Get Mystery Box with random crypto!

ልብወለድ Ethio_Fiction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_fiction
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.31K
የሰርጥ መግለጫ

#ለሃሳብ_አስተያየት

Admins:- @sam_lizu

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-11-06 21:22:48
አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት የክብር ዶክተር አሊ ቢራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ የቆየ ሲሆን ዛሬ ምሽት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ከኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

ቻናላችን በአርቲስቱ ሞት የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን ትገልፃለች ለቤተሰቦቹና ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ መፅናናትን ትመኛለች።

@ethio_fiction
1 viewሳ² lizu, 18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 16:23:06 ...ዶ/ር ኬይም ጌንት፤ (የናዚ ጀርመን ዘረኞች ከ6 ሚልየን በላይ አይሁዳውያን ሲገድሉ በተዓምር የተረፈ እስራኤላዊ የስነ አዕምሮ ስፔሻሊስት ነው።)

እርሱ እንዲህ አለ :-

"ሕይወቴ በአጋጣሚ ነው የተረፈው። ሚሊየኖች ሲገደሉ በአይኖቼ ተመልክቻለሁ።  ትምህርት ብቻውን ጠቃሚ እንዳልሆነም አይቻለሁ።

የተማሩ ኢንጂነሮች የጅምላ ግድያውን አዳራሽ ገነቡ::

የተማሩ ዶክተሮች ህጻናትን በመርዝ ገደሉ::

እመጫትና እናቶች በተማሩ ነርሶች ተገደሉ።

ሴቶችና ልጆች በኮሌጅ ምሩቃንና መምህራን ግንባራቸው በጥይት እየተመታ ሕይወታቸው እንደዋዛ አለፈ።

ታድያ ይህንን ሁሉ በተማሩ ሰዎች ሲፈጸም አይቼ፤ ትምህርት ብቻውን ጠቃሚ እንዳልሆነ ተገነዘብኩ።

... ....
ወላጆች ልጆቻቸውን ሲያስተምሩ ሰብዓዊነትን ጭምር እንዲያስተምሩ እጠይቃለሁ። እርግጥ ነው ማንበብ፣ መጻፍና የሒሳብ እውቀት አስፈላጊና ተገቢ እንደሆነ አምናለሁ።
ነገር ግን ልጆችን የቀለም ትምህርት ብቻ ሳይሆን
#ሰብዓዊነትንም ጭምር ማስተማር ግዴታችን ነው። "

የተወደዳችሁ የቻናሉ ቤተሰቦች
በዚህ ጉዳይ ዙርያ ምን ሃሳብ አላችሁ? በመወያያ ቡድኑ ላይ ሃሳባችሁን አስፍሩልን!

#share -----> @ethio_fiction

#comment ---> @Cr7_reunited
142 viewsሳ² lizu, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 12:03:25 አስቸኳይ ማስታወቂያ !!!

ክቡራትና ክቡራን ፣ ወንዶችና ሴቶች፣ እህቶቼና ወንድሞቼ፣ አባትና እናቶቼ፣ አክስቶቼና አጎቶቼ፣ አያቶቼና ዘመዶቼ፣ ባልና ሚስቶች፣ ህፃናትና ልጆች፣ እናትና አባት ዛሬ ምንም የምናገረው የለኝም ደህና ዋሉ

#share -----> @ethio_fiction

#comment ---> @Cr7_reunited
534 viewsCr 7, 09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 11:41:46 የአመፃ ልጅ (Born a crime)

ቋንቋን በተመለከተ እየተሻኮታችሁ ላላችሁ ሁሉ ከትሬቨር ኖህ "Born a Crime" መፅሐፍ ላይ ከተተረጎመው "የአመፃ ልጅ" መፅሃፍ "ምትሃተኛው" ምዕራፍ ላይ ይሄንን ቅንጭብ ታነብቡ ዘንድ ጋብዤአችኋለሁ።

