Get Mystery Box with random crypto!

ልብወለድ Ethio_Fiction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_fiction
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.31K
የሰርጥ መግለጫ

#ለሃሳብ_አስተያየት

Admins:- @sam_lizu

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-23 17:06:24 አንብባችሁ የemoji ምልክቶችን በመንካት ለቀጣይ ስራ ድጋፋችሁን አድርሱኝ።
536 viewsሳ² lizu, edited  14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 16:54:55 (የባለደብዳቤዋ የስንብት ሙዚቃ )
ፍቅርህ እንኳን ቋሚ ሙት የሚቀሰቅስ
ስለተለየኸኝ ሳትሞት እንዴት ላልቅስ ።

Inbox Comment
➷ ➷
@sam_lizu @ethio_fiction
570 viewsሳ² lizu, 13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 16:54:41 የሳሚ ደብዳቤዎች

ቀን: 15/08/2015 ዓ.ም

#ርዕስ: የለውም

#አዘጋጅ ፦ ሳምሶን (channel Admin)

#ላኪ፦ ሔመን

#ተቀባይ: ዳንኤል

#የላኪ_አድራሻ: ደብረዘይት

#የተቀባይ_አድራሻ: ድሬድዋ

ውዴ ሆይ፣ ለዘመኔ ማብቂያ ላንተ ፍቅር መርሻ፣ ባንጠለጠልኩት መታነቂያ ገመድ ፊት የመጨረሻ ቃሌን በወረቀት አሰፈርኩልህ። ደብዳቤው ላይ፣ የስልክ ቁጥርህንና አድራሻህን ስለፃፍኩኝ: አስከሬን የሚያነሱ ሰዎች ያቀብሉሃል። ውዴ መለየቴ መርዶ አይሁንብህ:: እኔ እኮ በድን ከሆንኩኝ ድፍን 10ት አመታት ተቆጠሩ።  ያሳለፍናቸው ውብ ወቅቶች፣ ናፈቁኝ የምንቀመጥባቸው ድንጋዮች፣ ታወሱኝ እንጃልኝ እኔ .... የሆንኩትን አላውቅም የሆነውንም አላምንም ..።

አንዳንድ ጊዜ ውዴ ጫወታና ሳቅህ ባይኔ እየዋለለ፣ ብዙ ጊዜ ስቃዬን አሳየኝ ፣ አልቻልኩም ቸገረኝ፣ በነጋ በጣ በፊቴ ትመጣለህ፣ ድምፅህ በጆሮዬ እየተመላለሰ ያስተጋባል፣ አይ መከራዬ። ድንገት ተነስቼ በደካከሙ እግሮቼ መንገዱን እገፋዋለሁ። አንተ ወዳለህበት፣ አንተን ወደማገኝበት፣ እሄዳለሁ።

ይኸው የመንደሩ ሰዎች እየተጠቋቆሙ ልጅቷ ጨለለለች ነቀለች ይላሉ። ምንም አደለም ይሁን፣ ጨርቋንም ጥላለች ቀወሰች ይበሉ። ይሳሳቁብኝ ይዘባበቱብኝ። "ደሞ ምን ሆነሻል" ሲሉኝ በመውደድህ ቅዠት  የምናገረው እየጠፋኝ፣ ስርበተበት እንደህፃን ስኮላተፍ
ደሞ ከመንገዴ እቆምና ጥንዶች እየተሳሳቁ ሳይ ሆድ ይብሰኛል።
አይዞሽ ባይ በሌላት በትንሿ ጎጆዬ የዘመመ በሬን ዘግቼ አለቅሳለሁ ፣ እነዚያን የማይረሱ ዕለታት በምን ልተዋቸው?

