Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Students Books(Grade 9-12 )

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 ) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 )
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_students_only
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 282
የሰርጥ መግለጫ

በቻናላችን የሚገኙ ጠቃሚ ነገሮች
✅ entrance exam
✅extreme book & referance book
✅Textbook ( 9-12 )
✅Teachers Guide (9-12)
✅worksheet ( 9-12)
✅students info እና ለሎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
@Ethio_Students_only
For comment @EthioStudentsOnly_bot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-04-23 15:29:00 በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!
ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው ። ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና እንድንተጋ ስለሚረዳን በተሻለ ለመዘጋጀት እንዲሁም ጥሩ ትኩረት ለመድረግ ያስችለናል።  ሆኖም ግን ይህ ጭንቀት ወይም ቴንሽን መጠነኛ ካልሆነ ወደ መደናገር እና ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። በዚህም የተነሳ ፈተናችንን በጥሩ እንዳናስኬድ እና ተገቢውን ትኩረት እንዳንሰጥ ያረገናል ።  ከዚህም ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለዚህ አይነቱ ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ እንድንገባ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ: 
አሉታዊ ሀሳቦች ወደ አዕምሮ በመምጣት ሀሳባችን በሙሉ ስለ ፈተናው አስከፊነት እና ስለውጤት መበላሸት አብዝተን ስናስብ ።

በቂ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ግመታ እና ድምዳሜ አጠቃሎ ስለፈተናው ማሰብ ። 

የውጫዊ ተፅእኖ እንደ ቤተሰብ ፣ መምህራን እና ጓደኛ የሚመጡ ጫናዎች አስተሳሰባችን ላይ ይህ መሆን አለበት ወይም መሆን የለበትም የሚል አቋም መያዝ ስህተትን እንዳንቀበል እና መሳሳትን እንድንፈራ ስለሚያረግ በፈተና መዳረሻ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ።

ሙሉ ሀሳብን ወደ ፈተናው ይዘት እና ሁኔታ ከማተኮር ይልቅ ወደ ውጤት እና ነጥብ ብቻ ላይ ማተኮር እና ማስላት።  እነዚህ ዋና ዋናዎቹ በፈተና ወቅት ውጥረትን እና ጭንቀትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ናቸው።  ስለዚህ ተፈታኞች የተወሰነ ዘዴን በመጠቀም ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤

ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤

ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። 

ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ይህ ማለት ስለፈተናው ክብደት እና አስከፊነት ከማሰብ በተቃራኒው በአይነ ህሊና (visualization) ዘና ብለን ስንፈተን እና ፈተናውን በተገቢ መንገድ ስንፈተን በአእምሮችን መሳል ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በክፍል ውስጥ በብቃት የሰራናቸውን ፈተናዎች እና የገኘነውን ጥሩ ውጤቶች ማሰብ።  እናም ምን አይነት ፈተና ሊመጣ ይችላል ብለን አብዝተን አለመጨነቅ ይልቅ የሚመጣው ፈተና ከዚህ በፊት ከተማርነው የተለየ አለመሆኑን መረዳት እና መጪውም ፈተና በተመሳሳይ እንደምንሰራው ማሰብ።

ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። ምክንያቱም ከላይ እንደ ምክንያት ለተቀመጡት ነጥቦች ከዚህ ሀሳብ በተያያዘ አንድ ተማሪ በፈተና ጥሩ ውጤት ባያገኝ እና ቢሳሳት ቀድሞውኑ ወደ ጭንቅላቱ የሚመጣው አለማወቁ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እና ቤተሰቦቹም ሆነ መምህራን እንደ ሰነፍ እና ዋጋ እንደሌለው ስለሚገመት ስህተትን አስተካክሎ ለቀጣይ ለማሻሻል እና ለመማር መሰናክል ይፈጥራል።   ስለዚህ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። 

ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል። 

የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።

ፈተና ከጀመርን በኋላ መድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤

ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።  

አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ። 

ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።

በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ።
ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር፡፡ ለምሳሌ ;አሁን ደህና ነኝ ፥ ጥሩ ሆኛለሁ ወይም በምናምነው ሀይማኖት ጊዜ የማይወስድብንን አጭር ፀሎት በልባችን መፀለይ። ከዛም መልሰን በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን መጀመር። 

ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤

በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።

ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ። 

በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ይልቅ በጣም ሳንንቀራፈፍ ተረጋግተን ፈተናውን  መስራት እና ፈተናውን ከጨረስን በኋላ ተመልሰን የሰራነውን ጥያቄዎች አጠቃላይ ማየት። 
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.4K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, 12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 19:35:22 #MekelleUniversity

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ላይ በመቐለ ዩኒቨርስቲ ስትከታተሉት በነበረዉ ጦርነት ምክንያት ትምህርታችሁን ያቋረጣችሁና በሌሌች ዩንቨርሲቲዎች ያልተመደባቹህ የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች ቀጥሎ የተቀመጡት መረጃዎችን ከሚያዝያ 16-20/2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ሰዓታት  በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመጠቀም መረጃዎች እንድትሰጡ ተጠይቃቹሃል።

ስልክ ቁጥሮች
EiTM- 0984026089 /0984 026059
MIT-0984 026727
CLG-0984 023987
CHS-0984 023986
CSSL-0984 023985
CBE- 0984 024069
IPS & IPHC-0984 025512
CDAaNR- 0984025593
CVS-098402 4072

ለተጨማሪ መረጃዎች በ 0984025582 ይደዉሉ::

