Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Students Books(Grade 9-12 )

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 ) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 )
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_students_only
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 282
የሰርጥ መግለጫ

በቻናላችን የሚገኙ ጠቃሚ ነገሮች
✅ entrance exam
✅extreme book & referance book
✅Textbook ( 9-12 )
✅Teachers Guide (9-12)
✅worksheet ( 9-12)
✅students info እና ለሎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
@Ethio_Students_only
For comment @EthioStudentsOnly_bot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-13 13:23:47 እንመረቅ እንጂ አንፈተንም አላልንም

የ ደብረማርቆስ  ዩኒቨርሲቲ  ተማሪ ነኝ እኛ እንመርቅ እንጂ አንፈተንም አላልንም ሳይማሩ ያስተማሩን ቤተሰቦቻችን ልጄ ሊመርቅ ነው እያሉ ሳልመርቅ ብቀር ምንድነው የሚሰማቸው ብቻ ከባድ ነው ፡፡ለቤተሰቦቻችን እንኳን ስትሉ አስመርቁን

  ፍትህ ለ ተመራቂ ተማሪዎች!!!ትግላችን ይቀጥላል!!!!
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
1.9K viewsE, 10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 11:14:22
#Update

የሬሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰኔ 05/2015 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ የተላከ ደብዳቤ እንደሚያሳየው፤ የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የተቀበሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎችን ዝርዝር፣ ፈተናውን የሚወስዱበት ካምፓስ ማዕከልና የከተማ ሙሉ አድራሻ እንዲሁም በማዕከል የተዘጋጀውን ፈተና የሚረክብ የተቋም ኃላፊ ወይም ባለቤት መረጃ እስከ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም ድረስ ለትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን እና በትምህርት ሚኒስቴር ለአካዳሚክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ መላክ እንዳለባቸው ደብዳቤው ያመለክታል፡፡

(የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ከላይ ይመልከቱ፡፡)
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
2.1K viewsE, 08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 21:51:12
በእንዳንድ የመገናኛ ብዙሃንና የማሕበራዊ ሚድያዎች መቐለ ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 12/2015 ዓ ም ተማሪዎቹን እንደሚቀበል እየተነገረ የሚገኘው መረጃ ትክክለኛ #አለመሆኑን እና እስካሁንም መቐለ ዩንቨርሲቲ የሰጠው ኦፊሽያል መግለጫ አለመኖሩን ዩንቨርሲቲው ዛሬ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
2.1K viewsE, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 20:02:09 #መመረቅአለባቸው

በእውነቱ ከዚህ አድስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ጋር በጣም ቅራኔ አለኝ። ምክንያቱም እንያንዳንዱ የሚወጡት ውሳኔዎች ተማሪዎች እና ቤተሰቦችን ተስፋ ቢስ የሚያደርጉ ናቸው።

ከነዚህም ውስጥ
1. Exit exam
2. በቀጣይ አመት የስራ ቅጥር አለመኖር
3. Exit exam የወደቁ አለመመረቅ

ይህን ስል exit exam አያስፈልግም ወይም መቅረት አለበት እያልኩ አደለም ነገር ግን የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ግዜ ወሳጅ ከመሆናቸው ባሻገር ሲማሩ የነበሩት በድሮው የትምህርት ፍኖተ ካርታ ነው። ይህ ማለት exit exam በሌለው ነበር። በመሆኑ በጣም ብዙ ጫና ያሳድራል ይባስ ብሎ ካላለፉ #አይመረቁም የሚለው ሀሳብ በጣም አስፈሪና አንገብጋቢ ነው።

ይህ በራሱ ኮንፊደስ ያሳጣል እናም ትምህርት ሚንስተር እንዲሁም የሚመለከተው አካል ሁሉ ለምሳሌ ወመህ  ይህን ነገር አስቸኳይ ማስተካከያ ቢሰጠው ለሀገራችንም ለሰላማችንም ጠቃሚ ነው ።

.... እኔ ባለፈው አመት ነው የጨረስኩት ግን በዚህ ሰአት ተመራቂ ብሆን ብየ ሳስብ በጣም ውስጤ ይጎዳል ...እውነት ለመናገር መማር ኪሳራ የሆነባት ሀገር ላይ ነው የምንማረው ምክንያቱም እንዲህ ሁነን ተምረን ራሱ በአግባቡ ቅጥር የለም ቢኖርም በሰውና በገንዘብ ሆኗል። ብቻ ተስፋ ላስቆርጣችሁ አደለም ግን ወታችሁ ብዙ እንዳትጠብቁ እየነገርኳችሁ ነው እንጅ ...።

