Get Mystery Box with random crypto!

ከመጪው ግንቦት አንድ ጀምሮ የድረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ክፍያ አገልግሎ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

ከመጪው ግንቦት አንድ ጀምሮ የድረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ክፍያ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ የክፍያ ስርዓቶች እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

ዘመናዊ የክፍያ ስርዓቱ በቴሌ ብር፣ሲቢኢ ብር እንዲሁም በሞባይል ባንኪንግ አማራጮች በኩል የሚተገበር ሲሆን ደንበኞች ይህንን በመገንዘብ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያቸውን በወቅቱ እንዲያከናውኑ አገልግሎቱ አሳስቧል።

በአገልግሎቱ የደንበኞች አገልግሎት ሽያጭና ቅሬታ ሰሚ ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት ስምረት በለጠ ለኢዜአ እንደገለጹት የድረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ወርሃዊ የክፍያ ስርዓትን ለማዘመን ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ስትራቴጂካዊ ትግበራ መጀመሩን አስታውሰዋል።

በዚህም፤ላለፉት ሁለት ዓመታት 72 በመቶ የሚሆኑ የድረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ወደ ዘመናዊ የክፍያ ስርዓት መቀላቀላቸውን ጠቅሰው አሁን የቀሩት 28 በመቶ የሚሆኑ ተጠቃሚዎች ወደ ስርዓቱ የሚካተቱ ይሆናል ብለዋል።

በመላ አዲስ አበባ 30 የድረ-ክፍያ አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት መኖራቸውን ጠቅሰው በመጪው የግንቦት ወር 21 የሚሆኑት የድረ-ክፍያ ማዕከላት ሙሉ በሙሉ በቀጥታ ወደ ዘመናዊ ስርዓት ይገባሉ ብለዋል።

እንደ ስራ አስኪያጇ ማብራሪያ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የሚገኙ ዘጠኝ የድረ-ክፍያ አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት ለግንቦት ወር ብቻ የቢል የአከፋፈል ስርዓትን የሚሰጡ ይሆናሉ።

የክፍያ ስርዓቱን በዘመናዊ የአከፋፈል ስርዓቶች ማደረጉ ደንበኞች ከዚህ ቀደም በክፍያ ማዕከላት ሲያጋጥማቸው የነበሩ መጉላላቶችን ከማስቀረቱ ባሻገር ፈጣን እና ተደራሽ የሚሆን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል
 @Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY