Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Students Books(Grade 9-12 )

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 ) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 )
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_students_only
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 282
የሰርጥ መግለጫ

በቻናላችን የሚገኙ ጠቃሚ ነገሮች
✅ entrance exam
✅extreme book & referance book
✅Textbook ( 9-12 )
✅Teachers Guide (9-12)
✅worksheet ( 9-12)
✅students info እና ለሎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
@Ethio_Students_only
For comment @EthioStudentsOnly_bot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-13 15:48:40
በትግራይ ክልል ትምህርት ከሦስት ዓመት መቋረጥ በኋላ ቢጀመርም፤ 200 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች አሁንም የተፈናቃዮች መጠልያ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።

በርካታ ተማሪዎች አሁንም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ ተገልጿል።

በክልሉ እስካሁን 1,218 ትምህርት ቤቶች ወደ ሥራ ቢመለሱም ሌሎች ከ490 በላይ ትምህርት ቤቶች በተለያየ ምክንያት አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ኪሮስ ጉዑሽ (ዶ/ር) በክልሉ የሚገኙ 200 የሚጠጉ ትምህርት ቤቶች፤ 182 ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ተጠልለውባቸው ይገኛሉ ብለዋል።

"ከተተኳሾች ባልፀዱ ትምህርት ቤቶች ሥራ አልተጀመረም" የሚሉት ኃላፊው፤ በትምህርት ቤቶች የተጣሉ ተተኳሾችን የማስወገድ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

እስካሁን 1,544 በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ከተተኳሽ ቁሶች የማፅዳት ሥራ የተከናወነ መሆኑን አመልክተዋል።

ሙሉ በሙሉ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባትና በከፊል ውድመት የደረሰባቸውን መልሶ ለማቋቋም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በክልሉ ከ88 በመቶ በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች በጦርነቱ ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መውደማቸውን የትግራይ ትምህርት ቢሮ መግለጹ አይዘነጋም።
#ዶይቼቬለ (DW
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
1.4K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 12:16:59 GRADE 11 BIOLOGY
1.5K viewsFana Education, 09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 12:16:59 GRADE 10 BIOLOGY full note
ይጠቅማችኋል ጥያቄዎቹን ስሯቸዉ በተጨማሪም ኖቶቹንም አንብቡ አሪፍ ናቸዉ
1.5K viewsFana Education, 09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 12:16:59 Grade 10 unit 4 Mathematics
1.5K viewsFana Education, 09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 12:16:59 Grade 10 Physics
1.4K viewsFana Education, 09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 12:16:59 Biology Grade 10 Unit 4 Note
1.2K viewsFana Education, 09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 12:16:58 History Note for Grade -10
1.3K viewsFana Education, 09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 19:02:17
#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ አሟልተው የላኩ 158 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

እስካሁን የተሟላ ዝርዝር ከላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ፣ ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ፣ አድማስ ዩኒቨርሲቲ፣ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ይገኙበታል።

በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላኩ ተማሪዎችን መረጃ እያጣራ መሆኑን የገለጸው ባለሥልጣኑ፤ የተማሪዎችን መረጃ አጣርቶ እንደጨረሰ ለመውጫ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎችን ዝርዝር እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

(የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን የተሟላ መረጃ የላኩ 158 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዝርዝር ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
2.1K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 17:58:19
ከተማሪ ወላጅ ተወካዮችና ከባለስልጣን መስራቤቱ ጋር ውይይት  በማድረግ በሚቀመጠው አቅጣጫ ብቻ ወደ ተግባር ይገባል፡፡

የግል ት/ቤቶች ያደረጉትን ከፍተኛ ጭማሪ በማስመልከት የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለግል ት/ቤቶች ደብዳቤ የጻፈ ሲሆን ከተማሪ ወላጅ ተወካዮችና ከባለስልጣን መስራቤቱ ጋር ውይይት  በማድረግ በሚቀመጠው አቅጣጫ ብቻ ወደ ተግባር የሚገባ መሆኑን አሳውቃል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2016 ዓ.ም የግል የትምህርት ተቋማት የዋጋ ጭማሪ ላይ ውይይት መደረጉን የጠቀሰ ሲሆን ነገርግን በአንዳንድ የትምህርት ተቋማት ላይ አለመግባባት በመፈጠሩ በወረደው ሰርኩላር መሰረት ተግባራዊ እንዲደረግ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
1.3K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 19:05:31
የ2016 የትምህርት ቤት የክፍያ ጭማሪ ከወላጆች ጋር በቂ መግባባት ላይ ሳይደርስ ወደ ተግባር መግባት እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ለሚገኙ የግል እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ፤ የ2016 የክፍያ ጭማሪ በተመለከተ በቀን 12/08/2015 ከኹሉም ት/ቤት ባለቤቶች ጋር ባደረግነው ውይይት መሠረት፤ የክፍያ ጭማሪው በት/ቤቱ እና በወላጆች ውይይት እና መግባባት መሠረት ያደረገ እንዲሆን በጋራ መሥማማት ላይ መደረሱን አስታውሷል፡፡

ቢሆንም ግን፤ በከተማዋ አንዳንድ ተቋማት የክፍያ ጭማሪውን በተመለከተ ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ያልተደረሰ መሆኑን ባለስልጣኑ በውይይቱ ወቅት በአካል ተገኝቶ ባደረገው ምልከታ ማረጋገጡን ገልጿል፡፡

ስለሆነም በ2016 የትምህር ዘመን የክፍያ ጭማሪ ከወላጆች ጋር በቂ መግባባት ላይ ሳይደርስ ወደ ተግባር መግባት እንደማይቻል ያሳሰበው ባለስልጣኑ፤ ባለው አሰራር መሰረት ከተማሪ ወላጅ ተወካዮች እና ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጠው የጋራ አቅጣጫ መሰረት ብቻ ወደ ተግባር የሚገባ መሆኑን አሳስቧል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አክሎም፤ የ2016 የተማሪዎች ምዝገባ በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የትምህርት ቢሮ በሚያወጣው የትምህርት ካላንደር መሠረት ከሀምሌ 2015 በኋላ ብቻ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ በማያደርጉ ተቋማት ላይ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
2.5K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