Get Mystery Box with random crypto!

ተናግሮ ነበር --- ፍርሃት አለኝ! እኔ እዚህ ሃገር ውስጥ... ተው ሌላውን(እነ አብይን | ልብወለድ Ethio_Fiction

ተናግሮ ነበር

--- ፍርሃት አለኝ! እኔ እዚህ ሃገር ውስጥ... ተው ሌላውን(እነ አብይን) ስጋት ነበረኝ። ደም እንዲፈስ አልፈልግም። ታሪኬን ማቆሸሽ አልፈልግም።

➛ስጋት ነበረኝ ፍርሃት ነበረኝ...
እዚህ ሃገር ውስጥ እስካፍንጫው ድረስ ጥላቻ ... በጥላቻ ነበረ። ጥግ የደረሰ ጥላቻ ..

➛እነኚህ መፈናቀል ምናምን የምናለቸው ዝም ብለው እኮ የመጡ አይደሉም። ለዘመናት በጥላቻ ላይ ጥላቻ ድሪቶ ስንመግብ ነው የኖርነው።

➛ትውልዱን ጠላትህ የበዘበዘህ፣ የገደለህ፣ ጡትህን የቆረጠ፣ ዘርህን ያጠፋ እየተባለ እየተሰበከ በዚህ እየተሞላ ነው የኖረው ትውልዱ።

➛በሰውነቱ ሰው መሆኑን እስኪክድ ድረ፣ ገዳይ አስገዳይ ሆኖ እንዲተያይ፣ ጠላት ሆኖ እንዲተያይ፣ ሲጫንበት ነው የኖረው።

➛በተለይ በአማራና በኦሮሞ መካከል ተደርጎ የተተከለው ተክል ቀላል አይደለም። መርዙ ቀላል አይደለም። አሳስቦኛል ይህን ጉዳይ መልክ ካልቀየርን ኢንቫይሮመንቱን ካልቀየርን የሺዎች ነፍስ ይጠፋል፣ ደም ይፈሳል፣ ሌላ ሯንዳ እዚህ ይከሰታል።

➛እኔ እሱ ነው አስሩጦ የወሰደኝ።
ዛሬ ኢትዮጵያዊነት ያዋጣናል፣ አንድነት ያወጣናል ብዬ መስበኬ መናገሬ ለዛ መስራቴ ኃጢያትነቱ ምኑ ጋር ነው? መገንጠል አለብን ማለት ነው እንዴ የነበረብኝ።

➛እሱ ነው መፍትሄው? ለኔ ወንጀል የሚሆነው ጥፋት የሚሆነው
ለኦሮሞ ጠቅሜ ሌላውን ጎድቼ ብሆን፣
ኦሮሞ ሲገባ ሌላው እንዲወጣ ተደርጎ ከሆነ ይህ ኃጥያትም ነው ወንጀልም ነው!

➛አላደረግንም ህሊናዬ እስከሚያቅ ድረስ ሰውን በሰውነቱ ነው የማየው እኔ በግሌ በማንነቱ አይደለም።

#አቶ ለማ_መገርሳ !

➛ዛሬ ለማን በቅንነቱና ንፁህ ህሊናው ጠልተውት፣ አሸሹት።

#Share - @ethio_fiction