Get Mystery Box with random crypto!

እውነት ነው ባንድ ወቅት ሳሚ እንዲህ ብሎኝ ነበር 'ካፍሽ የሚወጣውን ነገር ተጠንቀቂ! ሰው በጥ | ልብወለድ Ethio_Fiction

እውነት ነው
ባንድ ወቅት ሳሚ እንዲህ ብሎኝ ነበር

"ካፍሽ የሚወጣውን ነገር ተጠንቀቂ! ሰው በጥይት ወይም በሰይፍ ብቻ አይደለም የሚወድቀው። ሰው በክፉ ንግግርም በቁሙ መቃብር ይወርዳል።

'አትግደል' የሚለው ትዕዛዝ የሰዎችን ስነ ልቦና እና ክብር በቃላት መግደልንም ይጨምራል። ሰውዬው ቆሞ ይኼዳል ግን 'ሞቷል'።

አንዳንዴ ሰዎች እንዲህ ብለው ሲናገሩ ሰምተሻቸው ይሆናል። 'እንዲህ ከምትለኝ ብትገለኝ ይሻለኝ ነበር።' ይህ እውነት ነው። በስድብና ቀናነት በጎደለው ንግግር ሰዎች በቁማቸው ይረሸናሉ፣ ውስብስብ የሆነ ስነልቦናዊ ቀውስ ውስጥ ይገባሉ፣ 'ይማርህ!' የማይባል በሽታ ይዘው የውሸት ኖረው የእውነት ይሞታሉ።

በክፉ ንግግር ስነልቦናን መግደል፣ የሌላውን እምነትና ሞራል መግፈፍ፣ ክብርና ማንነቱን ማኮሰስም ሆነ በሰይፍ አንገት መቅላት ወይም በጥይት ግንባርን መበጥረቅ ለኔ አንድ ናቸው።"
>>>
- - - - - - - - - - - - - - - - -
አንዳንዴ ከሳሚ ጋር
እና ሌሎችም
መንግሥቱ መርሃፅዮን
(ገፅ 93 - 94)

Share - @ethio_fiction