..... .....
"እኔም ልክ እንደ እናቴ ብዙ ቋንቋዎችን መናገር ቻልሁ። ንግግራችሁን አስመስዬ ለራሳችሁ መልሼ በማውራት የተካንሁ ነበርሁ። አንዳንድ ጊዜ በጎዳና ላይ ስሄድ ሰዎች በጥርጣሬ አይን እየተመለከቱኝ "ከየት ነው የመጣኸው?" በማለት ሲጠይቁኝ ባናገሩኝ ቋንቋና የአነጋገር ዘዬ ስመልስላቸው ፊታቸው ላይ የግርምት ቅፅበት እየታየና ጥርጣሬያቸው እየተገፈፈ "ይገርማል! ጥሩ ነው። እንግዳ መስለኸን ነው። እንደዚያ ከሆነ ጥሩ።" ብለው ይመልሱልኛል።

..... .....
ቋንቋ እድሜ ልኬን የተጠቀምኩበት መገልገያዬ ነበር። አንድ ቀን ወጣት ሳለሁ መንገድ ላይ ብቻዬን እየሄድሁ የዙሉ ተወላጅ የሆኑ ወጣቶች በቡድን ሆነው እየተከተሉኝ አጠገቤ ሲደርሱ እንዴት አድርገው እንደሚጥሉኝ ሲያወሩ ሰማኋቸው። "ይሄንን ነጫጭባ ሃንግ እንሥራው። “አንተ በግራ በኩል ሂድ። እኔ ከኋላ ሄድበታለሁ” ሲባባሉ ስሰማ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ። መሮጥ አቃተኝ። ድንገት በፍጥነት ወደ ኋላ ዞሬ በዙሉኛ "ስሙ ልጆች ለምን አብረን ሌላ ሰው ማጅራት አንመታም? እኔ ዝግጁ ነኝ። እናድርገው!” አልኋቸው።
ልጆቹ ንግግሬን ሲሰሙ ለጥቂት ጊዜ ክው ብለው ከደነገጡ በኋላ መሳቅ ጀመሩ "ኧረ ጓደኛችን ይቅርታ! ሌላ ነገር መስለኸን ነው። ካንተ ምንም ለመውሰድ አስበን አይደለም። እኛ ለመስረቅ የምንፈልገው ከነጮች ላይ ነው። መልካም ቀን ይሁንልህ ወዳጃችን!" ብለው ጥለውኝ ሄዱ። አንድ ጎሳ መሆናችንን ሳይረዱ በፊት ደብድበው ሊዘርፉኝ ነበር። ይሁን እንጂ ሰላም አወረድን። ይሄንን የመሳሰሉ ገጠመኞች የምናገረው ቋንቋ ከቆዳ ቀለሜ በበለጠ ሰዎች ስለ እኔ የሚኖራቸውን እይታ የሚበይን መሆኑን እንድገነዘብ አድርገውኛል።

.... ....
በጠቅላላው እንደ እስስት ነበርሁ ማለት ይቻላል። የቆዳ ቀለሜን ሳልቀይር ቋንቋን ተጠቅሜ እናንተ ስለእኔ ቆዳ ቀለም ያላችሁን አመለካከት መቀየር እችላለሁ። በዙሉኛ ካናገራችሁኝ በዙሉኛ እመልስላችኋለሁ። በፅዋናኛ ካናገራችሁኝ በፅዋናኛ እመልስላችኋለሁ። ምናልባት በመልክ ላልመስላችሁ እችል ይሆናል የእናንተን ቋንቋ መናገር ከቻልሁ ግን እናንተን እሆናለሁ።".......

.... ....
ለማንኛውም አስራ አንድ የሥራ ቋንቋ ካላት ደቡብ አፍሪቃ ብዙ ትምህርት እንማራለንና የትሬቨር ኖህን "የአመፃ ልጅ" ከመፅሐፍ መደብር ብቅ ብለው ይሸምቱና ያነቡት ዘንድ ጋበዝንዎ።

#share -----> @ethio_fiction

#comment ---> @Cr7_reunited
608 viewsሳ² lizu, 08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 15:21:35
#ለአባትዓለም

ለልጅ ሚኖር አባት
ድሃ ቢሆን እንኳን ያጣ ምንዳና ስም
ራሱን ጥሎም ቢሆን ለልጁስ አያንስም ።

በኢዛና መስፍን

#share -----> @ethio_fiction

#comment ---> @Cr7_reunited
779 viewsሳ² lizu, 12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 10:50:11 "..........ግጥም ላንብብላችሁ አለ ?! "  ባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ ተፈቀደለት።

