Get Mystery Box with random crypto!

ልብወለድ Ethio_Fiction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_fiction
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.31K
የሰርጥ መግለጫ

#ለሃሳብ_አስተያየት

Admins:- @sam_lizu

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-02-12 01:34:21
#አስቸኳይ_ማሳሰቢያ

ቅዱስ ሲኖዶስ መንግሥት አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤ እንግልት እየተፈጸመባቸው ያሉት ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ፤ አገልግሎታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል ቢልም በኦሮሚያና በአዲስ አበባ አገልጋዮችን ሰባኪያንን  የሰንበት ትምሕርት ቤት እና የማኅበራት አባላትን የማሠሩ ሒደት እንደቀጠለ የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ።

#ሕገ_ወጡን ሹመት አልቀበልም በማለቷ ምክንያት በኦሮሚያ የጸጥታ ኃይሎች በተደረገው ግድያ ውድ ልጆቿን የገበረችው የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት መናገሻዋ ሻሸመኔ ዛሬም ብዙ ልጆች ትሥረውባታል እሥሩም ከወጣቶች ወደ ከተማዋ ባለሀብቶችና ሽማግሌዎች ተሸጋግሯል።

#በዛሬው_ዕለት በከተማዋ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ባለ ሀብቶች፣ የከተማዋ የተከበሩ ሽማግሌዎችና እጅግ ብዙ ወጣቶች ታሥረዋል።

#መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በምእመናን ላይ የደረሰውን ሞትና አካል ጉዳት ለመሸፋፈንና ተጠያቂ እንዳይኖር ለማድረግ የመንግሥት አካላት የሚመለከታቸውን ሰዎች ሁሉ ምንም እንዳይናገሩ ለማስገደድ እየሞከሩ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

#ምንጭ:- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መገናኛ
ብዙኀን አገልግሎት ስርጭት።
486 viewsCr 7, 22:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 00:50:17
#Update #እንዳይረሳ

#ቅዱስ ሲኖዶስ፤ " መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል " ብሏል።
513 viewsሳ² lizu, 21:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 14:19:10
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ መግለጫው ትላንት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በነበረው ውይይት ስለተደረሰበት ስምምነት አሳውቋል።

በዚህም ከመንግስት ጋር፦

- የጉዳት ሰለባ ለሆኑቱ መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንዲያደርግ፤

- አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤
እንግልት እየተፈጸመባቸው ያለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት፤ የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ አገልግልታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ
#ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ ለነገ እሁድ የተጠራው ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል።

በዚሁ እለትም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁለም በየአጥቢያው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ ምሕረት ላይ ባለመቅረት የተለመደውን የእለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፤ የጸሎት፣ የምሕላ እና የትምህርተ ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ ሥርዓት በማከናወን እንዲያሳልፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰላማዊ ሰልፉ ለተወሰኑ ቀናት እንዲተላለፍ የተደረገው የአቋም ለውጥ ተደርጎ አለመሆን በመግለፅ አስቀድማ ቤተ ክርስቲያኗ በሮቿን ለሰላም ክፍት በማድረግ ባስተላለፈችው ጥሪ እና በአስቀመጠችው ቀነ ገደብ መሠረት
በመንግሥት በኩል ወዲያውኑ ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት
በማሳየቱ ምክንያት መሆኑን አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ፤ " መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል " ብሏል።

#እግዚአብሔር ይመስገን!
914 viewsሳ² lizu, 11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 18:38:27
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መግለጫ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበረው ውይይት የቤተክርስቲያኗ ብዙ ጥያቄዎቿ እንደተመለሰላትና ነገ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ ዝርዝር እና ሰፊ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።
1.2K viewsሳ² lizu, 15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 21:11:00 ከድርሰትና ግጥሙ በተጨማሪ ቀልዱም ይቀጥል የምትሉ
306 viewsሳ² lizu, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 21:03:32 ለፈገግታ 1 ልጨምርላችሁ

