Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል ትምህርት ከሦስት ዓመት መቋረጥ በኋላ ቢጀመርም፤ 200 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች አሁ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

በትግራይ ክልል ትምህርት ከሦስት ዓመት መቋረጥ በኋላ ቢጀመርም፤ 200 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች አሁንም የተፈናቃዮች መጠልያ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።

በርካታ ተማሪዎች አሁንም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ ተገልጿል።

በክልሉ እስካሁን 1,218 ትምህርት ቤቶች ወደ ሥራ ቢመለሱም ሌሎች ከ490 በላይ ትምህርት ቤቶች በተለያየ ምክንያት አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ኪሮስ ጉዑሽ (ዶ/ር) በክልሉ የሚገኙ 200 የሚጠጉ ትምህርት ቤቶች፤ 182 ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ተጠልለውባቸው ይገኛሉ ብለዋል።

"ከተተኳሾች ባልፀዱ ትምህርት ቤቶች ሥራ አልተጀመረም" የሚሉት ኃላፊው፤ በትምህርት ቤቶች የተጣሉ ተተኳሾችን የማስወገድ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

እስካሁን 1,544 በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ከተተኳሽ ቁሶች የማፅዳት ሥራ የተከናወነ መሆኑን አመልክተዋል።

ሙሉ በሙሉ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባትና በከፊል ውድመት የደረሰባቸውን መልሶ ለማቋቋም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በክልሉ ከ88 በመቶ በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች በጦርነቱ ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መውደማቸውን የትግራይ ትምህርት ቢሮ መግለጹ አይዘነጋም።
#ዶይቼቬለ (DW
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy