Get Mystery Box with random crypto!

የሳሚ ደብዳቤዎች ቀን: 12/12/1991 የ100 አለቃው ደ | ልብወለድ Ethio_Fiction

የሳሚ ደብዳቤዎች

ቀን: 12/12/1991
የ100 አለቃው ደብዳቤ

አዘጋጅ ፦ ሳምሶን (channel Admin)

ላኪ ፦ 100 አለቃ ሳምሶን

ተቀባይ: ወ/ት ብሌን

የላኪ አድራሻ : ሰሜን ዕዝ 31ኛ ክ/ጦር

የተቀባይ አድራሻ : ናዝሬት

400 ፍቅር 300 ትዝታ
የምችለው ስጠኝ አቤት የኔ ጌታ
ይድረስ በተስፋና በፍቅር ለምትጠብቂኝ ፈገግታና ጨዋታ ለተዋሃዱልሽ የጥንቷ ጓደኛዬ ወ/ት ብሌን።
በጥይት እሩምታ በመድፍና መትረየስ ጋጋታ የምትናጠው ነፍሴ ጥቂት ፋታ ባገኘች ጊዜ ፃፍኩልሽ።

ህይወት በዚህ መንገድ ትመራናለች፣ ሃገሩም እንዲህ ይተራመሳል፣ የሚል ሃሳብና ዕቅድ እንዳልነበረን ሳስታውስ "አይ ጊዜ" እያልኩ እስቃለሁ ።
ነፍሱን ይማረውና አዝማሪው ታጋይ ጓደኛዬ እንዲህ ተጫወተ:-
"ማታ ተቀጣጥረን ስጠባበቃት
በጊዜ ተሸኘች ያቺን ልጅ አሟት።"

አየሽ ትናንትን በትውስታ ስጓዘው፣ ባለፈ እንጉርጉሮ ስመሰጥ፣ እነዚያን ውብ ሌሊቶች፣ ተቃቅፈን የተጓዝንባቸው ጎዳናዎች፣ አብሮ መብላት አብሮ ማደር፣ የሚናፈቅ መሽኮርመምሽ፣ ያ ውብ ሳቅሽ
ተራራሮችን ሰነጣጥቆ፣ ካለሽበት ሰማይ አድማስ ጥሶ ከሩቅ ማዶ ... እየመጣ ትዝታው ለኔ ሲሆን አንቺን አንቺን የሚያሰኘኝ ገራገርነትሽ ... በልቼ የጠገብኩ፣ ጠጥቼ የረካሁ የማይመስልሽ ... ሲከፋኝ የምታነቢልኝ፣ መጥፋቴ ሚጨንቅሽ ... የምሽት ህልሜ የለት ጉጉቴ የነበረሽ

ታስታውሺ እንደሆን መች እንደምንጋባ፣ ፣እነማን ሚዜ እንደሚሆኑን፣ ስንት ልጆች እንደሚኖሩን ... ካልረሳሽ ደግሞ አንቺ የበኩር ልጄ ሴት እንድትሆን እፈልጋለሁ ባልኩሽ ጊዜ ... ወንድ መሆን አለበት በማለት 1 ሳምንት ሙሉ ማኩረፍሽን... ... አቤት ኩርፊያሽ ... 1 ጋንታ ያስከፋል እኮ ... አንቺን ከኩርፊያሽ ለመለየት እንደ ደንበኛ የጠላት ምሽግ ልዩ ኦፕሬሽን ይጠይቃል።

ደሞ የቤተሰቦችሽ ሃይለኝነት ያባትሽማ ለጉድ እኮ ነው፣ በዛ ላይ በረባ ባልረባው ሄደሽ ምታቃጥሪው ነገር...
ተደራጅተው ሲመጡ ደሞ ለወሬ ነጋሪ አያስቀሩንም አብዛኛው የሰውነቴ ጠባሶች ይህን በሚገባ ያስረዱኛል።

ይኸው ዛሬም አንቺን ማሰብ ... የአድዋን ተራራ መውጣት ሆኖ ... ወደ ኋላ ይጎትተኛል። ከውሃው በላይ ጫወታሽ ጠማኝ፣ ከምግብ ይልቅ አይኖችሽን ተራብኩ፣ ... እረፍት አጣሁ። መለያየትን አንገት ለአንገት ተናነቅኩልሽ።

የኔ ውድ እያንዳንዱ ደብዳቤዎቼ ላይ ስንብቴም ተያይዞልሻል። ምናልባት ከተሰውት መሀል ልትመለከቺኝ ትችያለሽ፣ ወሬዬን ላትሰሚ ትችያለሽ፣ አርፏልም ሊሉሽ ይችላሉ። ከዚህ ደብዳቤ ጋር ያፅናናሽ ይሆን ብዬ ፎቶዎችን አንድ ላይ ደብዳቤው ውስጥ አስቀምጬልሻለሁ።
ቻው!


ያንቺው ምርኮኛ!

ከሰሜን ዕዝ 31ኛ ክ/ጦር
---- ----_

#share - @ethio_fiction