ማምሻውን የጎረቤታችን ልጅ ድንገት ታማ ይዘናት ሄደን
ዶክተሩ "አንዴ ሱሪሽን ትንሽ ወለቅ አድርጊ ማበረታቻ ልወጋሽ ነው።" ሲላት ጊዜ
"መጀመሪያ አንተ አውልቅ አትልም መሰላችሁ።"
አይ አመል

Contact --- @sam_lizu

Share --- @ethio_fiction
382 viewsሳ² lizu, 18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 20:44:06 ሳሚ_channel Admin ኮሜዲነቴ ጀመረኝ
(Original ቀልደኛ ነኝ )

#1. ዛሬ የሆቴል ገብቼ መኝታ ቤቱ ኮሪደር ላይ ቆሜ "ሚስትህ መጣች" ብዬ ስጮህ
97 የሚሆኑ ወንዶች  ከመኝታ ክፍል እግሬ አውጪኝ አሉ። በቃ ነገም በየ ሆቴሎች እየዞርኩኝ አስበረግጋለሁ።
ይቺን ሃገር ማፅዳት ይኖርብናል

#2. ሃብታም አደለሁም ግን ትናንትና iphone፣ ውድ ሰአቴን እና የኪስ ቦርሳዬን
ጎዳና ላይ ለሚኖር ወጣት አበረከትኩለት።
የተሰማኝን ደስታ አትጠይቁኝ በተለይ ኪሱ ውስጥ ሳንጃውን ወደኪሱ ሲያስገባ
መልካምነት በቃላት አይገልፅም

#3. ጓደኞች ቴክኖሎጂ ተራቋል
ወደዚህ ቁጥር +251915997280 የአየር ሰዐት ስትልኩ ስልካችሁ ወደ ላፕቶፕነት ይቀየራል በተኑም ቢሆን ችግር የለውም ተብሏል።

#4. " ፍቅራችንን ለመታደግ ቢራ መጠጣትህን ብታቆም ይሻልሃል።"
" ሳስበው ለዚህ ጥያቄ አንድ በደሌ ያስፈልገዋል።"

#5.
(ባልና ሚስት ራት ላይ ዶሮ ወጥ እየተመገቡ)
ባል :- ላንቺ ታፋና መላላጫውን እየበላሽ ለእኔ የዶሮውን ጭንቅላት ብቻ ያቀረብሽው ምን ማለት ነው? ገንዘቤን ቆጥሬ የሰጠሁሽ ለዚህ ነው

ሚስት :- ተረጋጋ ውድ ሁልጊዜ የቤተሰቡ ራስ እኔ ነኝ ስለምትለን ነው እኮ

Contact --- @sam_lizu

Share --- @ethio_fiction
493 viewsሳ² lizu, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 19:35:48
በሕዝብ ፊት ንግግር ስታደርግ

ፍርሃትህን አትናገር

" የግል ፍርሃት የግል ስሜትህ ሆኖ እንዲቀር የማድረግ ኃላፊነት አለብህ :: ፍርሃትህን ለአድማጭ ስትናገር የአድማጮችህን ትኩረት ከመልህትህ ወደ ፍርሃትህ እያሸጋገርከው እንደሆነ ማወቅ አለብህ :: በተጨማሪም ፍርሃትህን በተናገርክ ጊዜ የአንተንም ትኩረት በመልህክትህና በአድማጮችህ ላይ መሆኑ ይቀርና በተደጋጋሚ ስለፍርሃትህ ማሰብ ትጀምራለህ :: ... "

" በሕዝብ ፊት የመናገር ክህሎት " አዲስ መጽሐፍ ::
#በብሩክ_ወልዴ

Share - @ethio_fiction
708 viewsሳ² lizu, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 16:25:16 Channel photo updated
13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 15:51:09
" ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤
እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ። " ማቴዎስ 3 ፥ 16 - 17

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደሳችሁ።

Share - @ethio_fiction
755 viewsሳ² lizu, 12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