Get Mystery Box with random crypto!

#መመረቅአለባቸው በእውነቱ ከዚህ አድስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ጋር በጣም ቅራኔ አለኝ። ምክንያቱ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

#መመረቅአለባቸው

በእውነቱ ከዚህ አድስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ጋር በጣም ቅራኔ አለኝ። ምክንያቱም እንያንዳንዱ የሚወጡት ውሳኔዎች ተማሪዎች እና ቤተሰቦችን ተስፋ ቢስ የሚያደርጉ ናቸው።

ከነዚህም ውስጥ
1. Exit exam
2. በቀጣይ አመት የስራ ቅጥር አለመኖር
3. Exit exam የወደቁ አለመመረቅ

ይህን ስል exit exam አያስፈልግም ወይም መቅረት አለበት እያልኩ አደለም ነገር ግን የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ግዜ ወሳጅ ከመሆናቸው ባሻገር ሲማሩ የነበሩት በድሮው የትምህርት ፍኖተ ካርታ ነው። ይህ ማለት exit exam በሌለው ነበር። በመሆኑ በጣም ብዙ ጫና ያሳድራል ይባስ ብሎ ካላለፉ #አይመረቁም የሚለው ሀሳብ በጣም አስፈሪና አንገብጋቢ ነው።

ይህ በራሱ ኮንፊደስ ያሳጣል እናም ትምህርት ሚንስተር እንዲሁም የሚመለከተው አካል ሁሉ ለምሳሌ ወመህ  ይህን ነገር አስቸኳይ ማስተካከያ ቢሰጠው ለሀገራችንም ለሰላማችንም ጠቃሚ ነው ።

.... እኔ ባለፈው አመት ነው የጨረስኩት ግን በዚህ ሰአት ተመራቂ ብሆን ብየ ሳስብ በጣም ውስጤ ይጎዳል ...እውነት ለመናገር መማር ኪሳራ የሆነባት ሀገር ላይ ነው የምንማረው ምክንያቱም እንዲህ ሁነን ተምረን ራሱ በአግባቡ ቅጥር የለም ቢኖርም በሰውና በገንዘብ ሆኗል። ብቻ ተስፋ ላስቆርጣችሁ አደለም ግን ወታችሁ ብዙ እንዳትጠብቁ እየነገርኳችሁ ነው እንጅ ...።

መንግስት መውደቅ ሲፈልግ ገበሬና ተማሪ ጋር ይጣላል ይላሉ ያለፉ አባቶቻችን እና ትኩረት ትኩረት  ለተማሪዎች...አመሰግናለሁ
   
መልካሙ ሁሉ ለናንተ ይሁን!
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy