Get Mystery Box with random crypto!

#Update ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ መግለጫው ትላንት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች ከፍተኛ | ልብወለድ Ethio_Fiction

#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ መግለጫው ትላንት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በነበረው ውይይት ስለተደረሰበት ስምምነት አሳውቋል።

በዚህም ከመንግስት ጋር፦

- የጉዳት ሰለባ ለሆኑቱ መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንዲያደርግ፤

- አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤
እንግልት እየተፈጸመባቸው ያለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት፤ የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ አገልግልታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ
#ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ ለነገ እሁድ የተጠራው ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል።

በዚሁ እለትም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁለም በየአጥቢያው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ ምሕረት ላይ ባለመቅረት የተለመደውን የእለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፤ የጸሎት፣ የምሕላ እና የትምህርተ ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ ሥርዓት በማከናወን እንዲያሳልፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰላማዊ ሰልፉ ለተወሰኑ ቀናት እንዲተላለፍ የተደረገው የአቋም ለውጥ ተደርጎ አለመሆን በመግለፅ አስቀድማ ቤተ ክርስቲያኗ በሮቿን ለሰላም ክፍት በማድረግ ባስተላለፈችው ጥሪ እና በአስቀመጠችው ቀነ ገደብ መሠረት
በመንግሥት በኩል ወዲያውኑ ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት
በማሳየቱ ምክንያት መሆኑን አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ፤ " መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል " ብሏል።

#እግዚአብሔር ይመስገን!