Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሚያስተምሩ መምህራን እና የትምህርት አመራ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሚያስተምሩ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ለአራት ቀን የሚቆይ ውይይት በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

ውይይቱ በዛሬው እለት በ77 ክላስተሮች 63,470 መምህራን እና የትምህርት አመራሮችን ተሳታፊ በማድረግ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በዛሬው እለት ውይይቱን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸው በውይይቱ 1,368 ቡድኖች ከመደራጀታቸው ባሻገር 2,736 አወያዮች መመደባቸውን አስታውቀዋል።

ውይይቱ በዋናነት ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት ያስመዘገበቻቸውን ውጤቶችና በሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መሰረት በማድረግ የሚካሄድ መሆኑን ዶክተር ዘላለም ገልጸው ለትምህርት ልማት ስራው ውጤታማነት መምህራንም ሆኑ የትምህርት አመራሮች የአንበሳውን ድርሻ እንደመውሰዳቸው  የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የተማሪዎችን ውጤት እና ስነምግባር ለማሻሻል ውይይቱ የጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት መሆኑንም አስረድተዋል።

ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን በክላስተር ደረጃ ተካሂዶ እሁድ እለት ከየትምህርት ቤቱ ከተውጣጡ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች  ጋር በየክፍለከተማው ተመሳሳይ ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር እሁድ 500 የሚሆኑ መምህራን በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ ታላላቅ የልማት ስራዎችን የሚጎበኙበት መርሀ ግብር መዘጋጀቱን ኃላፊው ጠቁመው ሰኞ ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም በከተማ ደረጃ የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት 5,000 ከሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY