Get Mystery Box with random crypto!

ልብወለድ Ethio_Fiction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_fiction
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.31K
የሰርጥ መግለጫ

#ለሃሳብ_አስተያየት

Admins:- @sam_lizu

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-14 01:25:26
#ትዝታሽን_ለእኔ_ትዝታዬ_ለአንቺ

ሰዎች እየገዙና እያነበቡት ነው

እናንተስ ምን ትጠብቃላችሁ

#share @ethio_fiction
59 viewsሳ² lizu, 22:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 01:41:43 Channel photo updated
22:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 01:40:58
#የመፅሀፍ_ጥቆማ

" .. ለኔ ያ ቀን እንደ ህልም ነው የሚታየኝ :: አሌክስና ልጅቷ በደንብ ተላምደው ቆይተዋል :: የቆዩም ፍቅረኛሞች ናቸው :: እኔና አብይ ግን ገና ዛሬ ነው እንደዚህ ዓይነት ቦታ ላይ ስንገናኝ ::

ፈራሁ ::

ጠንካራ ልጅ ነበርኩ እኮ :: ከዳኒ አምልጫለሁ :: ወንድ ልጅን እኔ ልጫወትበትም ልቀልድበትም የምፈልግ ሴት እንጂ ተረትቼ ራሴን አልጋ ላይ አገኘዋለሁ ብዬ ለሰከንድም አስቤ አላውቅም ነበር :: ግራ ገባኝ አዲስ የሚያስጨንቅ የሚያስፈራ  ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት ተሰማኝ :: አብይ ግን ምን የተለየ ነገር ኖሮት ነው " እሺ " ብዬው እዚህ ድረስ እየተጎተትኩለት የመጣሁት ?!

ልቤ ይመታል !

ደረቴን ደገፍ አድርጌ ያዝኩት !

ልብስ ማውለቅም አስፈራኝ ::

እየሳመ የሆነ የማላውቀው ሰመመን ውስጥ ከተተኝ :: ከከንፈሮቹም ከሱም ማምለጥ አልቻልኩም :: ውስጤ አንድ የፈራው ነገር ነበረው :: የሰጠሁትን ደብዳቤ አንብቦት ይሆን ? አንብቦትስ ከሆነ ለምን ዝም አለ ? ለምንስ ስላሳለፍኩት የውስጤ ቁስል አንስቶ ሊያዋየኝ ወይም ሊኮንነኝ አልፈለገም ? አብይ ፍርሃቴ የገባው ይመስላል ዓይን ዓይኑን ሳየው እየሳመ ያጣድፈኛል ::  ....  "

ገጽ | 36
የሕይወት ጎዳና
በሕይወት ጥላሁን
የመጀመሪያ ዕትም
እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

#share - @ethio_fiction
651 viewsሳ² lizu, 22:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 16:01:31
355 viewsሳ² lizu, 13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 11:38:53
ትዝታሽን : ለእኔ ትዝታዬ : ለአንቺ
(ገዝታችሁ አንብቧት)
ደራሲ :- እሱባለው አበራ

"… እንድን ሰው በስብእናው ብርሃናዊነት በጣም ልትወጂው እንደምትችይ ሲገባሽ ያኔ መፍራት አለብሽ። ህልውናሽ ራስሽን በማፍቀር ላይ ሳይሆን ሌላን ሰው በፍጹም ልብ ከመውደድ ከተነሳ አደገኛ ነው።

አየሽ… ቢያጠፋም ብርሃን–ብርሃን ነው። አምርረሽ መጥላት አትችይም። ካለ እርሱ ሕይወትሽ ጨለማ እንደሆነ እንዲሰማሽ የማድረግ ትልቅ አቅም አለው።

… ብርሃንን መጥላት መቼ የዋዛ ሆኖ? እንደማፍቀሩ አይቀልም።
ከባድ ሥራውን ነው። ልብሽን ከመክፈትሽ በፊት ቅድሚያ ራስሽን ማፍቀር መማር አለብሽ።

ያለበለዚያ ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ ሆነሽ ቁጭ ነው። ሲበድሉሽ ለራስሽ አትቆሚም። ‘እሺ’ እንጂ ‘አይ’ አትዪም። ምርጫዎችሽና ሕልሞችሽ ይጨልማሉ። ብርሃንን ስለተጠጋሽ
ብርሃንን አትሆኚም። በሌላ ሰው ማንነት አትደምቂም። የራስሽን ጌጥነት መፈለግ አለብሽ።

