Get Mystery Box with random crypto!

ልብወለድ Ethio_Fiction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_fiction
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.31K
የሰርጥ መግለጫ

#ለሃሳብ_አስተያየት

Admins:- @sam_lizu

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-02-18 20:58:50 በዓለም ላይ ስንት አምባገነኖች ተሰባብረው እንደወደቁ ማሰላሰል ነው! የደገፉ መስለው ጧት ማታ ሲያጨበጭቡልን ጤነኛ መስለውን፤ “አሁን ነው ራስን ማሳየት” ብሎ ብቅ ማለት አደጋ አለው! ለመውረድ ብዙ ሽቅብ መውጣትም ክፉ ባህሪ ነው፡፡ ሁሉን፣ ሁልጊዜ አገኛለሁ ማለትም ግብዝነት ነው፡፡ እያጨበጨቡ ጎል ከሚከቱን ይሰውረን!

ዛሬ የትምህርት ጊዜ ነውና ትምህርታችንን ይግለጥልን፡፡ እንደ እስያ፤ “ዕውቀት እያለ የሚማር ጠፋብን” የሚል ትራጀዲ ውስጥ እንዳንገባ አምላክ ይጠብቀን!

“ምዕራቡ ዓለም ሲያስነጥስ ሌላው ክፍለ ዓለም ኒሞኒያ ይይዘዋል” የሚለውን በማሰብ፤ እንዳይምታታብን ራሳችንን እንቻል! የራስን የመሰለ ምንም ነገር የለም፡፡
የመጨረሻው እንግሊዛዊ የህንድ ገዢ ሎርድ ሉዊ፣ ለማህታማ ጋንዲ እንዲህ አለው “እኛ ከወጣን በህንድ አገር ቀውስ ይፈጠራል!”
ይሄኔ ማህታማ ጋንዲ፤
“አዎን ቀውስ ይፈጠራል - ቀውሱ ግን የራሳችን ነው!” አለና፤ ኩም አደረገው፡፡

“የራሳችንን ቀውስ ‘ራሳችን እንፈታዋለን!”
አንድ ፀሐፊ ካነበብናቸው በርካታ መጣጥፎች አንዱ ላይ፤ “የአዕምሯችን ማዕከል፣ እና ደጃፉም ሆነ ግንባሩ በጣም ሩቅ ለሩቅ ናቸው! ግን ተቀናጅተው ሥራ ይሰራሉ” ይላል፡፡ የእኛም ተግባር እንደዚሁ የተቀናጀ መሆን ይኖርበታል! ከተሳሰብንና ከተናበብን የስሌት ስህተት አንሰራም፡፡ የፍርድ ማዛባት ስህተት አንሰራም፡፡ የመረዳዳት ማቃት ስህተት አንሰራም፡፡

Share ----> @ethio_fiction

#መልካም_ምሽት
572 viewsሳ² lizu, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 20:58:50 #አስተማሪ_ታሪክ

እናትና ልጂ ቢምቢዎች

ከዕለታት አንድ ቀን፣ አንድ እናት ቢምቢ ትንኝና ልጅ ቢንቢ ትንኝ ነበሩ፡፡ ልጅዬዋ ቢምቢ፤ በአገሩ እየተዘዋወረች ዙሪያ ገባው ውስጥ ነዋሪ - የሆኑትን እንስሳት፣ አዕዋፍና ነብሳት ልትጠይቃቸው ጎራ ልትል አሰበች፡፡ ይህንን ያወቀችው እናት፤
“መሄዱንስ ሂጂ፡፡ ዘመድ ማግኘትና መጠየቅ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ወዳጅና ጠላትሽን መለየት ይኖርብሻል፡፡ ጠላት የመሰለሽ ወዳጅ ሆኖ ይገኛል፡፡ ወዳጅ ያልሺው ደግሞ፣ ጠላት ሆኖ ተለውጦ ታገኚዋለሽ። ለማንኛውም ማጣራትን የመሰለ ነገር የለም፡፡”

#ልጅዬዋ ቢምቢም፤
“እሺ እማማ፣ ቀስ ብዬ እያጣራሁ ለማየት እሞክራለሁ” ብላ አካባቢዋን ልታጠና መንገድ ቀጠለች፡፡
መጀመሪያ ቢራቢሮን አገኘች፡፡ “ቢራቢሮ እንደምነሽ?”
ቢራቢሮ፤
“ደህና ነኝ” አለች፡፡
“በአካባቢው ያሉ ነብሳት ተስማምተውሽ ይኖራሉ?”
“አዎን፡፡ ግን ክረምትም በጋም ሳልቸገር ለመኖር በመቻሌ፣ ወረተኛ ነሽ እያሉ ይወቅሱኛል”
“እነሱ ምን ፈልገው ነው?”
“ወይ የበጋ ሁኚ ወይ የክረምት ሁኚ ነው የሚሉኝ”
“ቆይ፤ ስለዚህ ጉዳይ እናቴን ጠይቄ ምን እንደምትል እነግርሻለሁ” ብላት ቢምቢ ሄደች፡፡

