የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰኔ 03/2015 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ ለ4 የዩኒቨርስቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እድገት ሰጥቷል።
በዚሁም መሰረት ፦
1ኛ. ዶ/ር ጌታቸው ዓለማየሁ ዳሞት ከግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ በአግሮኖሚ የሙሉ ፕሮፌሰርነት
2ኛ. ዶ/ር ንጉስ ጋብዬ ሀብቱ ከባሕርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ሙሉ ፕሮፊሰርነት
3ኛ. ዶ/ር መላኩ ዋለ ፈረደ ከሳይንስ ኮሌጅ በኢንቶሞሎጂ ሙሉ ፕሮፌሰርነት
4ኛ. ዶ/ር ፀጋዬ ካሳ ጎጂ ከሳይንስ ኮሌጅ በሥነ-ህዋ ሳይንስ ሙሉ ፕሮፌሰርነት እድገት ማግኘታቸውን ዩኒቨርሲቲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
አንጋፋው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት 60ኛ ዓመት የብርኢዮቤልዩ በዓሉን በማክበር ላይ ይገኛል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy