Get Mystery Box with random crypto!

ልብወለድ Ethio_Fiction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_fiction
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.31K
የሰርጥ መግለጫ

#ለሃሳብ_አስተያየት

Admins:- @sam_lizu

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-01-12 20:48:59 #የቀጠለ
በመሰረቱ ማንንም ማዋራት አይፈልግም። እቺኛዋ ልታወራው ስትሞክር ተቆጣት።
“መንገድ የተዘጋጋው ምን ሆኖ ነው?” ብላ የሆነ የወሬመግቢያ ልታመቻች ሞከረች።

“እኔ ምናውቃለሁ” ብሎ ለመክፈት የሞከረችውን ዘጋው። ወዲያው መልሶ ጸጸተው። ግን በትራንስፖርት ስራ ላይ ለጸጸት ጊዜ የለም። እሱ ማን እንደሆነ እንዲያውቁም ሆነ እነሱም ማን መሆናቸውን እንዲያሳውቁት አይፈልግም። እቺ ግን ጋጠ-ወጥ መሆኗን ጠርጥሯል። መጠርጠር የሚያስፈልግበት ሰዐት አይደለም። ገና አልመሸም። ከቀኑ ስምንት ሰዐት ተኩል ገደማ ነው። በቅርብ ነው እሱም ሱሰኝነቱን የተወው። ሲተው ያገኘው ነገር ጥላቻ ብቻ ነው። ሱሰኛ የመሰለውን ችክ ብሎ መጥላት። እርግጠኛ ነው ሱሰኛ መሆኗን የተጠራጠረው፣ ሴተኛ አዳሪ በሚመስለው አለባበሷ ነው።

ትንሽ እንደተጓዙ በስልኳ በከፈተችው ሙዚቃ የጠረጠረውን ስለመሆኗ እርግጠኛ ሆነ። አብራ ከሙዚቃው ጋር ታዜማለች። ድምጿ የጎረና ነው። በምሽት ቤቶች የማይጠፉ ሴቶች ላይ የሚያስታውሰው አይነት ድምጽ ነው ያላት፤ የጎረና። እግሯን አንፈራጣ ነው የተቀመጠችው። በማቀፊያ የተጠቀለለውን ህጻን በአግድም ጭኗ ላይ አጋድማዋለች። አያለቅስም። ጠረንም አያመነጭም። ህጻናት የሚያመነጩት ጠረን አለ። ይኸኛው የለውም። እናትየዋ ግን የማይረባ ሽቶ ተቀብታለች። በሃይል ይሰነፍጣል። የተጫማችው ጫማ ማንነቷን የበለጠ ያብራራል። ከስክስ ቡትስ ጫማ ነው::

  ወርቃማ ዘለበት እና ረጅም ለጃኬት የሚመጥን ዚፕ ያለው ቡትስ ጫማ ነው።  አፍንጫዋ ላይ ሁለቱን ቀዳዳዎች በሚለየው ስጋ ላይ ቀለበት አንጠልጥላለች። እንደ ፈረንጅ ከብት ቀለበቱን ይዞ የሚነዳት ሳይኖር አይቀርም- ብሎ አሰበ። ጆሮዋ ከአንድ በላይ ጌጥ በመደዳ ይዟል፤ ሊፒስቲክ ግን አልተቀባችም።
ያለሙዚቃ አንድ እርምጃ መንቀሳቀስ የማይችሉ  አይነት ሰዎች አሉ። የምትሰማው ሙዚቃ ሰው ጭፈራ ቤት ገብቶ ሲሰክርና ራሱን ሲረሳ ብቻ የሚሰማው አይነት ነው።

በቀን ከተከፈተ ከሽቶው ጋር ተደባልቆ የሚያጥወለውል። በቀን በራስ ፍላጎት ከፍቶ ያውም አራስ ህጻን ታቅፎ ለመስማት እንደሚመርጠው አያውቅም ነበር። ደግሞ አብራ ታዜማለች። አንዳንዱን ትደጋግመዋለች። ድግምቱ ከራሷ በስተቀር ለማንም ትርጉም  የሚሰጥ አይደለም።

#ከ50 like በኋላ #ይቀጥላል....
1.0K viewsሳ² lizu, 17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 20:48:41 #ርዕስ:- “እነ እሙጢ ጋ እየሄድኩኝ ነው”
#ደራሲ:- ሌሊሳ ግርማ

#ክፍል....1

  “ለዛሬ ይበቃኛል” ብሎ ወደ ሰፈር ሊያዞር ሲል አንድ ተጨማሪ ስራ መጣ። “ራይድ ነህ አይደል?” ብሎ ተጠግቶ ጠየቀው። አመኔታ የሚጣልበት አይነት ነው። ቦርጭ እና ቅላት አለው። በተለምዶ ካለ ጥሪ ተሳፈሪ አይጭንም።
“አዎ ነኝ” ከማለቱ “ጠብቃት ትመጣለች… ልጅ ይዛለች” አለው። “ጠሪ አክባሪ” የሚባለው አይነት መሆኑ ነው። የሚሄዱትን ራሱ ሳይሄድ የሚያገናኘው። ልጅቷ መጣች። ህጻኑን ይዛ ከኋላ ወንበር ተሳፈረች። ወደ ኋላ በሚያሳየው መስታወት ሲገመግማት እንዲሁ አልወደዳትም። ወደምትፈልግበት ከደረሰች በኋላ “የምከፍለው የለኝም” ብላ አይኗን ልታፈጥ የምትችለው አይነት ትመስላለች።

ብዙውን ጊዜ መጓጓዣውን ጠርቶ የሚያሳፍረው… ጉዞው ከመጀመሩ በፊት ይከፍላል። እንደ ቅርበቱ። ለተጓዡ እንደሚሰጠው አክብሮቱ። ብዙም ትውውቅ ያላቸው አይመስልም። በጎዳና ላይ ሲያልፍ “ራይድ ጥራልኝ” ብላው ተባብሯት ሊሆን ይችላል።
 ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ነገር በእጇ ታቅፋለች። ያመናት በታቀፈችው ህጻን ምክንያት ነው። የታቀፈችው ህጻን ከታቃፊዋ ወጣት በላይ ንጹህ ይመስላል። በነጭ መታቀፊያ ነው የተጠቀለለው። ብዙም ደስ ሳትለው ነው መኪናውን አስነስቶ ጉዞ የጀመረው።

አንድ ጊዜ ብቻ ወደ ኋላ አንገቱን አዙሮ በደንብ በአይኑ ከላይ እስከ ታች አዳርሷታል። ከሰላምታ በስተቀር ተሳፋሪን ማየት አይወድም። ዞሮ ማየት ሳያስፈልገው፣ ምን አይነት ሰው እንደተሳፈረ ያውቃል። አንዳንዶቹ ጠረናቸው ማንነታቸውን ይናገርላቸዋል። ሌሎቹ ዝምታቸው። ዝምታቸው የሆኑትን ሳይሆን ምን መስለው መቅረብ እንደሚሹ ይነግረዋል። ራሳቸውን ስለሚያከብሩ፣ መዋረድ ስለማይፈልጉ… የተጠየቁትን መክፈላቸው አይቀርም።
ከመነሳቱ በፊት መዳረሻዋን እና ስልክ ቁጥሯን ጠየቃት። ስልክ ቁጥርም የቁጥሩን ባለቤት ማንነት ለማሳየት ይጠቅማል። ተደብቆ ሰው ለመሳደብ የፈለገ ሰው፣ የሚደውልበት አይነት ቁጥር ነው። 0911 ወይንም ሁለት፣ ወይንም በአንድ ሶስት የሚጀምሩ አድራሻ ያላቸው ስልኮች ናቸው። ስልኳን ነገረችው እና ሞላው። ፈረሱ ስራውን ጀመረ።
1.0K viewsሳ² lizu, 17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 11:14:09
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ

#ሰላም

በጌታችን ልደት ለዓለም ሁሉ የሚሆን ዘላለማዊ ሰላም ተገኝቷል። ይህም <<ክብር ለእግዚአብሔር በሰማያት ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጐ ፈቃድ>> እያሉ ቅዱሳን መላእክት በመዘመራቸው ተረጋግጧል። ሉቃ 2፥14። ስለዚህ በክርስቶስ ያገኘነው እውነተኛ ሰላም በእኛ ጸንቶ እንዲኖር ዘወትር በጾምና በጸሎት እየተጋን ስለሰላም የምንማፀን ሆነን ልንገኝ ይገባል። ሰላም የክርስትና መታወቂያ አርማ ነውና።

#ብርሃን

<<በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃንን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።>> ኢሳ 9፥2። ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ያህል በዲያብሎስ ቁራኝነት ተይዞ የነበረው አዳም ወደሚደነቀው ብርሃን የተሸጋገረው በክርስቶስ ልደት ነው። እኛም በልደቱ ያገኘነውን የጽድቅ ብርሃን ጠብቀን ለመኖር (ብርሃነ ወንጌልን) ፈጽመን ከኃጢአት ርቀን በጽድቅ ሥራ ተወስነን ብርሃን ሆነን ልንኖር ይገባል።