ቀጥላ ጦጣን አገኘቻት፡፡
“ጦጢት እንደምንድነሽ?”
“ደህና ነኝ”
“ከእንስሳቱ ጋር ስትኖሪ ምን ችግር ገጥሞሽ ያውቃል?”
“ምንም ችግር አልገጠመኝም፡፡ ግን ሁሉም በአንድነት በእኔ ላይ ፈርደው ብልጣ - ብልጥ ብትሆኚ ምን አለበት ታዲያ?”
“ታታልይኛለሽ፡፡ ታሞኚኛለሽ እያሉ ነው፡፡”
“የራሳቸው ጅልነት ነው ተያቸው” ብላ ቢምቢ መንገድ ትቀጥላለች፡፡

ብዙም ሳትሄድ አንበሳን አገኘችው፡፡
ቢምቢ፤
“ደህና ዋልክ አያ አንበሶ?”
“ደህና ነኝ፤ ቢምቢ”
“እንስሳት አብረውህ ሲኖሩ ምን ይሉሃል?”
“ጉልበተኛ ነህ፡፡ አምባገነን ነህ፤ ነው የሚሉኝ” አለ እየተጎማለለ፡፡
“አቅም ስላነሳቸው ነው እነሱ፡፡ ተዋቸው፡፡” ብላው መንገዷን ቀጠለች፡፡

በመጨረሻ የተሰበሰቡ ሰዎች አግኝታ፣ እነሱን አዳመጠችና፣ እየመሸ ስለመጣ ወደ እናቷ ተመለሰች፡፡ የሆነችውን ሁሉ ነገረቻት፡፡

“ሰዎችስ ምን አሉሽ?” አለቻት እናት ቢምቢ፡፡
ልጅየዋ ቢምቢም፤
“ይገርምሻል፤ ሰዎችማ ሲያጨበጭቡልኝ ዋሉ” አለቻት፡፡

እናት ቢምቢም፤
“ልጄ ሁለተኛ እንዳትሳሳቺ! እንደ፣ሰዎች ክፉ የለም፡፡ ያጨበጨቡልሽ የመሰለሽም በመዳፍና መዳፋቸው ጨፍልቀው ሊገድሉሽ ሲሞክሩ ነው፡፡ ስለዚህ ዳግመኛ እንዳትታለይላቸው!” አለችና መከረቻት፡- “ማጨብጨብ የሰው ልጆች ኃይለኛ መሳሪያ ነው፤ ተጠንቀቂ!”
#ተፈፀመ
557 viewsሳ² lizu, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 02:57:42
"ይኼ ሰው ... ዕብሩቱና ትዕቢቱ ለታላቅ ውድቀት ዳረገው ...
ሰይጠን ቤተክርስቲያን ላይ ዝናሩን ጨረሰ ... ቤተክርስቲያንን ግን ሊያሸንፍ አልቻለም! "
ዝም!

Share ----> @ethio_fiction
525 viewsሳ² lizu, 23:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 21:23:35
" ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ ታላቅ ደስታ ተሰምቷታል " - ቅዱስ ሲኖዶስ

ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ውስጥ የተወሰደ ፦

" ... በዛሬው ዕለት የቤተ ክርስቲያን ጸሎቷ፣ ሐዘኗና ጩኸቷ ተሰምቶ ወደ ነበረችበት ልዕልናዋና አንድነቷ ተመልሳለች፡፡ ይህ አንድነቷና ልዕልናዋ እስከ ዓለም ፍጻሜ ተጠብቆ ይኖራል፡፡

በቅርቡ በቤተ ክርስቲያናችን ተከስቶ የነበረው ችግርም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ተፈትቷል፡፡

... በችግሩ አፈታት ወቅት መንግሥት በተለይም ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፖለቲካዊ ችግሩን በፖለቲካዊ መንገድ ከመፍታታቸውም ባሻገር የቤተ ክርስቲያን ችግር በቀኖናና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት እንዲፈታ ታላቁን አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀደም ሲል ሁለቱን ሲኖዶስ አንድ በማድረግ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አሁንም የቤተ ክርስቲያን አንድነት ተጠብቆ እንዲኖር ላደረጉት መልካም ተግባር ቤተ ክርስቲያን ከልብ ታመሰግናለች፡፡

... ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ ታላቅ ደስታ ተሰምቷታል፡፡ ካህናት፣ ምእመናን በሀዘናችን ተካፋይ የነበራችሁ በሙሉ የዚህ ደስታ ተካፋዮች በመሆናችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት ቅድስት ቤ ክርስቲያን ደስታዋን ትገልጻለች፡፡ "

share - @ethio_fiction
778 viewsሳ² lizu, 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 20:36:58
#መግለጫ

ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መልኩ ሣመት በፈጸሙት አባቶች መካከል ስምምነት የተደረሰ ሲሆን ስምምነቱን በተመለከተ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩት በቀድሞ ስማቸው እነ አባ ሳዊሮስ በዛሬው ዕለት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተው የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባታቸው መረጋገጡን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን አሳውቀዋል።

እልልልልልልል

share ---> @ethio_fiction
826 viewsሳ² lizu, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 17:56:01 #ሰበር_ዜና

በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት "አባ" ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ  ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በማስረከብ ቤተክርስቲያንንና ምእመናንን ይቅርታ ጠይቀዋል።

በይቅርታ ደብዳቤያቸውም ሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖዶሱ እውቅና ውጪ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሲካኼድ ከኢየሩሳሌም መጥቼ ከተሾሙት አንዱ ነበርኩ።

በዚህ ምእመናንን ባሳዘነ ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ውግዘት ባስተላለፈበት ሕገ ወጥ ሢመት ውስጥ ባለማወቅና ነገሩን ሳላጣራ የገባሁበት በመሆኑ በእጅጉ የተጸጸትኩና በዚህም ተግባር ያዘንኩ መሆኔን በይቅርታ ልብ ለመግለጥ እወዳለሁ። በመሆኑም በዛሬው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሠየመው አቀራራቢና በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት በተከፈተው የይቅርታና የምሕረት በር ወደ እናት ቤተክርስቲያኔ እና የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼ እንዲሁም ምእመናን ለይቅርታ የቀረብኩ ስለሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ይቅርታዬን በአባትነት መንፈስ ይቀበለኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ ብለዋል ።

#ወጥሩ #ተዋህዶ_አትፈርስም

ምንጭ:- EOTC TV
648 viewsሳ² lizu, 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 02:21:44
ጠያቂ "ሰው እየሞተ እርሶ ግን መፍትሄ ከመስጠት ችግኝ መትከሉን ተያይዘውታል።"

ጠ/ሩ “ሰው እየሞተ የሞተበት ቦታ ችግኝ እንተክላለን፣ ቢያንስ አስክሬኑ ጥላ እንዲኖረው”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

ምንጭ፡- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

#ደህና_እደሩ !!!
591 viewsCr 7, 23:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 02:07:12 #የተወደዳችሁ
የፕሮቴስታንት፣ የሙስሊሙ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ... በመሀላችን ምን ያህል ሰይጣናዊ መረብ እንደተዘረጋ በመረጃና በማስረጃ ጭምር አስደግፌ የማቀርብላችሁ ነገር ይኖራል ጠብቁ!!!

#ለምን_ሞት ተፈለገ !?

#ለምን_ሞትን ተላመድነው !?

#መንግስት_ለምን ሞትን አቅለን እንድናይ ባደባባይ ያውም በግልፅ በጅምላ የሚታረዱትን የሚቀበሩትን ያሳየናል?!

#ጠይቁ!!!
593 viewsCr 7, edited  23:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 01:44:12
#መረጃ

ከላይ በተያያዘው የፎቶ መልዕክት ላይ እንደምታዩት መንግስት የማምለጫ ምክንያት ደርድሮ ይታያል!

#የኔ_ጥያቄ???
ለምን የቅዳሴ ሰዐት መጀመርያና ማብቂያ ጊዜን ለመጠቀም አስፈለገው???

#ጠርጥሩ!!!
528 viewsሳ² lizu, 22:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 01:36:52 #ውድ የቻናሉ ቤተሰቦች
የሰሞኑየሃይማኖት ጉዳይ መስመሩን እስኪይዝ ድረስ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በትዕግስት ተከታተሉን!

ሰላም ለሃገራችን ውድቀት ለጠላቶቿ !
469 viewsCr 7, 22:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