ተፈላጊ መረጃዎች:-
1.ሙሉ ስም
2.የመታወቅያ ቁጥር
3.ትምህርት ክፍል
4.የስንተኛ አመት ተማሪ

# በተመሰሳይ በሌሎች የአገራችን ዩኒቨርስቲዎች ስትማሩት የነበረዉ ትምህርት በጦርነቱ ምክንያት ያቋረጣቹሁ የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች ከላይ ከተጠየቁት መረጃዎች በተጨማሪ ስትማሩበት የነበረዉ ዩኒቨርስቲ ስም በማከል መረጃ በዚህ ስልክ 0984025589 እንድትሰጡ ተጠይቃቹሃል፡፡


የድህረ ምረቃ  ተማሪዎች  በቅርብ  ይጠራሉ::
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY

   
2.2K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, edited  16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 17:38:45 Remedial

physics worksheet
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
2.0K viewsElshio Owner,Ethio Students Admin, edited  14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 17:15:32
For Remedial Students.

Geography work sheet

Buluhora University
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.9K viewsElshio Owner, Ethio Students Admin, edited  14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 17:15:20
General Physics Final Exam

Bahir Dar University
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.7K viewsElshio Owner, Ethio Students Admin, 14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 16:50:00
Haramaya University.

Physics Exam.
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.7K viewsAYY, 13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 16:27:22
#የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል በዝግጅት ላይ እንደሆነ ገልጿል።

በመሆኑም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ #የማይገኙ ሁሉም የዲግሪ (መደበኛ፣ ኤክስቴንሽን፣ ክረምት) እንዲሁም የማስተርስ (መደበኛ፣ ኤክስቴንሽን ፣ ክረምት) ተማሪዎች ከዚህ በታች ባለው ሊንክ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

ሊንክ ፦ http://196.190.28.50

ምዝገባው የሚያበቃበት ቀን ሚያዚያ 18 ቀን 2015 ዓ/ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

ለበለጠ መረጃ ደግሞ ዘውትር በየስራ ሰአት በሚከተሉት ቁጥሮች መወደወል ይቻላል ፦ 0914485592 / 0921990158

ከኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ #የራያ_ዩኒቨርሲቲም በጦርነት የተቋረጠውን መደበኛ ትምህርት ለማስቀጠል እየሰራ ይገኛል።

በዚህም ከ2ኛ እስከ 5ኛ ዓመት በራያ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩና ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የመማር እድል ያላገኙ ተማሪዎች ከ09/08/2015 ዓ/ም እስከ 13/08/2015 ዓ/ም ባሉ የስራ ቀናት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎች የሚመዘገቡት ለዩኒቨርስቲው ረጅስትራር እየደሉ ሲሆን የስልክ ቁጥሮቹ 0970140000፣ 0970240000 ፣ 0970230000 ናቸው። ተማሪዎች ዘውትር በስራ ሰዓት ብቻ እንዲደውሉ ጥሪ ቀርቧል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.8K viewsAYY, 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 10:57:59 ያልተሳሳተ ሰው የለም

እርስዎም ይሞክሯት

1 + 4 = 5

2 + 5 =12

3 + 6 = 21

8 + 11 = ?
524 views Fana Owner, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 18:32:19
የወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ተማሪዎች ቅሬታ

በወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ መብራት ከጠፋ #40 አካባቢ ማለፉን ተከትሎ በግቢው ውስጥ የሚገኙ ከ1500 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ባለፉት ቀናት ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ሲያሰሙ ቆይተዋል። በርካታ ተማሪዎች ጨለማ ላይ እንደሚገኙና ትምህርታቸውን ለመከታተልም እያዳገታቸው እንደሆነ ለATC ሲገልፁ ሰንብተዋል።

ይህ የመብራት ለበርካታ ሳምንታት መቋረጥ ያስመረራቸው የግቢው ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት ሻንጣቸውን በመያዝ ከግቢ ለመውጣት የሞከሩ ቢሆንም የፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ከግቢ እንዳይወጡ እይዳደረጓቸው ገልፀውልናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአንድ ወር በላይ በዞኑ ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት ከሰዓታት በኋላ እንደሚለቀቅ የዞኑ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEM
    
1.2K viewsAYY, 15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 17:38:14
#RayaUniversity

በራያ ዩንቨርሲቲ መደበኛ ትምህርት ስትከታተሉ ቆይታቹህ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ትምህርታችሁን ላቋረጣቹህ ተማሪዎች በሙሉ፣

በራያ ዩንቨርሲቲ በመደበኛ ፕሮግራም ከ2ኛ እስከ 5ኛ ዓመት ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁና ወደ ሌሎች ዩንቨርሲቲዎች ተመድባቹህ የመማር ዕድል #ያላገኛቹህ ተማሪዎች በስራ ሰዓት ብቻ ከ09-13/2015 ድረስ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች እየደወላቹህ ተመዝገቡ።

# Raya University registration
  የራያ ዩኒቨርስቲ ምዝገባ ከ 09-13/08/2015
   via 1.0970140000
         2.0970240000
         3.0970230000
    N.b-በስራ ቀንና በስራ ሰዓት ብቻ

ዩንቨርሲቲው ሙሉ ዝግጅቱን ሲያጠናቅቅ የግቢ መግቢያ ቀንን በመገናኛ ብዙሃን እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEM
1.1K viewsAYY, edited  14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