ውዴ ሆይ መተው እኮ አቅቶኛል ... የምታዜምልኝን ዜማ እኮ አሁንም ይሰማኛል በተለይ ....
"አንቺ የእንጆሪ ፍሬ
ማዛሽ እያማረ
ከሾህ ሀረግ በቅለሽ
መውጫው አስቸገረ።" ይኸውልህ ልቤ ልክ እንደ እንጆሪዋ ፍሬ የኔም ህይወት መውጫው ጠፍቶታል የሃሳብ እሾህ ተሰክቶብኛል ዕድሜ ልኬን ታምሜ አለሁ። አንተ ሰው አታውቅም ብነግርህም አትረዳም።

ውይ ትዝታው ምንም የሚጣልና የሚረሳ አደለም፤ አሁንማ ምንያደርጋል አንተ የለኸኝም ቆሜ ዳርኩህ፤ እያረርኩኝ ሳቅኩልህ፣ እያነባው እልልልል አልኩኝ፣ ... በሀዘኔ ቀን ላንተ ነጭ ለበስኩ።
አሁን የመጨረሻ ቃሌን ሰጥቼሃለሁኝ፤
ከነልጅነት ንፁህና ሀቀኛ ፍቅሬ ተሰናበትኩህ በቀለበት ፋንታ ገመድ አጠለቅኩ አንተ እየበራልህ የእኔ ዘመን ጨለመ ታሪኬ አበቃልኝ እኮ መውደዴ ሜዳ ቀረ፣ ፍቅሬን ውሃ በላው።
ቻው ቻው!
ያንተ ደካማ ሴት!

(አንድ ሙዚቃ በሚሞሪ አድርጌ ደብዳቤው ውስጥ አስቀምጬልሃለሁኝ። የልጅነት ፎቶም ተያይዞልሃል።)

#ተፈፀመ

#Comment: @sam_lizu
      
   ---- ----

#share - @ethio_fiction
599 viewsሳ² lizu, 13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 10:24:11
<<እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤ የወይን ስካር
እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ፤»
(መዝ 77፡65)።

ውድ የቻናሉ ቤተሰቦች ...
ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ  ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም የትንሣኤ በዓል

Contact --> @sam_lizu

Share ---> @ethio_fiction
1.0K viewsሳ² lizu, 07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 12:21:04 #ግጥም: በ Tsedi Haile ከአዳማ

#ርዕስ : የዳዊት ጠጠር

#Share :- @ethio_fiction
282 viewsCr 7, 09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 21:57:58 ደብዳቤዬን ግጩት

Inbox --> @Cr7_reunited
915 viewsሳ² lizu, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 21:57:24 የሳሚ ደብዳቤዎች

ቀን: 14/07/2015 ዓ.ም

#ርዕስ: ያራዳው ደብዳቤ

አዘጋጅ ፦ ሳምሶን (channel Admin)

ላኪ ፦ ሳሚ

ተቀባይ: ቲቲ

የላኪ አድራሻ : የለውም

የተቀባይ አድራሻ : ቦሌ

ክረሽ ፎንቃሽ ጠግርሮኝ ይኸው መሃል ፒያሳ ላይ ሻሿ እንደተሰራ ሼባ መሬት መሬቱን እየሾፍኩልሽ ነው እና ምንሼ ነው ? ቤትሽ ድቃስ መተሽ ያለሽው! realy አይነፋም! እና ደሞ ጀማው በሞላ ፎንቃ እንደቀወረኝ ባኔ ብሏል።
ምንሼ ገነቸርሽ እኮ ... የግድ ክላክስ ማድረግ አለብኝ ... በየትኛው መላዬ ነው ጋቢና ምበረግድልሽ ... በቸርኬው ዎክ መተን ብንከንፍስ ... ጭዌሽ ደሞ ፈምሶብኛል .. ያ ደሞ ፀጉር ላይ እንደተጣበቀ ማስቲካ የማይነጠለው ጀለስ ምንሼ ነው ... ቀይ ግጪው እንጂ አልነፋኝም ... ድጋሚ ካገኘሁት እቀየርበታለሁ እቴትዬን!