ሰዎች በሚያነቡት ምንባብ፣ በሚያዩት ቅርጽ፣ በሚያደምጡት ድምፀት ውስጥ የማያቋርጥ የትርጉም ኀሰሳን ያደርጋሉ። ምክንታዊትን ይጠይቃሉ። ሕይወት ላይ ግን ‘ለምን እንዲህ ሆነ? ለምን እንዲያ አልሆነም?’ ብለን መጠየቅ አንችልም። ከአልተመለሱልን ጥያቄዎች ጋር
እንጓዛለን። ምክንያቱም ምድር ላይ የያዝነው ሕይወት እንጂ ተውኔት አይደለም።

#share - @ethio_fiction
1.1K viewsሳ² lizu, 08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 15:28:26
ተናግሮ ነበር

--- ፍርሃት አለኝ! እኔ እዚህ ሃገር ውስጥ... ተው ሌላውን(እነ አብይን) ስጋት ነበረኝ። ደም እንዲፈስ አልፈልግም። ታሪኬን ማቆሸሽ አልፈልግም።

➛ስጋት ነበረኝ ፍርሃት ነበረኝ...
እዚህ ሃገር ውስጥ እስካፍንጫው ድረስ ጥላቻ ... በጥላቻ ነበረ። ጥግ የደረሰ ጥላቻ ..

➛እነኚህ መፈናቀል ምናምን የምናለቸው ዝም ብለው እኮ የመጡ አይደሉም። ለዘመናት በጥላቻ ላይ ጥላቻ ድሪቶ ስንመግብ ነው የኖርነው።

➛ትውልዱን ጠላትህ የበዘበዘህ፣ የገደለህ፣ ጡትህን የቆረጠ፣ ዘርህን ያጠፋ እየተባለ እየተሰበከ በዚህ እየተሞላ ነው የኖረው ትውልዱ።

➛በሰውነቱ ሰው መሆኑን እስኪክድ ድረ፣ ገዳይ አስገዳይ ሆኖ እንዲተያይ፣ ጠላት ሆኖ እንዲተያይ፣ ሲጫንበት ነው የኖረው።

➛በተለይ በአማራና በኦሮሞ መካከል ተደርጎ የተተከለው ተክል ቀላል አይደለም። መርዙ ቀላል አይደለም። አሳስቦኛል ይህን ጉዳይ መልክ ካልቀየርን ኢንቫይሮመንቱን ካልቀየርን የሺዎች ነፍስ ይጠፋል፣ ደም ይፈሳል፣ ሌላ ሯንዳ እዚህ ይከሰታል።

➛እኔ እሱ ነው አስሩጦ የወሰደኝ።
ዛሬ ኢትዮጵያዊነት ያዋጣናል፣ አንድነት ያወጣናል ብዬ መስበኬ መናገሬ ለዛ መስራቴ ኃጢያትነቱ ምኑ ጋር ነው? መገንጠል አለብን ማለት ነው እንዴ የነበረብኝ።

➛እሱ ነው መፍትሄው? ለኔ ወንጀል የሚሆነው ጥፋት የሚሆነው
ለኦሮሞ ጠቅሜ ሌላውን ጎድቼ ብሆን፣
ኦሮሞ ሲገባ ሌላው እንዲወጣ ተደርጎ ከሆነ ይህ ኃጥያትም ነው ወንጀልም ነው!

➛አላደረግንም ህሊናዬ እስከሚያቅ ድረስ ሰውን በሰውነቱ ነው የማየው እኔ በግሌ በማንነቱ አይደለም።

#አቶ ለማ_መገርሳ !

➛ዛሬ ለማን በቅንነቱና ንፁህ ህሊናው ጠልተውት፣ አሸሹት።

#Share - @ethio_fiction
729 viewsሳ² lizu, 12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 00:45:25
(ፎቶ: ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ)

ገጣሚ : ሳሚ ቻናል Admin

#እሺ_በይኝና
.
.
እጦት ስላለብኝ
ሳይሽ የሚፀና ያይን ፍቅር ጥማት
የኔ አለም...
ደረትሽ ላይ ባለው
ባንገት ማህተብሽ ጉንጭሽን ልሳመው


Share ----> @ethio_fiction
415 viewsሳ² lizu, 21:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 12:55:36 ልብወለድ Ethio_Fiction pinned « .........የሳሚ ደብዳቤዎች........ ክፍል....1 ቀን 7/05/1997ዓ.ም ፀኃፊ: ሳምሶን (የቻናሉ Admin) ላኪ: ሳሚ ተቀባይ: ራሂ (የላኩልሽን ደብዳቤ ሌሊት ተነስተሽ እንድታነቢ በማሳሰብ ፃፍኩልሽ) በተወደዱ ፊደላትና በተዋቡ ቀለማት በልቤ ብራና ላይ የሳልኩት መልክሽን እንዳላስታውስ አድርጌ ያጠፋሁት መስሎኝ ነበር ። ይኸው ዛሬም መንግስታትን…»
09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 12:55:12 ቤተሰብ ምልክቷን ተጫኗት
843 viewsሳ² lizu, 09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 12:39:40 .........የሳሚ ደብዳቤዎች........

