Get Mystery Box with random crypto!

ትዝታሽን : ለእኔ ትዝታዬ : ለአንቺ (ገዝታችሁ አንብቧት) ደራሲ :- እሱባለው አበራ | ልብወለድ Ethio_Fiction

ትዝታሽን : ለእኔ ትዝታዬ : ለአንቺ
(ገዝታችሁ አንብቧት)
ደራሲ :- እሱባለው አበራ

"… እንድን ሰው በስብእናው ብርሃናዊነት በጣም ልትወጂው እንደምትችይ ሲገባሽ ያኔ መፍራት አለብሽ። ህልውናሽ ራስሽን በማፍቀር ላይ ሳይሆን ሌላን ሰው በፍጹም ልብ ከመውደድ ከተነሳ አደገኛ ነው።

አየሽ… ቢያጠፋም ብርሃን–ብርሃን ነው። አምርረሽ መጥላት አትችይም። ካለ እርሱ ሕይወትሽ ጨለማ እንደሆነ እንዲሰማሽ የማድረግ ትልቅ አቅም አለው።

… ብርሃንን መጥላት መቼ የዋዛ ሆኖ? እንደማፍቀሩ አይቀልም።
ከባድ ሥራውን ነው። ልብሽን ከመክፈትሽ በፊት ቅድሚያ ራስሽን ማፍቀር መማር አለብሽ።

ያለበለዚያ ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ ሆነሽ ቁጭ ነው። ሲበድሉሽ ለራስሽ አትቆሚም። ‘እሺ’ እንጂ ‘አይ’ አትዪም። ምርጫዎችሽና ሕልሞችሽ ይጨልማሉ። ብርሃንን ስለተጠጋሽ
ብርሃንን አትሆኚም። በሌላ ሰው ማንነት አትደምቂም። የራስሽን ጌጥነት መፈለግ አለብሽ።

ሰዎች በሚያነቡት ምንባብ፣ በሚያዩት ቅርጽ፣ በሚያደምጡት ድምፀት ውስጥ የማያቋርጥ የትርጉም ኀሰሳን ያደርጋሉ። ምክንታዊትን ይጠይቃሉ። ሕይወት ላይ ግን ‘ለምን እንዲህ ሆነ? ለምን እንዲያ አልሆነም?’ ብለን መጠየቅ አንችልም። ከአልተመለሱልን ጥያቄዎች ጋር
እንጓዛለን። ምክንያቱም ምድር ላይ የያዝነው ሕይወት እንጂ ተውኔት አይደለም።

#share - @ethio_fiction