መንግስት መውደቅ ሲፈልግ ገበሬና ተማሪ ጋር ይጣላል ይላሉ ያለፉ አባቶቻችን እና ትኩረት ትኩረት  ለተማሪዎች...አመሰግናለሁ
   
መልካሙ ሁሉ ለናንተ ይሁን!
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
2.2K viewsE, 17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 21:09:17 መመረቅ እንፈልጋለን

ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው አዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት Exit Exam በዚህ አመት ይጀምራል ።

ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ/ግንቦት 23/ ባወጣው መግለጫ መሰረት Exit Exam ያላለፈ ተማሪ #አይመረቅም ማለቱ ተማሪዎችን አስቆጥቷል።

እስካሁን ተማሪዎች ያላቸው መረጃ Exit Exam አለፉም ፣ አላለፉም እንደሚመረቁና የደስታቸውን ቀን ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደሚያሳልፉ ነው።

ሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች በጊዜያቸው መመረቅ አለባቸው። የመውጫ ፈተናውን የወደቁ ተማሪዎች Document ተከልክለው ድጋሚ መፈተን እንጂ አትመረቅም ማለት ለህሊና እንኳን ይከብዳል ።

ቤተሰብ ልጄ ይመረቃል ብሎ እየጠበቀ አትመረቅም ማለት አይከብድም???

ለተመራቂ ተማሪዎች ድምፅ እንሆናለን። እናንተም ሀሳባችሁን በቦት አድርሱን
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
793 viewsE, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 19:05:36
የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰኔ 03/2015 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ ለ4 የዩኒቨርስቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እድገት ሰጥቷል።

በዚሁም መሰረት ፦

1ኛ. ዶ/ር ጌታቸው ዓለማየሁ ዳሞት ከግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ በአግሮኖሚ የሙሉ ፕሮፌሰርነት

2ኛ. ዶ/ር ንጉስ ጋብዬ ሀብቱ ከባሕርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ሙሉ ፕሮፊሰርነት

3ኛ. ዶ/ር መላኩ ዋለ ፈረደ ከሳይንስ ኮሌጅ በኢንቶሞሎጂ ሙሉ ፕሮፌሰርነት

4ኛ. ዶ/ር ፀጋዬ ካሳ ጎጂ ከሳይንስ ኮሌጅ በሥነ-ህዋ ሳይንስ ሙሉ ፕሮፌሰርነት እድገት ማግኘታቸውን ዩኒቨርሲቲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

አንጋፋው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት 60ኛ ዓመት የብርኢዮቤልዩ በዓሉን በማክበር ላይ ይገኛል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
1.2K views Elshio owner, 16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 18:12:07 ቤተሰብ  EUEE  english Part ውስጥ  የሚገኘው እና  ብዙ  ጊዜ  የሚወስደው  passage  በቀላሉ  የምትሰሩበትን መንገድ  እጠቁማቹሀለው  ከናንተ  የሚጠበቀው  join,Like,Share,Comment  በማድረግ  ማበረታታት  ነው።
ፈተናውን  ለመስራት  directly  Reding  የምትገቡ ከሆነ  ትልቅ  ችግር  አለው።ችግሮቹም  timeing(ሰአት)forget  ደጋግሞ  የማንበብ  እና የመርሳት  ችግር  ስለሚያጋጥም  ቀድማቹህ  ልትዘጋጁ  ይገባል።
#Step 1 :Skimming:Read  The  Surface  of  the  Text.
አሁን  ለምሳሌ  3 Passage   ቢኖረን የpassagን  ሁሉ  ክፍል ማንበብ  አይጠበቅብንም።የመጀመሪያ  የመጀመሪያ  sentenceኑን   በደንብ  አድርጎ   ማንበብ።ጥቅሙ  የPassagን  አንዳንድ  ነገር  እንድናውቅ  ያደርገናል።
#Step  2:  Read  The  Questions
Passage  በምታነቡበት  ሰአት  ከጥያቄው  ጋር  እያዛመዳቹህ  በቀላሉ  መስራት  ያስችሏቹሀል።
#ሁለት  ነገር  እስኪ  እንመልከት
1.ጥያቄዎቹን  መረዳት  ያስፈልጋል።ይህም  ማለት እኛ  የፈጠረን  ብለን  የምናምነው  ፈጣሪ  ነው።በሳይንስ  ደግሞ  የሰው  ልጅ  የመጣው ከዝንጀሮ  ነው  ይላል።ስለዚህ መልሱን  በምትመርጡበት  ጊዜ  በContext እና  በደንብ  በመረዳት  መስራት  ትችላላቹህ።
2.እያንዳንዱ  ጥያቄዎች  ላይ  Key  Word  መያዝ።ለምሳሌ፦በ1995 ምን  ተካሄደ  የሚል  ጥያቄ  ቢኖር  እንደ  Key  Word  የምትጠቀሙት በ1995  የሚለውን  ነው ማለት  ነው።
Step  3:Scanning:reading  to  find  Specific  Key  Words.
የምትፈልጉትን  Part እስክታገኙ  ድረስ ቶሎ  ቶሎ  እያላቹህ  መፈለግ  ማለት  ነው።
ከPersonal  Believe  መመለስ  የለባቹህም።መመለስ ያለባቹህ ከPassage  ጋር  የተገናኘውን  ነው።ለዚህ  ጥሩ ምሳሌ  እኛ  ፈጣሪ ፈጠረን  ብለን  ነው  የምናምነው ሳይንስ ደግሞ  የሰውን  ልጅ  ከዝንጀሮ  ነው  የመጣው  ይለናል  ስለዚህ  ጥያቄውን  በመረዳት  ትክክለኛውን  መልስ  ማስቀመጥ  ይጠበቅብናል  ቤተሰብ።
በPassage  ወቅት  Vocabulary  ሊጠየቅ ይችላል።እነሱም  SYNONYM(ተመሳሳይ)ANTONYM(ተቃራኒ) ናቸው።በተቻላቹህ  መጠን  ከአራቱ  ምርጫዎች  ሁለቱን  ለመቀነስ  ሞክሩ።ከሁለቱ  replice  እያረጋቹህ ከpharagraph  ውስጥ እየከተታቹህ  ትርጉም  የሚሰጠውን   መስራት  ትችላላቹህ።
ለአስተማሪ  እና  ጠቃሚ  መረጃዎች  ቻናሉን join,share,comment  በማድረግ  ያበረታቱን።
መልካም  የዝግጅት  ጊዜ
join our   main  channel

@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
1.1K viewsE, 15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 18:11:34 ፓስዋርድ ሲጠፋን ኮምፒውተራችንን እንዴት መክፈት እንችላለን?

አይበለውና የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴው ቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ… አንድ መላ አይጠፋም፡፡

የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ሲሆን ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡

Step1: መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን

Step2: ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡፡

Step3: ፍላሹ ን ሰክተን ኮመፒዩተሩን Turn ON ማድረግ፣ ከዛF12 (Boot key) መንካት፡፡

Step4: “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለዉን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል፡፡

Step5: ኮምፒዩተሩ ከከፈተ በኃላ “Spotmou Bootsuite 2012 Application” ይከፈትልናል፡፡

Step6: ከአፕልኬሽኑ ላይ “Password and Key Finder” የሚለዉን “Menu” እንመርጣለን፡፡

Step7: “Admin Password Resetter” የሚል መንካት፡፡

Step8: “Please select the target widows” ከሚለዉ ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/10)” ይመርጣሉ፡፡ ቀጥሎ “please select the target user” ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን “User Account” መርጠዉ “Reset” የሚለዉን መጫን፣ ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለዉን እንጫናለን፡፡

Step9: መጨረሻ ላይ “Password is reset successfully” የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡፡

Step10: ኮምፒዩተሩን ዘግተዉ ይክፈቱት (Reboot). በትክክል ይሰራል…
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
792 views Elshio owner, 15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 18:06:51 ◈ለ12ኛ እንዲሁም ለ Remedial ሼር አድርጉ◈

ENGLISH EXAM አሰራር !

COMPRESSION QUESTIONS (10-20Questions )

English Exam ላይ ሁለት እና ከዛ በላይ  Passage  ይሰጠናል፥

Passage እንዴት በፍጥነት አንበበን እንረዳ።አንዳንዶች ሙሉን passage በማንበብ ጊዜያቸውን ይገላሉ ፤ አንዳንዶች ደግሞ ጥያቄውን አይተው passage ውሰጥ መልስ ለማግኘት ይንከራተታሉ፤ አነኚህ ሁለቱም የጊዜ ፀር ናቸው።ይልቁንስ Experts የሚጠቁሙን ነገር አለ ፤በመጀመሪያ ንባባችሁ

INTRODUCTION (The fist paragraph of a passage) and CONCLUSION( The Last paragraph of a passage)፣እነኚ part በሙሉ ትኩረት አንድም ሳይቀር ይነበብ ! Cause Ye will able to answer the ff concepts

What does the writer want to inform you ?(in conclusion )

Definition about the subject of the passage (not sentence!).(In introduction)

Argue for and argue against Ideas of the writer.

ከ Introduction እና Conclusion መኻል ያሉትን paragraph ሙሉውን ማንበብ አይጠበቅባችሁ።ከእያንዳንዱ paragraph አንድ sentence በማንበብ ስለምን እንደሚያወራ ተረዱ አለቀ።ከዛን ወደ ጥያቄ ስትገቡ What is the main idea of  Paragraph 3?ቢላችሁ ያቺን Para መርጣችሁ ለብቻ ማንበብ ተመራጭ ነው!



Word and paragraph Coherence (10 Questions)

ከ 1-5  ጥያቄ Word order ይመጣል።እነኚን ቃላቶች ለማወቀር Order of Some parts of speech ማወቅ ያስፈልጋል ?

lemisale አንድ sentence bizu type of adjectives ቢኖረው Order of adjective ማወቅ ግድ ነው

Order of adjectives quantity, opinion, size, age, color,shape, origin, material and purpose

Adverbs ቢሆን ?እንዴት ነው order ምታረጉት?

Order of adverbs : manner, place (location), frequency, time, reason/purpose.

Paragraph Coherence

ከ a-e ሰጥቶ Sentence order enditaregu ስትጠየቁ ማረግ ያለባችሁ ተግባራት

topic sentence (ሃይለ ቃል) - የፓራግራፉ ዋና ሃሳብ የያዘውን ቃል ፈልጉ ፤ እርግጠኛ ሆናችሁ አንድ ቃል ካገኛችሁ እሰየው ፤ ምናልባት ሁለት sentence እንደዛ ከያዛችሁ ጥሩ

ሌላኛው ሚስጢር እዚጋ ነው ፤ ሁለት ተደጋጋፊ ቃላት ፈልጉ እና እነሱን ይዛችሁ ምርጫችሁ ውስጥ ፈልጉ! ከአራቱ በአንዱ ምርጫ ላይ እነኚ ሁለት አረፍተ ነገሮች መሃል አልያም ዳር ላይ ሆነው ታገኛኋላችሁ ፤ የጠረጠራችሁት Topic sentence እራሱ ከቸች ይላል።መልሳችሁ ተገኘ ማለት አደል!


Grammar (25-35 Questions )

English Grammar በአጭር ጊዜ ውስጥ Cover ለማረግ ከተገኘ Advaced English world wide Book1&2 ተጠቀሙ።ቢያንስ ባታነቡ እንኳን Review Exercise ድብን አርጉና ስሩ!Advanced ካላገኛችሁ ደግሞ English Text Book ላይ በአረንጓዴ Colour Box ውስጥ ያሉትን Shortnotes አንብቧቸው!

VOCABULARY (5-10Questions )

Vocabulary part ላይ አይተን የማናውቀው ቃል ዱብዳ ቢያጋጥመን ምን እናረጋለን GUESS ልንሞላ? ኸረ በጭራሽ GUESSማ አንሞላም! መልሱን ማግኘትን የምንችልበት ሌላ ዘዴ እያለ!

Vocabulary ጥያቄ በዳሽ ሙላ መልክ ነው የሚሰጠን። መልሱን ለማግኘት መጀመሪያ ጥያቄውን አንበብበው ትርጉሙን አውቃችሁ ከመለሳቹ።በጣም ጥሩ ግን ።አራቱም ቃላቶች የማታውቋቸው ቢሆኑስ ....?ሚስጥሩ እዚጋ ይገለጣል!

ዳሽ ሙላው ያለበት አረፋተ ነገር ላይ (Yet,hardly ,seldom ,never ,n't )ሚሉ ቃላቶች ካሉ ምርጫው ላይ Negative ቃላቶች ሚገቡበት ሁኔታ rare ነው።So Choose the positive ones!

ሌላኛው ነገር (Phrasal verbs and Idioms ከ (4-6) ጥያቄ ይመጣሉ እዚሁ Vocabulary part lay so .

English Text book lay ...ከጀርባ Apendix on Phrasal verbs list በደምብ ማየት ይኖርባችኋል!

Lists of Idoms ደግሞ እኔ PDF ልክላችኋለሁ!


Communication (20-30Questions )

English Subject ላይ ካሉት የፈተና Portion ይችኛዋ ምርጥዬ ናት!ነገር ግን አንዳንድ አሳሳች ጥያቄዎች አይጠፉም!እነሱን የምንመልስበት ልዩ ዘዴ ምንድነው?

Communication ላይ ምንም መጣጠር የለባችሁም! ጥያቄ ከሆነ የተጠየቀው ፤ የመረጣችኋት መልስ አጠረች ብላችሁ አትጠርጥሩ !

Writing Usually 20 Questions)

ይሄን ለመመለስ መነበብ ያለባቸው Topics

በ20 ደቂቃ የምትረዷ ንባብ ነች 20 ጥያቄ ታተርፋለች

Types of essay
     i.Narative ii descriptive iii argumentative & i.v Expository

letter &memo
Punctuation

ምክሩ፤ በእርግጠኝነት ይጠቅማችኋል ብዬ አስባለሁ ።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
824 viewsE, 15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 15:28:07 ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤

ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።

አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።

ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።

በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር::

ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤

በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።

ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።

በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።

መጭው ወቅት የፈተና ወቅት ነውና ለተፈታኞች በሙሉ መልካም ፈተና ተመኘን

"ለሁሉም ተማሪ share ይደረግ "
#Share #Join_us
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
1.0K views Elshio owner, 12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