ክፍል....1
ቀን 7/05/1997ዓ.ም

ፀኃፊ: ሳምሶን (የቻናሉ Admin)

ላኪ: ሳሚ
ተቀባይ: ራሂ

(የላኩልሽን ደብዳቤ ሌሊት ተነስተሽ እንድታነቢ በማሳሰብ ፃፍኩልሽ)

በተወደዱ ፊደላትና በተዋቡ ቀለማት
በልቤ ብራና ላይ የሳልኩት መልክሽን እንዳላስታውስ አድርጌ ያጠፋሁት መስሎኝ ነበር ። ይኸው ዛሬም መንግስታትን አየዘለለ ... ከብዙ ዓውደ ዓመቶች በኋላም እያንዳንዷን ሌሊት አንቺን ሳላሰላስል እነዚያን ምርጥ ቀኖች ያላንቺ እንደማላነጋ ... የሚወድሽ ልቤ አፅናኝ የራቃት ነፍሴ ... ትንገርሽ። በእነዛ ምትሃተኛ ቃላት እየቀመምኩ ስፅፍልሽ የነበሩ በጉጉት የምትጠብቂያቸው
ግጥሞች ትዝ ይሉሻል ... ?

እኔ ምልሽ ቃላቱ እንዴት እንደሚፈበረኩልኝ እስከዛሬ ግራ እጋባለሁ። በስሜት ያስሩኛል ... በተመስጦ የማልረግጠው ስፍራ አልነበረም... ከሰው ጋርም ሆኜ ብቻዬን ነኝ ግን አንቺ የቃላት ምንጬ እንደሆንሽ ታውቂ ነበር?

ይልቁኑ እኔን ስትጠሪኝ በሙሉ ስሜ አልነበረም። "ሳዬ" ነበር የምትይኝ ከዛም አልፎ "ሳ" ትይኛለሽ። ቆይ ግን "ስሜን እንደዛ የምታሳጥሪልኝ ለምን ይሆን?" ብዬ ስጠይቅሽ "ጊዜው ሲደርስ እነግርሃለሁ።" አልሺኝ። ጊዜው ስላለፈ
ደብዳቤዬ እንደደረሰሽ ምክንያትሽን በመልዕክተኛ ፅፈሽ በቶሎ ብትልኪልኝ ደስታዬ ወደር አልባ ይሆናል።

ደግሞ ያንቺ ጦስ የማያመጣብኝ ጣጣ የለም ... በቫላንታይን ሰሞን ... የገጠመኝን ላጫውትሽ ... ነገርግን አብዝተሽ መሳቅም ሆነ ማዘን አልፈቀድኩልሽም

ማምሻዬን ከስራ በመውጣት እግሬ እንዳመራኝ በከተማው መሀል ካለ ካፌ ውስጥ ጎራ አልኩኝ። ቤቱ በደማቅ እና የተለያዩ ቀለማትን በሚተፉ መብራቶች አጊጧል። ለናቷም ላባቷ የቀረች የምትመስል ቦታ አገኘሁና ወንበር ስቤ አረፍ አልኩኝ። ከእኔ በቀር ሁሉም ማለት ይቻላል ጥንድ ጥንድ ሆነው፣ አፍለአፍ ገጥመው ካፌውን አድምቀውታል። ለሰርግ የተጠሩ ሚዜዎች ይመስላሉ እንደውም ሙሽራው የታል እንድል አስገደዱኝ።

በነገሩ በመገረሜ ያዘዝኳትን ያመጣችልኝን ቀጭን አስተናጋጅ "የኔ እህት ሲንግሎች የት እንሂድ?" ብዬ ብጠይቃት። ብርጭቆዎቹን እያስቀመጠች በፈገግታ " እስቲ ከበስተኋላህ ዞር ብለህ ዕድልህን ሞክር።" ብላኝ ሂሳብ ሂሳብ ወደ ሚሏት ሰዎች ተፈተለከች። "ሲምቢሮ!" አልኳት በሆዴ።

አፍታ እንደቆየሁ የመጣልኝን የብርቱካን ሻይ ፉት አልኩና ሁኔታው ከንክኖኝ ከበስተኋላዬ ገልመጥ ሳደርግ እንደመደንገጥም እንደመሳቅም ያደረገችኝን አንቺን መሳይ ቆንጆ በኩራት ሆና አየሁ። ያውም ከዚህ ቀደም ሰርግ ላይ ሆነሽ የተነሳሽው ፎቶ ላይ የለበስሽውን ቀሚስ ራሱን ለብሳለች።

