#የመፅሀፍ_ጥቆማ
" .. ለኔ ያ ቀን እንደ ህልም ነው የሚታየኝ :: አሌክስና ልጅቷ በደንብ ተላምደው ቆይተዋል :: የቆዩም ፍቅረኛሞች ናቸው :: እኔና አብይ ግን ገና ዛሬ ነው እንደዚህ ዓይነት ቦታ ላይ ስንገናኝ ::
ፈራሁ ::
ጠንካራ ልጅ ነበርኩ እኮ :: ከዳኒ አምልጫለሁ :: ወንድ ልጅን እኔ ልጫወትበትም ልቀልድበትም የምፈልግ ሴት እንጂ ተረትቼ ራሴን አልጋ ላይ አገኘዋለሁ ብዬ ለሰከንድም አስቤ አላውቅም ነበር :: ግራ ገባኝ አዲስ የሚያስጨንቅ የሚያስፈራ ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት ተሰማኝ :: አብይ ግን ምን የተለየ ነገር ኖሮት ነው " እሺ " ብዬው እዚህ ድረስ እየተጎተትኩለት የመጣሁት ?!
ልቤ ይመታል !
ደረቴን ደገፍ አድርጌ ያዝኩት !
ልብስ ማውለቅም አስፈራኝ ::
እየሳመ የሆነ የማላውቀው ሰመመን ውስጥ ከተተኝ :: ከከንፈሮቹም ከሱም ማምለጥ አልቻልኩም :: ውስጤ አንድ የፈራው ነገር ነበረው :: የሰጠሁትን ደብዳቤ አንብቦት ይሆን ? አንብቦትስ ከሆነ ለምን ዝም አለ ? ለምንስ ስላሳለፍኩት የውስጤ ቁስል አንስቶ ሊያዋየኝ ወይም ሊኮንነኝ አልፈለገም ? አብይ ፍርሃቴ የገባው ይመስላል ዓይን ዓይኑን ሳየው እየሳመ ያጣድፈኛል :: .... "
ገጽ | 36
የሕይወት ጎዳና
በሕይወት ጥላሁን
የመጀመሪያ ዕትም
እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
#share - @ethio_fiction