#ፍቅር

ፍቅር ኃያል ወልድን ከዙፋኑ አወረደው እስከ ሞትም አደረሰው።
እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጅን በደል ሳይቆጥር በዙፋኑ ሆኖ ምሬሃለሁ ማለት ሲችል ፍቅሩን ይገለጽ ዘንድ በከብቶች በረት ተወለደ። እውነተኛ ፍቅሩ ለክርስትናችን መሠረት ለጽድቃችን ፋና እንደሆነ መጻሕፍት ያረጋግጣሉ።

መልካም የገና በዓል ይሁንልን አሜን።

ሁለቱ ቻናሎቼን Share እሺ
    ➷  
@ethio_fiction & @Fikr_Amargna
782 viewsሳ² lizu, 08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 13:50:02
እውነት ነው
ባንድ ወቅት ሳሚ እንዲህ ብሎኝ ነበር

"ካፍሽ የሚወጣውን ነገር ተጠንቀቂ! ሰው በጥይት ወይም በሰይፍ ብቻ አይደለም የሚወድቀው። ሰው በክፉ ንግግርም በቁሙ መቃብር ይወርዳል።

'አትግደል' የሚለው ትዕዛዝ የሰዎችን ስነ ልቦና እና ክብር በቃላት መግደልንም ይጨምራል። ሰውዬው ቆሞ ይኼዳል ግን 'ሞቷል'።

አንዳንዴ ሰዎች እንዲህ ብለው ሲናገሩ ሰምተሻቸው ይሆናል። 'እንዲህ ከምትለኝ ብትገለኝ ይሻለኝ ነበር።' ይህ እውነት ነው። በስድብና ቀናነት በጎደለው ንግግር ሰዎች በቁማቸው ይረሸናሉ፣ ውስብስብ የሆነ ስነልቦናዊ ቀውስ ውስጥ ይገባሉ፣ 'ይማርህ!' የማይባል በሽታ ይዘው የውሸት ኖረው የእውነት ይሞታሉ።

በክፉ ንግግር ስነልቦናን መግደል፣ የሌላውን እምነትና ሞራል መግፈፍ፣ ክብርና ማንነቱን ማኮሰስም ሆነ በሰይፍ አንገት መቅላት ወይም በጥይት ግንባርን መበጥረቅ ለኔ አንድ ናቸው።"
>>>
- - - - - - - - - - - - - - - - -
አንዳንዴ ከሳሚ ጋር
እና ሌሎችም
መንግሥቱ መርሃፅዮን
(ገፅ 93 - 94)

Share - @ethio_fiction
405 viewsሳ² lizu, 10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 22:04:57
  ሁለት ሰዎች ከሲጋራ ማጨስ ሲታቀቡ በዓይነ ሕሊናዎ ይመልከቱ ።

ሲጋራውን ሲጋበዙ  የመጀመሪያው ሰው

“ አይ አመሰግናለሁ ። እኔ ለማቆም እየሞከርኩ ነው ” ይላል ። ይህ ምክንያታዊ ምላሽ ይመስላል :: ነገር ግን ይህ ሰው አሁንም አጫሽ እንደሆነና ሌላ አይነት ሰው ለመሆን እየሞከረ እንደሆነ ነው የሚያምነው ። እንደዚህ ያሉ ሰዎች ተመሳሳይ እምነቶችን ይዘው ባህሪያቸው እንደሚለወጥ ተስፋ የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው ።

ሁለተኛው ሰው “ አይ አመሰግናለሁ ። እኔ አጫሽ አይደለሁም ” በማለት ሲጃራውን አይቀበልም። ከላይኛው ሰው ምላሽ ጋር ያለው ልዩነት ትንሽ ነው :: ምላሾቻቸው ግን የማንነት ለውጣቸውን ያሳያል።

ብዙ ሰዎች ለመሻሻል ሲነሱ የማንነት ለውጥን እምብዛም አያስተውሉትም ። ለድርጊቶቻቸው የሚያነሳሱ እምነቶችን ከግምት ሳያስገቡ ግቦችን ያስቀምጣሉ ፤ እንዲሁም ግቦቹን ለማሳካት መውሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች ይወስናሉ ። ነገር ግን እራሳቸውን የሚመለከቱበትን መንገድ በጭራሽ አይቀይሩም፤ የድሮው ማንነታቸው አዲሱን የመለወጥ ዕቅዳቸውን ሊያበላሽ እንደሚችል አይገነዘቡም ።