ልጂት እንዳየችኝ ምንም ሳይመስላት ስልኳን አንስታ መነካካት ቀጠለች። "አይ ዕድሌ ሲምቢሮ! ታይቷታል" በውስጤ ፈገግኩኝ። "ዛሬማ የቃላት ጥይት ያልቃል እንጂ አንላቀቃትም ዛሬማ ድባቅ መምታት አለብኝ።" ራሴን አጀገንኩት።

ከወንበሬ በዝግታ ተነሳሁ ፊቴን ወደ ኮራችው ውብ ልጅ ትይዩ አስተካከልኩኝ። ደሞ ሃይ ኮፒሽ እኮ ናት። አቤት መመሳሰል "ለሴት ልጅ ጀርባ አይሰጥም በሚል ብሒል ነው ወንበሬን ወዳንቺ ያዞርኩት።" አልኳት የልቤን መደለቅ ለመሸሸግ ጉሮሮዬን እየሳልኩ።

"ካልተሳሳትኩ ሙሽራዋ አንቺ ነሽ ።" አየኋት የልቧን ተራሮች ከናድኩት በሚል ፈገግታ።

" ታውቀኛለህ!?" ተኮሳተረች ።

" እሱን በሂደት " ዙሩን አከረርኩት።
ፊቷ መቅላት ጀመረ ... ድል በጠላት አቅጣጫ እያሽቃበጠች ሄደች...
አጠገቧ ለመቀመጥ እያኮበከብኩ የመጨረሻውን መድፍ ተኮስኩኝ።

"ብቻሽን ነሽ ማለት.. " አላስጨረሰችኝም።

"አፍህን ዝጋ! ደፋር!" ጮኸኝ።

ውሃ በላኝ ... ከባድ መኪና እየሄደብኝ ያህል ተሰማኝ በዙርያዬ ያሉ አፋቸውን ይዘው መሳቅ ጀመሩ።

ወረረኝ!

አቀረቀርኩ!

ባቀረቀርኩበት ....

"ወይኔ ሳዬ የኔ ናፍቆት..."

መብረቅ የሆነብኝን ድምፅ ሰማሁ ... ስድቧ ፕራንክ መሆን አለበት ማለት ነው። ተስለመለምኩ ተሽኮረመምኩ ... በደስታ ጨበስኩኝ አይ ራሂ ለኔ ብላ ካዲስ አበባ መጣች ውስጤን ማመን አልቻልኩም።
በፈገግታ ቆማለች፤ ተከትያት ቆምኩኝ።

አንድ ግዙፍ ለመሬት የከበደ ሰው ጥቁር አምባሳደር በነጭ ሸሚዝ የለበሰ ሽክ ብሎ ከበስተኋላዬ ወደ እርሷ ጎምለል ጎምለል እያለ መጥቶ ተጠመጠመባት።
እግዚኦ!

ቆሜ ቀረሁ!

ተቀመጥኩኝ
ዳግም አቀረቀርኩ ባቀረቀርኩበት ህመሜ ተነሳ .... ውድ ራሂ ስከፋም ስደሰትም ሙሉ ነገሬን በግጥም መግለፄን ላንቺ ማውጋት ለቀባሪ እንደማርዳት እንደሆነ የታመነ ነው።

ግጥም ግጠም አለኝ ....
ወረቀት አወጣሁ ... "ደግሞ ለጥቂት ሰንኝ ወረቀት ላውጣ አዎን ያው ይሁን እሺ።" ከገዛ ራሴ ጋር ንግግር ቀጠልኩ።
ማበዴ ነው አለች ዘፋኟ።

መፃፍ ጀመርኩ ...
ከንቱ ዕድሌ ጠማ ፊት አዙር ብላኝ
አይቀጡ ተቀጣሁ ፊት አዙሬ ብገኝ
ቀጠልኩ...
ስም ያለው ሞኛሞኝ እንኳንም ተሞኘ
እበላለሁ ብሎ ሲበላ ተገኘ
ቀጠልኩ... ➷(በ ይጠብቃል)
ማን አፍቅር አለው
ማን ውደድ አለው
ይፃፍ ይጫር እንጂ ገጣሚ ምናባቱ
ጨለማ ናት ሚስቱ ምሽግ ናት እቤቱ።

ሂሳቤን ከፍዬ መልሴን ሳልጠብቅ ተፈተለኩ! አይ ዕዳዬ

ያንቺው ሳ!

ቸር ያገናኘን!
ከሰላምታ ጋር
~ተፈፀመ~

ቀጣይ ፅሁፎቼን እንዲደርሳችሁ
ይቺን ተጫኑልኝ

Share ---> @ethio_fiction
934 viewsሳ² lizu, 09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