ይኸው ማዘሯ የሌለ ደንቅራለች .. ቤት ኦንና ኦፍ በሆንኩ ቁጠር ያቺ ካማሪካን የከተመችው ቸከስክ አትዘይረኝም እያለች የመጬ እያፈላች ነው። እና ምርጥዬ ማዘሯ ከቋጠረች physics ነው። ተከሰቺና ላይፏን ሹፊላት ... ያራዳ ፈላ መሆንሽን አስመቺ እንጂ እና ደግሞ ቲክታክ ላይ ከልሜሽ የመጬ ቦግ አልኩኝ ... ጉዳያችን ሳይጭር ሌላ ጭዌ መለኮስ ገመድ አይሆንብሽም ... እቴትዬን ይደብራል!

ክለብ ላይ ካንቺ ጋር የሚያቀኝ ፍሬንድ
የመጬ ጨብሶ ... ዕልልል ያለ ግጥም አወረደብኝም ... 6 ስንኝ ሚሞዬ ላይ ተቆልፎብኝ ደቅ አልኩልሽ።

እስቲ ከነፋም ካልነፋም መታ መታ አድርጊያቸው ከነ አክቱ ነው ...

ይንቦገቦጋል እንደ ክለብ ላይት
ሳሚዬ ሳሚዬ ቲቲዬ ጠፍታበት
አልጨረስኩም ቂቂቂቂ...
ቲቲዬ ቲቲዬ አንቺ አራዲቱ
ሳሚዬ ሳሚዬ ቀረ በራቁቱ
አልጨረስኩም ቂቂቂ...
በሶውን ለአበበ ጩቤውን ለጫላ
እግዜር ይስጥሽ ቲቲ ሳሚ ዲንጋይ በላ

አላስጨረስኩትም ቱቦ ውስጥ ቀርቅሬው
ይኸው ዶሴ ተበርግዶ ቂሊንጦ ሰመጥኩልሽ.... ደብዳቤውን ዛሬ አፉ ተብዬ እንደወጣሁ ጠቀጠቅኩልሽ
ይመችሽ ያራድዬ ልጅ ከመሃል ፒያስ ... ከድልድዩ ስር።
ቅዳሜ ማሙድ ጋር ጠብቂኝ!

ያንቺው ዘናጭ

         ---- ----

#share - @ethio_fiction
974 viewsሳ² lizu, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 19:46:53 ልብወለድ Ethio_Fiction pinned «የሳሚ ደብዳቤዎች ቀን: 12/12/1991 የ100 አለቃው ደብዳቤ አዘጋጅ ፦ ሳምሶን (channel Admin) ላኪ ፦ 100 አለቃ ሳምሶን ተቀባይ: ወ/ት ብሌን የላኪ አድራሻ : ሰሜን ዕዝ 31ኛ ክ/ጦር የተቀባይ አድራሻ : ናዝሬት 400 ፍቅር 300 ትዝታ የምችለው ስጠኝ አቤት የኔ ጌታ ይድረስ በተስፋና በፍቅር ለምትጠብቂኝ…»
16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 19:30:11 ደብዳቤዬን የተያያዙትን emoji በመጫን ብርታትን ስጡኝ

ትረካ መተረክ የምትፈልጉ ሰዎች በውስጥ መስመር አናግሩኝ
Inbox --> @Cr7_reunited
460 viewsሳ² lizu, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 19:29:56 የሳሚ ደብዳቤዎች

ቀን: 12/12/1991
የ100 አለቃው ደብዳቤ

አዘጋጅ ፦ ሳምሶን (channel Admin)

ላኪ ፦ 100 አለቃ ሳምሶን

ተቀባይ: ወ/ት ብሌን

የላኪ አድራሻ : ሰሜን ዕዝ 31ኛ ክ/ጦር

የተቀባይ አድራሻ : ናዝሬት

400 ፍቅር 300 ትዝታ
የምችለው ስጠኝ አቤት የኔ ጌታ
ይድረስ በተስፋና በፍቅር ለምትጠብቂኝ ፈገግታና ጨዋታ ለተዋሃዱልሽ የጥንቷ ጓደኛዬ ወ/ት ብሌን።
በጥይት እሩምታ በመድፍና መትረየስ ጋጋታ የምትናጠው ነፍሴ ጥቂት ፋታ ባገኘች ጊዜ ፃፍኩልሽ።