ግጥሞቹ በየሰው እጅ ነው የሚገኙት ከጻፈ በኋላ የትም ይጥለዋል ።  ለነገሩ የግጥም ሐሣብ ሲመጣለት  ዛር እንዳለበት ያደርገዋል... ያጣድፈዋል። 

"  አስዬ ጨብራሪት መጣች ፣ አስዬ  ጨብራሪት መጣች  ፣  አስዬ ጨብራሪት መጣችብኝ  …  " ብሎ ይቁነጠነጣል ።

አስዬ ጨብራሪት የምታስፅፈው ዛር ናት ። ይህች ዛር ከመጣች አሁኑኑ ነው የምታስብለው ።  በዚህ ጊዜ አጠገቡ ካሉ ሰዎች መካከል (ለምሣሌ ስንዱ)  እስኪርብቶ አንስታ የሚለውን ትገለብጣለች ።  አምስት ……  ስድስት ወይም ሰባት ገጽ ሊሆን ይችላል። 
" በቃሉ ነው የሚያወጣቸው "  ሲባል ሰምቻለው ያልተጻፉ ግጥሞቹን ።  ከተጻፈ በኋላ አይሰርዝም  አይደልዝም  ። 

ከዛ  "አንብቢልኝ "   ይላል ።  ታነባለች   " ሸላይ ናት "  ይላል   በቃ  ።  ከእነዚህ ግጥሞች አንዱን አንብቦልን ሲጨርስ አስተያየት ጠየቀን  ።   እኔም የሚደነቀውን አድንቄ   "  ...ግን ከመጠን በላይ ረዥም ነው "    አልኩት  ። ፈጣን መልስ ሰጠኝ  ።   

"  አንተ የበልግ ካፊያ ከሆንክ እኔ የሐምሌ ወጀብ እንዳልሆን ልትከለክለኝ አይገባም  "  አለኝ።  

ቀደም ሲል አጫጭር ግጥሞች አቅርቤ ስለነበር ነው ።  ግጥሞቼ በበልግ ካፊያ የመሰላቸው ። 

"  ጋሽ ስብሐት እንዴት አየሃት?  "  ጠየቀ።

" አልሰማኋትም .... "   አለው ስብሐት ።

"  አትኩረህ እያየኸኝ አልነበር ? "

"   ..........መጀመሪያ ልሰማህ ጓጉቼ ነበር ።   ቆይቶ ግን የግጥሙ ርዝመት ይሁን የቋንቋው ክብደት አላውቅም እኔና አንተን ለመለያየት ምክንያት ሆነን  ።   እናም አየሰማሁህ ጺምህን ሳይ  ፣   ፊትህን ሳይ በስዕል የማውቀው የራሺያው  ዶስቶቪስኪን  መሰልከኝ  ።  አዬ መመሳሰል ብዬ ስገረም ስገረም  ግጥምህን ጨረስከው አንድ ቀን ትደግምልኛለህ!  "   አለው።

※ እንዳለጌታ ከበደ በ2006  ከጻፈውና ካሳተመው ማዕቀብ  መጽሐፍ የተቀነጨበ  ።


#share -----> @ethio_fiction

#comment ---> @Cr7_reunited
1.4K viewsሳ² lizu, 07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 23:45:42
" ሽማግሌ ከእንቅልፍ ሌላ ምን አለዉ ልጄ ለሊት ዶፍ ጣለብኝና በርዶኝ እንቅልፍ አልወስድ አለኝ አሁን ነዉ የጠዋቱ ፀሀይ ስታገኘኝ... "

ንግግራቸዉን አቋርጠዉ ለመቀመጥ ሙከራ ሲያደርጉ መጪዉን የክረምት ወራት አስባ ሎዛ ነፍሷ እየተጨነቀ አዛዉንቱን ተመለከተቻቸዉ
አዛዉንቱ ግዙፍ ናቸዉ ወይም ሁልጊዜ ልብስ ደርበዉ ስለምትመለከታቸዉ ይሁን ብቻ ኮስማና ሆነዉ አይታዩዋትም ፡፡

ከተጨራመተዉ ቆዳቸዉ ስር ግንባራቸዉ ላይ የተጋደመዉ መስመር የተጓዙትን ህይወት፤ የረገጡትን መንገድ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ወደታች የተንጠለጠሉ ጉንጮቻቸዉን ስትመለከት እድሜያቸዉ ከ80-85 ሊሆን እንደሚችል ትገምታለች፡፡

