Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Students Books(Grade 9-12 )

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 ) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 )
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_students_only
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 282
የሰርጥ መግለጫ

በቻናላችን የሚገኙ ጠቃሚ ነገሮች
✅ entrance exam
✅extreme book & referance book
✅Textbook ( 9-12 )
✅Teachers Guide (9-12)
✅worksheet ( 9-12)
✅students info እና ለሎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
@Ethio_Students_only
For comment @EthioStudentsOnly_bot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-30 18:42:58 Inclusiveness power point.

 ━━━━━━━━━━━━━━━━━
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.6K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, edited  15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:41:17 @Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.6K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:36:37 ይሄ መልዕክት ለ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች አድርሱልኝ ። ያላችሁ በጣም ትንሽ ጊዜ ነው ።2 ወር ነው ያላችሁ ። በንባብ ውስጥ ያላችሁ እንድትበረቱ : የተዘናጋችሁ ደሞ በዚህች በቀረች አጭር ጊዜ ዉስጥ አቅም የፈቀደውን ሁሉ ማድረግ መቻል አለባችሁ ። በተለይ በተለይ ሁላችሁም ተፈታኞች ከንባቡ ጎን ለጎን ጥያቄ መስራት እንዳይረሳ ። ያለፉ አመታት entrance ፈተናዎችን በደንብ ደግማችሁ ደጋግማችሁ መስራት መቻል አለባችሁ።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
2.1K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:26:16 #NationalExam

" ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን አይፈተንም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን ነው የተገለፀው።

የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የተጠቀሰ ሲሆን ተማሪዎች የምዝገባ ሂደቱን ለማካሄድ በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ይካሄዳል።

የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ሲሆን ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን እንደማይፈተን አገልግሎቱ አሳውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ለምዝገባ ምን ያስፈልጋል / ተማሪዎች ምን ማሟላት አለባቸው ?

- መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ9 - 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም  በመማር ላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

- የማታ እና የርቀት ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ሶስት ሴሚስተር እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል የሁለት ሴሚስተር የትምህርት ማስረጃ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

- ድጋሜ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም የተፈተኑበትን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ መመዝገብ አለባቸው።

- ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ፈተናው መቼ እና የት ይሰጣል ?

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም  ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
2.0K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, edited  16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:24:13
#Tigray

ከዓመታት በኃላ በትግራይ ያሉ #ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ምዝገበ እየተካሄደ ይገኛል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ  ለዓመታት በኮቪድ-19 እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር ከሚያዚያ 18 ጀምሮ ምዝገባ እንደሚከናወን እና ሚያዚያ 23 ትምህርት እንደሚጀመር ማሳወቁ የሚዘነጋ አይደለም።

ተማሪዎች ያለፋቸውን ጊዜ ለማካካስ በሳምንት 3 የትምህርት ፕሮግራሞች የነበሩትን ወደ 5 እና 6 በመቀየር አንድ ሴሚስተር የሚጨርሰውን ጊዜ ለማሳጠር እንደሚሰራ መነገሩም ይታወሳል።

በትግራይ ጦርነት ምክንያት ክፉኛ ከተጎዱት መካከል #ተማሪዎች ዋነኛዎቹ ሲሆኑ ተማሪዎች ለበርካታ ወራት ከትምህርት ርቀው ይገኛሉ።

እንደ ህፃናት አድን ድርጅት (Save the Children) መረጃ በትግራይ 2.3 ሚሊዮን ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.5K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:22:43 የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  ባለፉት ዘጠኝ ወራት 85 ሺህ ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት አቅዶ ማከናወን የቻለው 66 በመቶ ብቻ ነው ብሏል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ስድስት ሚሊዮን ዜጎች በስራ ፈላጊነት መመዘገባቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን የገለጸው ትላንት ሐሙስ ሚያዝያ 19፤ 2015 የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው። የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፤ በስራ እድል ፈጠራ፣ በቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና እንዲሁም በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ላይ መስሪያ ቤታቸው ያከናወናቸውን ስራዎች ለፓርላማው አብራርተዋል።

የሚኒስትሯን ሪፖርት ተከትሎ ጥያቄዎችን ከሰነዘሩ የፓርላማ አባላት አንዱ የሆኑት አቶ ዮሃንስ መስፍን፤ “የውጭ ሀገር የስራ አማራጮችን ተጠቅሞ ለዜጎች ብቁ ስራ ዕድል ለመፍጠር ምን ታስቧል?” የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታው አቶ አሰግድ ጌታቸው ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ ከውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ጋር በተያያዘ የመዳረሻ ሀገራትን ለማበራከት ጥናት መጀመሩን ተናግረዋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.3K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:21:10
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሚያስተምሩ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ለአራት ቀን የሚቆይ ውይይት በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

ውይይቱ በዛሬው እለት በ77 ክላስተሮች 63,470 መምህራን እና የትምህርት አመራሮችን ተሳታፊ በማድረግ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በዛሬው እለት ውይይቱን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸው በውይይቱ 1,368 ቡድኖች ከመደራጀታቸው ባሻገር 2,736 አወያዮች መመደባቸውን አስታውቀዋል።

ውይይቱ በዋናነት ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት ያስመዘገበቻቸውን ውጤቶችና በሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መሰረት በማድረግ የሚካሄድ መሆኑን ዶክተር ዘላለም ገልጸው ለትምህርት ልማት ስራው ውጤታማነት መምህራንም ሆኑ የትምህርት አመራሮች የአንበሳውን ድርሻ እንደመውሰዳቸው  የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የተማሪዎችን ውጤት እና ስነምግባር ለማሻሻል ውይይቱ የጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት መሆኑንም አስረድተዋል።

ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን በክላስተር ደረጃ ተካሂዶ እሁድ እለት ከየትምህርት ቤቱ ከተውጣጡ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች  ጋር በየክፍለከተማው ተመሳሳይ ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር እሁድ 500 የሚሆኑ መምህራን በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ ታላላቅ የልማት ስራዎችን የሚጎበኙበት መርሀ ግብር መዘጋጀቱን ኃላፊው ጠቁመው ሰኞ ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም በከተማ ደረጃ የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት 5,000 ከሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.3K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, edited  16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:21:01
#ማሳሰቢያ

ለሁሉም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት !
በ2015 ዓ.ም ከሁሉም የከፍተኛ  ትምህርት ተቋማት   ለሚመረቁ  ተማሪዎች የመውጫ  ፈተና  (Exit Exam )  የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመራቂ ተማሪዎቻችሁን  መረጃ  በተላከላችሁ  የመረጃ መላኪያ  ቅጽ መሠረት  እስከ ሚያዚያ  26  ቀን 2015 ዓ.ም ለኢፊዲሪ ትምህርትና  ስልጠና  ባለሥልጣን እንድታቀርቡ እያሳሰብን እስከ ተጠቀሰው ቀን መረጃውን የማያቀርብ ተቋም ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡


የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.5K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, edited  16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 17:54:55
#Update

" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና  ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን  አብራርተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 ዓ.ም የሚካሄደው ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸው የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
3.3K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 16:49:05
Bahirdar University.

Civics and Moral Education.

2013 Mid Exam.
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
2.3K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