Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Students Books(Grade 9-12 )

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 ) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 )
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_students_only
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 282
የሰርጥ መግለጫ

በቻናላችን የሚገኙ ጠቃሚ ነገሮች
✅ entrance exam
✅extreme book & referance book
✅Textbook ( 9-12 )
✅Teachers Guide (9-12)
✅worksheet ( 9-12)
✅students info እና ለሎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
@Ethio_Students_only
For comment @EthioStudentsOnly_bot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-06 19:25:33
የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ከሃያ ሺህ ጫማ ከፍታ በላይ መጓዝ የሚችል ሮኬት አስወነጨፈ።


የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ "አፄ ቴዎድሮስ 2015" የሚል ስያሜ የተሰጣትን ሮኬት ከሃያ ሺህ ጫማ ከፍታ በላይ አስወንጭፎ ስኬታማ ሙከራ ማድረግ ችሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በህዋ ምርምር ላይ ትኩረት በማድረግ ጋፋት የህዋ ምህንድስና ልማት ማዕከልንም አቋቁሞ የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

የማዕከሉ መሥራችና ሰብሳቢ አቶ በለጠ ጌታቸው፣ ሮኬት የማስወንጨፉ ሙከራ ከዚህ በፊት ከተሞከሩት የተሻለ ምርምር የተደረገበትና ለህዋ ሳይንስ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ተሸክሞ መሄድ የሚያስችል ቴክኖሎጅ የተገጠመለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው ያሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው በዩኒቨርሲቲው ተማሪና ተመራማሪዎች የተሠራው ሥራ ኢትዮጵያ እንደሰለጠኑት ሀገራት በህዋ ምርምር የበኩሏን ድርሻ እንደምትይዝ ጅምሩን ያሳየ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ ከሚካሄዱት የህዋ ሳይንስ ምርምሮች ውስጥ በሮኬት ሳይንስ ዘርፍ ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የአማራ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሉ አያሌው (ዶ.ር) እንደዚህ አይነት ሙከራዎች ኢትዮጵያ ወደፊት በዘርፉ ለምታደርገው ምርምር አጋዥ ናቸው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

(ኢ ፕ ድ)
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
3.3K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 16:36:26
ከመጪው ግንቦት አንድ ጀምሮ የድረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ክፍያ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ የክፍያ ስርዓቶች እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

ዘመናዊ የክፍያ ስርዓቱ በቴሌ ብር፣ሲቢኢ ብር እንዲሁም በሞባይል ባንኪንግ አማራጮች በኩል የሚተገበር ሲሆን ደንበኞች ይህንን በመገንዘብ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያቸውን በወቅቱ እንዲያከናውኑ አገልግሎቱ አሳስቧል።

በአገልግሎቱ የደንበኞች አገልግሎት ሽያጭና ቅሬታ ሰሚ ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት ስምረት በለጠ ለኢዜአ እንደገለጹት የድረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ወርሃዊ የክፍያ ስርዓትን ለማዘመን ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ስትራቴጂካዊ ትግበራ መጀመሩን አስታውሰዋል።

በዚህም፤ላለፉት ሁለት ዓመታት 72 በመቶ የሚሆኑ የድረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ወደ ዘመናዊ የክፍያ ስርዓት መቀላቀላቸውን ጠቅሰው አሁን የቀሩት 28 በመቶ የሚሆኑ ተጠቃሚዎች ወደ ስርዓቱ የሚካተቱ ይሆናል ብለዋል።

በመላ አዲስ አበባ 30 የድረ-ክፍያ አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት መኖራቸውን ጠቅሰው በመጪው የግንቦት ወር 21 የሚሆኑት የድረ-ክፍያ ማዕከላት ሙሉ በሙሉ በቀጥታ ወደ ዘመናዊ ስርዓት ይገባሉ ብለዋል።

እንደ ስራ አስኪያጇ ማብራሪያ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የሚገኙ ዘጠኝ የድረ-ክፍያ አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት ለግንቦት ወር ብቻ የቢል የአከፋፈል ስርዓትን የሚሰጡ ይሆናሉ።

የክፍያ ስርዓቱን በዘመናዊ የአከፋፈል ስርዓቶች ማደረጉ ደንበኞች ከዚህ ቀደም በክፍያ ማዕከላት ሲያጋጥማቸው የነበሩ መጉላላቶችን ከማስቀረቱ ባሻገር ፈጣን እና ተደራሽ የሚሆን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል
 @Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
3.1K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 20:31:25
በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና (Exit Exam) የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ የላኩ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር፡-
-------------------------------------------------