ህይወት በዚህ መንገድ ትመራናለች፣ ሃገሩም እንዲህ ይተራመሳል፣ የሚል ሃሳብና ዕቅድ እንዳልነበረን ሳስታውስ "አይ ጊዜ" እያልኩ እስቃለሁ ።
ነፍሱን ይማረውና አዝማሪው ታጋይ ጓደኛዬ እንዲህ ተጫወተ:-
"ማታ ተቀጣጥረን ስጠባበቃት
በጊዜ ተሸኘች ያቺን ልጅ አሟት።"

አየሽ ትናንትን በትውስታ ስጓዘው፣ ባለፈ እንጉርጉሮ ስመሰጥ፣ እነዚያን ውብ ሌሊቶች፣ ተቃቅፈን የተጓዝንባቸው ጎዳናዎች፣ አብሮ መብላት አብሮ ማደር፣ የሚናፈቅ መሽኮርመምሽ፣ ያ ውብ ሳቅሽ
ተራራሮችን ሰነጣጥቆ፣ ካለሽበት ሰማይ አድማስ ጥሶ ከሩቅ ማዶ ... እየመጣ ትዝታው ለኔ ሲሆን አንቺን አንቺን የሚያሰኘኝ ገራገርነትሽ ... በልቼ የጠገብኩ፣ ጠጥቼ የረካሁ የማይመስልሽ ... ሲከፋኝ የምታነቢልኝ፣ መጥፋቴ ሚጨንቅሽ ... የምሽት ህልሜ የለት ጉጉቴ የነበረሽ

ታስታውሺ እንደሆን መች እንደምንጋባ፣ ፣እነማን ሚዜ እንደሚሆኑን፣ ስንት ልጆች እንደሚኖሩን ... ካልረሳሽ ደግሞ አንቺ የበኩር ልጄ ሴት እንድትሆን እፈልጋለሁ ባልኩሽ ጊዜ ... ወንድ መሆን አለበት በማለት 1 ሳምንት ሙሉ ማኩረፍሽን... ... አቤት ኩርፊያሽ ... 1 ጋንታ ያስከፋል እኮ ... አንቺን ከኩርፊያሽ ለመለየት እንደ ደንበኛ የጠላት ምሽግ ልዩ ኦፕሬሽን ይጠይቃል።

ደሞ የቤተሰቦችሽ ሃይለኝነት ያባትሽማ ለጉድ እኮ ነው፣ በዛ ላይ በረባ ባልረባው ሄደሽ ምታቃጥሪው ነገር...
ተደራጅተው ሲመጡ ደሞ ለወሬ ነጋሪ አያስቀሩንም አብዛኛው የሰውነቴ ጠባሶች ይህን በሚገባ ያስረዱኛል።

ይኸው ዛሬም አንቺን ማሰብ ... የአድዋን ተራራ መውጣት ሆኖ ... ወደ ኋላ ይጎትተኛል። ከውሃው በላይ ጫወታሽ ጠማኝ፣ ከምግብ ይልቅ አይኖችሽን ተራብኩ፣ ... እረፍት አጣሁ። መለያየትን አንገት ለአንገት ተናነቅኩልሽ።

የኔ ውድ እያንዳንዱ ደብዳቤዎቼ ላይ ስንብቴም ተያይዞልሻል። ምናልባት ከተሰውት መሀል ልትመለከቺኝ ትችያለሽ፣ ወሬዬን ላትሰሚ ትችያለሽ፣ አርፏልም ሊሉሽ ይችላሉ። ከዚህ ደብዳቤ ጋር ያፅናናሽ ይሆን ብዬ ፎቶዎችን አንድ ላይ ደብዳቤው ውስጥ አስቀምጬልሻለሁ።
ቻው!


ያንቺው ምርኮኛ!

ከሰሜን ዕዝ 31ኛ ክ/ጦር
---- ----_

#share - @ethio_fiction
530 viewsሳ² lizu, 16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