Get Mystery Box with random crypto!

#Update የሬሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም ይሰ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

#Update

የሬሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰኔ 05/2015 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ የተላከ ደብዳቤ እንደሚያሳየው፤ የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የተቀበሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎችን ዝርዝር፣ ፈተናውን የሚወስዱበት ካምፓስ ማዕከልና የከተማ ሙሉ አድራሻ እንዲሁም በማዕከል የተዘጋጀውን ፈተና የሚረክብ የተቋም ኃላፊ ወይም ባለቤት መረጃ እስከ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም ድረስ ለትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን እና በትምህርት ሚኒስቴር ለአካዳሚክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ መላክ እንዳለባቸው ደብዳቤው ያመለክታል፡፡

(የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ከላይ ይመልከቱ፡፡)
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy