Get Mystery Box with random crypto!

#አስቸኳይ_ማሳሰቢያ ቅዱስ ሲኖዶስ መንግሥት አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤ እንግልት እየተፈጸመባቸው | ልብወለድ Ethio_Fiction

#አስቸኳይ_ማሳሰቢያ

ቅዱስ ሲኖዶስ መንግሥት አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤ እንግልት እየተፈጸመባቸው ያሉት ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ፤ አገልግሎታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል ቢልም በኦሮሚያና በአዲስ አበባ አገልጋዮችን ሰባኪያንን  የሰንበት ትምሕርት ቤት እና የማኅበራት አባላትን የማሠሩ ሒደት እንደቀጠለ የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ።

#ሕገ_ወጡን ሹመት አልቀበልም በማለቷ ምክንያት በኦሮሚያ የጸጥታ ኃይሎች በተደረገው ግድያ ውድ ልጆቿን የገበረችው የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት መናገሻዋ ሻሸመኔ ዛሬም ብዙ ልጆች ትሥረውባታል እሥሩም ከወጣቶች ወደ ከተማዋ ባለሀብቶችና ሽማግሌዎች ተሸጋግሯል።

#በዛሬው_ዕለት በከተማዋ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ባለ ሀብቶች፣ የከተማዋ የተከበሩ ሽማግሌዎችና እጅግ ብዙ ወጣቶች ታሥረዋል።

#መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በምእመናን ላይ የደረሰውን ሞትና አካል ጉዳት ለመሸፋፈንና ተጠያቂ እንዳይኖር ለማድረግ የመንግሥት አካላት የሚመለከታቸውን ሰዎች ሁሉ ምንም እንዳይናገሩ ለማስገደድ እየሞከሩ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

#ምንጭ:- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መገናኛ
ብዙኀን አገልግሎት ስርጭት።