Get Mystery Box with random crypto!

የሳሚ ደብዳቤዎች ቀን: 15/08/2015 ዓ.ም #ርዕስ: የለውም #አዘጋጅ ፦ ሳምሶን ( | ልብወለድ Ethio_Fiction

የሳሚ ደብዳቤዎች

ቀን: 15/08/2015 ዓ.ም

#ርዕስ: የለውም

#አዘጋጅ ፦ ሳምሶን (channel Admin)

#ላኪ፦ ሔመን

#ተቀባይ: ዳንኤል

#የላኪ_አድራሻ: ደብረዘይት

#የተቀባይ_አድራሻ: ድሬድዋ

ውዴ ሆይ፣ ለዘመኔ ማብቂያ ላንተ ፍቅር መርሻ፣ ባንጠለጠልኩት መታነቂያ ገመድ ፊት የመጨረሻ ቃሌን በወረቀት አሰፈርኩልህ። ደብዳቤው ላይ፣ የስልክ ቁጥርህንና አድራሻህን ስለፃፍኩኝ: አስከሬን የሚያነሱ ሰዎች ያቀብሉሃል። ውዴ መለየቴ መርዶ አይሁንብህ:: እኔ እኮ በድን ከሆንኩኝ ድፍን 10ት አመታት ተቆጠሩ።  ያሳለፍናቸው ውብ ወቅቶች፣ ናፈቁኝ የምንቀመጥባቸው ድንጋዮች፣ ታወሱኝ እንጃልኝ እኔ .... የሆንኩትን አላውቅም የሆነውንም አላምንም ..።

አንዳንድ ጊዜ ውዴ ጫወታና ሳቅህ ባይኔ እየዋለለ፣ ብዙ ጊዜ ስቃዬን አሳየኝ ፣ አልቻልኩም ቸገረኝ፣ በነጋ በጣ በፊቴ ትመጣለህ፣ ድምፅህ በጆሮዬ እየተመላለሰ ያስተጋባል፣ አይ መከራዬ። ድንገት ተነስቼ በደካከሙ እግሮቼ መንገዱን እገፋዋለሁ። አንተ ወዳለህበት፣ አንተን ወደማገኝበት፣ እሄዳለሁ።

ይኸው የመንደሩ ሰዎች እየተጠቋቆሙ ልጅቷ ጨለለለች ነቀለች ይላሉ። ምንም አደለም ይሁን፣ ጨርቋንም ጥላለች ቀወሰች ይበሉ። ይሳሳቁብኝ ይዘባበቱብኝ። "ደሞ ምን ሆነሻል" ሲሉኝ በመውደድህ ቅዠት  የምናገረው እየጠፋኝ፣ ስርበተበት እንደህፃን ስኮላተፍ
ደሞ ከመንገዴ እቆምና ጥንዶች እየተሳሳቁ ሳይ ሆድ ይብሰኛል።
አይዞሽ ባይ በሌላት በትንሿ ጎጆዬ የዘመመ በሬን ዘግቼ አለቅሳለሁ ፣ እነዚያን የማይረሱ ዕለታት በምን ልተዋቸው?

ውዴ ሆይ መተው እኮ አቅቶኛል ... የምታዜምልኝን ዜማ እኮ አሁንም ይሰማኛል በተለይ ....
"አንቺ የእንጆሪ ፍሬ
ማዛሽ እያማረ
ከሾህ ሀረግ በቅለሽ
መውጫው አስቸገረ።" ይኸውልህ ልቤ ልክ እንደ እንጆሪዋ ፍሬ የኔም ህይወት መውጫው ጠፍቶታል የሃሳብ እሾህ ተሰክቶብኛል ዕድሜ ልኬን ታምሜ አለሁ። አንተ ሰው አታውቅም ብነግርህም አትረዳም።

ውይ ትዝታው ምንም የሚጣልና የሚረሳ አደለም፤ አሁንማ ምንያደርጋል አንተ የለኸኝም ቆሜ ዳርኩህ፤ እያረርኩኝ ሳቅኩልህ፣ እያነባው እልልልል አልኩኝ፣ ... በሀዘኔ ቀን ላንተ ነጭ ለበስኩ።
አሁን የመጨረሻ ቃሌን ሰጥቼሃለሁኝ፤
ከነልጅነት ንፁህና ሀቀኛ ፍቅሬ ተሰናበትኩህ በቀለበት ፋንታ ገመድ አጠለቅኩ አንተ እየበራልህ የእኔ ዘመን ጨለመ ታሪኬ አበቃልኝ እኮ መውደዴ ሜዳ ቀረ፣ ፍቅሬን ውሃ በላው።
ቻው ቻው!
ያንተ ደካማ ሴት!

(አንድ ሙዚቃ በሚሞሪ አድርጌ ደብዳቤው ውስጥ አስቀምጬልሃለሁኝ። የልጅነት ፎቶም ተያይዞልሃል።)

#ተፈፀመ

#Comment: @sam_lizu
      
   ---- ----

#share - @ethio_fiction