1. ሐይላንድ ኮሌጅ
2. አሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ቴክኖሎጂ
3. ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ
4. ፕሪሚየም ኮሌጅ
5. አንድነት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ
6. ያኔት ኮሌጅ
7. ኢትዮጵያ ካቶሊክ ከፍተኛ የትምህርት
8. ካኔኑስ ኮሌጅ
9. አክሞንሊንክ ኮሌጅ
10. መካነየሱስ ማኔጅመንትና ሊደርሺፕኮሌጅ
11. ሳታ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ
12. ሉናር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ
13. ብሉ ናይል ኮሌጅ
14. ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ
15. ፋሆባ ኮሌጅ
16.  ባምባ ኮሌጅ
17.  አዲስ አምባ ኮሌጅ
18.  ባቢት  ቢዝነስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
19. ግዮን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ እና
20. ጮቄ ፋና ኮሌጅ ናቸው፡፡
21. ድሪም ላንድ ኮሌጅ                        
22. ቤቴል ሜዲካል ኮሌጅ
23. ላልዛግ ኮሌጅ
24. ጉዛራ ኮሌጅ
25. ፍኖተ ብርሀን ኮሌጅ
26. አግሮ ቴክኒካል ኮሌጅ
27. ፋርማ ኮሌጅ
28. .ምስራቅ ግዮን ኮሌጅ
29. አባይ ምንጭ
30. አርባምንጭ መካነየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ
31. ፓራሜድ ኮሌጅ
32. ትሮፒካል ኮሌጅ ኦፍ ሜዲስን
33. ጎቶኒያል ኮሌጅ
34. አያት ሜዲካል ኮሌጅ
35. ሆራይዘን ኮሌጅ
36. እናት ኮሌጅ
37. ራዳ ኮሌጅ
38. ኢንኮዶ ኮሌጅ
39. ግሎባል ኮሌጅ
40. ጋምቢ ኮሌጅ
41. ቢፍቱ ኮሌጅ እና
42. ቴክ- ዞን ኢንጅነሪንግና ቢዝነስ ኮሌጅ ናቸው፡፡

#ETA
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
  
2.3K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, edited  17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 19:21:53
የ2024 ዲቪ ሎተሪ እድለኞች ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ይፋ እንደሚደረጉ አሜሪካ አስታወቀች


የዲቪ 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎች መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን ከፊታችን ቅዳሜ ሚያዚያ 28/2015 ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ አሜሪካ አስታውቃለች።

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በትዊተር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት፤ ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች መታወቃቸው ገልጿል።

በዚህም መሰረት፤ አመልካቾች በዲቪ ሎተሪ ድረገጽ ላይ በመግባት ያመለከቱበትን ልዩ ቁጥር ወይም ኮድ በማስገባት አሸናፊ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ ተብሏል።

ኤምባሲው አክሎም፤ የዲቪ ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው የምንደውለው በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ ያሳሰበ ሲሆን፤ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስለመመረጣቸውና አለመረጣቸው አመልካቾች በድቪ ሎተሪ ድረገጽ ow.ly/9E7A50O7plm ላይ በመግባት፤ በራሳቸው እጃቸው ላይ ባለው ሚስጢራዊ ቁጥር ማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ እንደሆነም አመላክቷል።

በተጨማሪም የ2023 ድቪ ሎተሪ አሸናፊዎች፤ እስከ ቀጣዩ መስከረም 2016 ድረስ ብቻ እንደሚስተናገዱ ኢምባሲው አስታውቋል።

አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺሕ ሰዎችን በ”ዳይቨርሲቲ ቪዛ“ ወይም ድቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ አገሯ የምታስገባ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ የአፍሪካ፣ እስያ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ ዜጎች ይገኙበታል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
2.3K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, edited  16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 19:12:38
Geography final exam

Jimma

2014

━━━━━━━━━━━━━━━━━
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
2.1K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 20:13:54
Arbaminch University

Logic mid exam 2013
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
2.7K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 20:13:54 Applied Mathematics III Final exams with Solutions

pass: 11223344

━━━━━━━━━━━━━━━━━
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
2.4K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, edited  17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 20:13:53
Remedial

English Exam
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.9K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 20:13:53
Remedial

Biology Exam
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.6K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 20:13:53
Remedial

Chemistry Exam
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.5K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