ሁሌም የሚያብጡት አይኖቻቸዉ ዉስጥ የምታነበዉ ባይተዋርነት ያሳዝናታል፡፡ትዉዉቅ አድርጋ ልግስናዋን ማሳየት ከጀመረች አንድ አመት ቢያልፍም ተጠግታ ታሪካቸዉን ጠይቃ አታዉቅም የምታዉቀዉ ብቸኝነታቸዉን ብቻ ነዉ፡፡ "

ከመጽሐፉ የተወሰደ ::

ስርቅታ
በሰራዊት ተወልደ
የመጀመርያ ዕትም

#share -----> @ethio_fiction

#comment ---> @Cr7_reunited
2.8K viewsሳ² lizu, 20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 00:27:22
" ሐሳብ ቤት ሲመታ " የተሰኘው
የዘወልድ አክመን የግጥም መድብል ለንባብ በቃ ::

ከግጥሙ ይህቺን: - ተጋበዙ

ዝምድና አልባውን በአንድ አሰናስሎ
የተደባለቀን ልይይ - ዘር ኩሎ
ፈር የለቀቀውን በፈርጅ ደምሮ
የተበተነውን ባንድነት አዋግኖ
ክብ አደረጋትና ክፍተቷን ለመሙላት
መወለድ እንዳለ ሞትን ፈጠረባት ::


Share :- @ethio_fiction

Inbox :- 
@Cr7_reunited
3.4K viewsሳ² lizu, edited  21:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 17:45:45
" ደሞዝ የመጣ ቀን ዶሮ ትበላለህ :: በማግስቱ ደሞዝህ ሲያንስብህ የዶሮ ውጤት የሆነውን ዕንቁላል ትበላለህ :: በቀጣዩ ቀን ደሞዝህ የበለጠ ሲሳሳ ደግሞ የዶሮ ምግቦችን እንደ በቆሎና ገብስ ያለ ጥሬዎችን ትመገባለህ :: በተከታታይ ቀን ደሞዝህ ሲሟጠጥ አንተ ራስህ ዶሮ ትሆንና የምትበላውን ነገር ፍለጋ ወዲህ ወዲያ በመባዘን ጊዜህን ታሳልፋለህ "

#ምንጭ
" የጠቢባን ማዕድ " ከተሰኘው የዲ/ን ወንደወሰን የኋላእሸት መጽሐፍ የተወሰደ ::




Share :- @ethio_fiction

Inbox :-  @Cr7_reunited
1.2K viewsሳ² lizu, 14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 22:17:59
" ... እዚህ አዲሳባ ውስጥ አንዳንድ ቦታ እንጀራ በቢላ ሲቆረስ እናያለን። ይኼ በቢላ እንጀራ የመቁረስ ባህል የጀመረው ማን ነው ? ለምን ጀመሩ ?

እንጀራን በቢላ መቁረስ እንጀራን ወደ ዳቦ ለማውረድ መጣር እንደሆነ አልተረዱትም?

የእኛ ትልቁ ችግራችን እውር ኮፒ አድራጊዎች መሆናችን ነው ። ፈረንጅ ዳቦ ሲቆርስ አይተን ከዛ  በጭፍን ያለ ጥየቃ ያለትንታኔ ተበደርን ። የዚህ ችግር መነሻው በራሳችን ማመን አለመቻላችን ነው ። በራሱ የማያምን ሕዝብ ወደ ባርነት የሚጓዝ ነው።

ለመሆኑ እንጀራ ለመቁረስ እጅ አነሳትና ነው ቢላ የመጣባት ? በእንግሊዘኛ ኦቨርኪል (overkill) ይባላል። ዝንብ ለመግደል ታንክ ስታወጣ ማለት ነው ።

እንጀራ ቢደርቅ እንኳን አይፈነክትም :: እንጀራ ጥፊ እንኳን አይሆንም :: ምኑ ሰይፍ ያስመዝዛል?
ግን እንጀራ አገር ያቆማል ...”

#ምንጭ
እቴሜቴ ሎሚሽታ ----አዳም ረታ

Share :- @ethio_fiction

Inbox :-  @Cr7_reunited
352 viewsሳ² lizu, 19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