ከራስ ጋር የማይጣጣም ባህርይ አይቆይም። ምናልባት ብዙ ገንዘብ ይፈልጉ ይሆናል፣ ግን ማንነትዎ ገንዘብን ከማፍራት ይልቅ የሚያባክን አይነት ሰው ከሆነ ከማግኘት ይልቅ ወደ ማባከን መሳብዎን ይቀጥላሉ ። የተሻለ ጤንነት ይፈልጉ ይሆናል፣ ነገር ግን ከድርጊት ይልቅ ምቾትን ማስቀደምዎን ከቀጠሉ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከማድረግ ይልቅ ወደ ዘና ማለት ይሳባሉ። ወደ ቀድሞ ባህሪዎ የመሩዎትን መሰረታዊ እምነቶቸ ካልቀየሩ በስተቀር፣ መቼም ቢሆን ልምዶችዎን መቀየር ከባድ ነው፡፡

አዲስ ዓላማ እና አዲስ ዕቅድ ካለዎት ልክ ያልሆነውን አስተሳስብዎንና ማንነትዎን ቀድመው ይለውጡ :: 

Atomic Habits ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ
499 viewsሳ² lizu, 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 13:16:09
በትዕዛዙ ካሳ የተዘጋጀው " የትዳር ወግ " መጽሐፍ ለንባብ በቃ ::

ለመሆኑ ትዳር ምንድር ነው ? ስኬታማ ትዳር የነበራቸው ሰዎችስ ተግዳሮቱን እንዴት አለፉት ? አሸናፊ ያደረጋቸው ምሥጥርስ ምንድር ነው ? የሚሉ ጥያቄዎችን ማሰላሰል ከጀመርኩም ሰነባብቻለሁ :: የጨበጡትና በሩቁ የሚያውቁት ትዳር ለየቅል እየሆነባቸው ግራ የተጋቡ ሰዎችም ደጋግመው ያጋጥሙኛል ::

.... ሦስቱ ጉልቻ እንደ እሳት ዓምድ የሚያስፈራቸው ሰዎችስ ቁጥራቸው ስንት ይሆን ? እነዚህን ውስብስብ ጥያቄዎች እያውጠነጠንኩ በነበርኩበት ከሦስት ዓመት በፊት አንድ በጋብቻ ዙሪያ የተጠና ጥናት ተመለከትኩ ::

በአሜሪካ ሀገር ከሚጋቡ ጥንዶች መካከል እኩሌታው የሚሆኑት ፍቺ ፈጽመዋል :: ' ዕድላችንን እንሞክር ' ብለው ለሁለተኛ ጊዜ ወደትዳር ከገቡት መካከልም 60 በመቶ ዕጣቸው መፋትት ሆኗል ::

ከትዳር በፊት በደባልነት የሚኖሩ ጥንዶች ቁጥራቸው በየጊዜው እየጨመረ ሲሆን እነዚሁ ጥንዶች ከተጋቡ በኋላ የመፋታት ዕድላቸውም ሰፊ ሆኖ ታይቷል :: እንዲያውም ከሦስት ልጆች አንዱ እንዲህ ባለው ደባልነት ኑሮ የሚወለዱ ናቸው ::

በተጨማሪም እንዲህ ባለ ሰባራ ትዳር ያደጉ ልጆችም የመለያየት ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው ::
እኔም ስለትዳር የሚወጡ መረጃዎች ለምን እንዲህ አስደንጋጭ ሆኑ ?! በእኛ ሀገር ያለው ሁኔታስ በቁጥር ባይሰፈርም የችግሩ አሳሳቢነት ምን ያህል ይሆን ? የትዳር ፈተናስ ቀድሞውንም ይህን ያህል የበረታ ነበር ወይንስ ከዘመኑ ጋር እየጠነከረ መጣ ?! ለመሆኑ ይህ ትዳር የሚባል ነገር ምንድር ነው ?!ስኬታማ ትዳርን ለመምራት የተቻላቸው ሰዎችስ የአሸናፊነት ምስጥራቸው ምንድን ነው ?! "

@ethio_fiction
673 viewsሳ² lizu, 10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 14:21:49
#ርዕስ:- ዝም

ተጫዋች ሳቂታ ይቆይ እያላችሁ
ዝምታው ለምነው ሲሄድ እያያችሁ
ከደሃም ከደሃም እሱኮ ኩሩ ነው
ማጣት መንጣቱን በሳቅ የሸፈነው
ያ የልጅ አዋቂ
ያ ምስጢር ጠባቂ
አለው ብሎ ሄደ
መጣሁ ብሎ ካደ
ልባችን ተሰበር ሆዳችንም ባባ
ሲወጣ የናቅነው ላይመለስ ገባ ።

ገጣሚ:- ሳሚ (@sam_lizu) Admin
1.1K viewsሳ² lizu, 11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 14:03:55 Channel photo updated
11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 10:37:28
#አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በተለያዩ የሀገራችን ፊልሞች ላይ በድንቅ ብቃት በመተወን በተለይ ደግሞ በአሁኑ ወጣቶች ዘንድ እጅግ የሚወደደው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ለማረጋገጥ ተችሏል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) አርባ ያህል ፊልሞች ላይ የተወነ ሲሆን በህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ለማረጋገጥ መቻሉን አሳውቋል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበረ።

ቻናላችን የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን በቤተሰቦቿ ስም ታስተላልፋለች።

ነፍስ ይማር

@ethio_fiction
1.5K viewsሳ² lizu, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-18 17:21:05 ጠበኛ እውነቶች
ደራሲ:- ሜሪ ፈለቀ

"እናትሽ በጠና ታማለች። እባክሽ ልታይሽ ትፈልጋለች።"
ለአራተኛ ጊዜ የተላከልኝ መልዕክት ነው።

"እስካሁን አልሞተችም እንዴ? ለምን ታጓጓኛለች? አንዳችሁ እንኳን ምናለ ‘ሞተች’ የሚል ብስራት ብታሰሙኝ?"

"በስመ አብ ወ ወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ!! (ገዳዳ መስቀል በሰራ እጁ እያማተበ) ምነው ልጄ? ምን የሚሉት ጭካኔ ነው? ደግም አይደል! እግዜርም አይወደው።"

መልሴ አንገሽግሾታል። ሀምሳ ዓመት የሚያልፈው ሰውዬ ነው። የወለደችኝ ሴትዮ የነፍስ አባቷ ነው።

"በናትህ ከቤቴ ውጣልኝ!!"

"ምነው ልጄ? እግዜር የሰጠኝን ሹመት ባታከብሪ በእድሜ አባትሽ አልሆንም?" የሚናገረው ቃል የለዘበ ይሁን እንጂ ቀይ ወጥ የመሰለ ግለታም ዓይኑ እንደተጠየፈኝ ያሳብቅበታል።

እድሜውን ሳይሆን የለበሰውን የቤተ ክህነት ልብስ ባከብር ደስ ባለኝ ግን ለባሹ ልብሱን እንጂ ልብሱ ለባሹን እንዴት ሊያስከብረው ይችላል? ልብሱ ይሄን ከንቱ ሰውዬ እንዴት ክቡር ሊያደርገው ይችላል? መሆን የነበረበት ልብሱ ተገፎ ለተከበረ ሰው መደረብ ነበር። ያኔ ልብሱም ለባሹም ይከበራሉ።

መጎናፀፊያ አካልን ይሸፍን ይሆናል፤ ምናልባትም የአካል እንከንን የነፍስ ሴሰኝነት ግን በልብስ አይሸፈንም። ዝቃጭ ምግባር ግን ለቅድስና ሌት ተቀን ለሚታገሉ ልበ ብርቱዎች በተዘጋጀ መደረቢያ አይከለልም። በሱ ቤት እኔ ከእናቴ ጋር የሚሰራውን ብልግና አላውቅበትም። የናቴ ውሽማዋ ነው።

ይሄኔ በየመቅደሱ ‘ሰው የዘራውን ያጭዳል’ እያለ ይቦጠለቃል። እሱ ግን ያልዘራውን ለማጨድ በሰው እርሻ ይኳትናል።

ሴሰኝነትን እየዘራ መከበርን ለማጨድ ማጭድ ይስላል። ከንቱ!!

ይሄኔ ስንቶች ስንጥር ለምታክል በደላቸው ንሰሃን ሽተው ከፊቱ ሲመጡ ዋርካ የሚያክል ስድነቱን በብብቱ ሸሽጎ ልባቸው ለንሰሃ እንዲሰበር ዘክሯል። የዘቀጠ!! የእናቴን ጣር ላይ መሆን ሊነግሩኝ እንደመጡት ሶስቱ እሱም
እየተፀየፈኝ ቤቴን ለቆ ወጣ።

(ከመፅሃፉ ገፆች የተቆረሰ)

#share -----> @ethio_fiction

#comment ---> @Cr7_reunited
826 viewsCr 7, 14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