Get Mystery Box with random crypto!

#የቀጠለ በመሰረቱ ማንንም ማዋራት አይፈልግም። እቺኛዋ ልታወራው ስትሞክር ተቆጣት። “መንገድ የተዘ | ልብወለድ Ethio_Fiction

#የቀጠለ
በመሰረቱ ማንንም ማዋራት አይፈልግም። እቺኛዋ ልታወራው ስትሞክር ተቆጣት።
“መንገድ የተዘጋጋው ምን ሆኖ ነው?” ብላ የሆነ የወሬመግቢያ ልታመቻች ሞከረች።

“እኔ ምናውቃለሁ” ብሎ ለመክፈት የሞከረችውን ዘጋው። ወዲያው መልሶ ጸጸተው። ግን በትራንስፖርት ስራ ላይ ለጸጸት ጊዜ የለም። እሱ ማን እንደሆነ እንዲያውቁም ሆነ እነሱም ማን መሆናቸውን እንዲያሳውቁት አይፈልግም። እቺ ግን ጋጠ-ወጥ መሆኗን ጠርጥሯል። መጠርጠር የሚያስፈልግበት ሰዐት አይደለም። ገና አልመሸም። ከቀኑ ስምንት ሰዐት ተኩል ገደማ ነው። በቅርብ ነው እሱም ሱሰኝነቱን የተወው። ሲተው ያገኘው ነገር ጥላቻ ብቻ ነው። ሱሰኛ የመሰለውን ችክ ብሎ መጥላት። እርግጠኛ ነው ሱሰኛ መሆኗን የተጠራጠረው፣ ሴተኛ አዳሪ በሚመስለው አለባበሷ ነው።

ትንሽ እንደተጓዙ በስልኳ በከፈተችው ሙዚቃ የጠረጠረውን ስለመሆኗ እርግጠኛ ሆነ። አብራ ከሙዚቃው ጋር ታዜማለች። ድምጿ የጎረና ነው። በምሽት ቤቶች የማይጠፉ ሴቶች ላይ የሚያስታውሰው አይነት ድምጽ ነው ያላት፤ የጎረና። እግሯን አንፈራጣ ነው የተቀመጠችው። በማቀፊያ የተጠቀለለውን ህጻን በአግድም ጭኗ ላይ አጋድማዋለች። አያለቅስም። ጠረንም አያመነጭም። ህጻናት የሚያመነጩት ጠረን አለ። ይኸኛው የለውም። እናትየዋ ግን የማይረባ ሽቶ ተቀብታለች። በሃይል ይሰነፍጣል። የተጫማችው ጫማ ማንነቷን የበለጠ ያብራራል። ከስክስ ቡትስ ጫማ ነው::

  ወርቃማ ዘለበት እና ረጅም ለጃኬት የሚመጥን ዚፕ ያለው ቡትስ ጫማ ነው።  አፍንጫዋ ላይ ሁለቱን ቀዳዳዎች በሚለየው ስጋ ላይ ቀለበት አንጠልጥላለች። እንደ ፈረንጅ ከብት ቀለበቱን ይዞ የሚነዳት ሳይኖር አይቀርም- ብሎ አሰበ። ጆሮዋ ከአንድ በላይ ጌጥ በመደዳ ይዟል፤ ሊፒስቲክ ግን አልተቀባችም።
ያለሙዚቃ አንድ እርምጃ መንቀሳቀስ የማይችሉ  አይነት ሰዎች አሉ። የምትሰማው ሙዚቃ ሰው ጭፈራ ቤት ገብቶ ሲሰክርና ራሱን ሲረሳ ብቻ የሚሰማው አይነት ነው።

በቀን ከተከፈተ ከሽቶው ጋር ተደባልቆ የሚያጥወለውል። በቀን በራስ ፍላጎት ከፍቶ ያውም አራስ ህጻን ታቅፎ ለመስማት እንደሚመርጠው አያውቅም ነበር። ደግሞ አብራ ታዜማለች። አንዳንዱን ትደጋግመዋለች። ድግምቱ ከራሷ በስተቀር ለማንም ትርጉም  የሚሰጥ አይደለም።

#ከ50 like በኋላ #ይቀጥላል....