቱ ታዳጊዉ ፍቺ እንደፈጸመ አዲስ ሚስት ከመፈለግ አላገደውም፡፡ለምንድን ነው የሚወዳቸውን ሴቶች ሁሉ ማግባቱን የቀጠለው በሚል ለካአን ለቀረበዉ ጥያቄ ሲመልስ ስለማከብራቸው ነው ብሏል።ለአንድ ሳምንት ብቻ የቆየ ትዳሩን ጨምሮ ለ87 ጊዜ ያህል ሲሞሸር 40 ያህሉ ህጋዊ በሆነ መንገድ ተፈራርሞ አግብቷል፡፡

87 ጊዜ ጋብቻ ቢፈጽምም 46 ሴቶችን ብቻ አግብቷል፡፡ይህ ሊሆን የቻለዉ ደግሞ አንዳንዶቹን ሶስት እና አራት ጊዜ በድጋሚ በማግባቱ የተነሳ ነዉ፡፡ካን ከቀድሞ ሚስቱ ጋር ለ88ኛ ጊዜ ጋብቻ ሊመሰርት መሆኑን ተከትሎ እንደተናገረዉ “ከተለያየን ረጅም ጊዜ ቢያልፈውም በመካከላችን ያለው ፍቅር አሁንም ጠንካራ ነው” ብሏል፡፡ የቀድሞ ትዳራቸው የፈጀው ለ 4 ወራት ብቻ እንደሆነ ተናግሯል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet