Get Mystery Box with random crypto!

ልብወለድ Ethio_Fiction

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_fiction — ልብወለድ Ethio_Fiction
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_fiction
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.31K
የሰርጥ መግለጫ

#ለሃሳብ_አስተያየት

Admins:- @sam_lizu

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-01-14 21:11:11 “እኔ ስራ አለኝ እንጂ ሌላ ምን አለኝ” ብሎ የንቀቱን አቅጣጫ ወደ ራሱ መለሰው። አንድ የሚንቀው ነገር ሁሌ በቅርብ ያስፈልገዋል። መጀመሪያ ተሳፋሪዋን ነበረ። ቀጥሎ ደግሞ እሷ በለቅሶ እና ለእሱ በጥቂቱ ባሳየችው አሳቢነቷ፣ እሷን አክብሮ ራሱን አርክሶ ቁጭ አለ።
“እሷ ባል አላት … እኔ ሚስት የለኝም።  እሷ ልጅ አላት…እኔ ልጅም በህይወቴ ላይ በቅርብ ርቀት አይታየኝም። ልጅነቴንም በፍጥነት አጥቻለሁኝ። ድንገት ከመሬት ተነስታ ከበረችብኝ እያለ አሰበ። ወደ ታች መውረድ ቀጠልን። መንገዱ ወደ ሁለት እንደሚሰነጠቅ ረስቷል። ሁለተኛውን ቅያስ ማንም የሚጠቀመው የለም። በታች የሚሄደውን ማንም የሚያዘወትረውን ቅያስ እንዲይዝላት ደጋግማ አስጠነቀቀችው። ቆሻሻው መንገድ ነው፡፡

የሀይላንድ ፕላስቲክ በአንድ ላይ ተከማችቶ በዚህ ቅያስ ጥጋጥግ ላይ ተከምሯል። የቆሻሻው መግፊያ ጋሪዎች ተደርድረው ክብደታቸውን ወደ ፊት ዘንበል አድርገው ቆመዋል። ቆሻሻ ገንዳ ያለበት አካባቢ የተለመደ እይታ ነው። ከቆሻሻ ገንዳው ትንሽ ፈቀቅ ብሎ የላስቲክ ቤቶች አሉ። ሁለት ሊሆኑም ብዙ ሊሆኑም ይችላሉ፡፡ ከተነሳችበት የዛ አይነት ርቀት የመጣችው ለዚህ መዳረሻ ይሆናል ብሎ ፈፅሞ አልጠረጠረም፡፡
መኪናውን ዳሩ ላይ ከላስቲኩ ቤት አጠገብ አቆመ።  እነ እሙጢ መአት ሆነው እየተሯሯጡ ወጡ። አንድ ጥርሷ የጎደላት፣ ያልጎደሉት ደግሞ ተዛንፈው የተበላሹባት፣ ትንሽ ከሌሎች በእድሜ ከፍ የምትለው ሴትዮ ልትሆን ትችላለች፤ እሙጢ፡፡ ደጋግማ በሥሟ ጠራቻትና ታቅፋ የቆየችውን ነገር ተቀበለቻት። እሙጢ በአስተቃቀፏ እንደዛ አይነት ህጻን ለመታቀፍ የመጀመሪያዋ እንዳልሆነ ግልፅ ነበር፡፡

ከበው ተቀበሏት፤ ወደ ላስቲክ ቤታቸው አጅበው አስገቧት። ከማስገባታቸው በፊት ግን የጉዞ ተመኑን ጠይቃ ለሾፌሩ ከፍላዋለች። አልቀበልም ብሎ ለመግደርደርም አልተመቸውም። የናቃት እንዳይመስል ተመኑን በልኩ ወሰደ። ቲፑን ግን እንቢ አለ።  ሊያዝንላት የጀመረው ሰው፣ በተቃራኒው አዝናለት ጨምድዳ አስጨበጠችው፡፡
የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ቤት አጅበዋት እስኪገቡ ድረስ እንደ ሰላይ በጥንቃቄ ተከታትሎ፣ ለመሄድ ተነሳ። በእሙጢ ስም ፋንታ የእሷን የእናትየውን ቢያውቀው የበለጠ ደስ ይለው እንደነበር እያሰበ ጎዳናውን ተያያዘው፡፡

#ተፈፀመ
በድርሰቱ ላይ ያላችሁን ሃሳብና አስተያየት
በአስተያየት መስጫው ይግለፁልን

Share - @ethio_fiction

Comment -
@sam_lizu
471 viewsሳ² lizu, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 21:11:11 #ርዕስ:- “እነ እሙጢ ጋ እየሄድኩኝ ነው”

#ደራሲ:- ሌሊሳ ግርማ

#የመጨረሻ_ክፍል

ለመድረስ ብዙ ይቀራቸዋል። ሃያ ሁለት መጀመሪያ… ከዛ በቅዱስ ጊዮርጊስ ሆስፒታል ቁልቁል ወደ ሀያ አራት…።
በእሷ በኩል እንጂ በስልክ በሚያናግራት ወንድ በኩል ለለቅሶዋ ምን ምላሽ እንደቀረበ መስማት አይችልም። ጥቅሉ ነገር ይገባዋል። ጥቅሉ ነገር ልጁን  ይዛባት እሙጢ ጋ እንድትሄድ አለመፈለጉ ብቻ ነው፡፡ ለማባበያ ምን አይነት ምክንያት እንደደረደረ ወይንም የተጠቀመው ብልሀት አድብቶ ለሚያደምጠው ሾፌር ባይገለጥለትም… የእናትየዋን የጉዞ  አቅጣጫ ግን ሊለውጠው አልቻለም፡፡   
“ወደመጣንበት ልመለስ…” ብሎ መጠየቅ የእርጎ ዝንብነት ነው። በራሱ ጭንቅላት በሰራው ካርታ እነ እሙጢ የሚወክሉት የቀድሞ ህይወቷን ነው። ሲ.ኤም.ሲ የሚባል የሀብታም ሰፈር ልጅ ታቅፋ ከመቀመጧ በፊት ለምዳ የኖረችውን የቀድሞ ታሪኳን--- አለባበሷን አልቀየረውም፤ አዲሱ ህይወቷ፡፡ በጉዞ ለመመለስ የተሳፈረችበት አቅጣጫ በምትሰማው ሙዚቃ ውስጥ ቁልጭ ብሎ ሾፌሩን ታየው።

የልጁ አባት ላይ በስልክ አልጮኸችም። ወቀሰችው እንጂ አልኮነነችውም።  የደወለው አባትዬው መሆኑ እርግጥ ነው። በስራ ምክንያት ራቅ ያለ ይመስላል፡፡ የመሰለ ሁሉ ግን ነው ማለት አይቻልም፡፡ በስሜቱ ማሰብ ከጀመረ በቀላሉ ሊጭበረበር እንደሚችል ሹፌሩን ታሰበው፡፡
መዳረሻው የሆነ የሴተኛ አዳሪዋን መንደር ማታ ማታ ለመበጥበጥ ጮሆ የሚነሳ፣ ቀን ቀን ድምፁን አጥፍቶ በሩን ቆልፎ የሚሰወር አንድ ቤት ሊሆን ይችላል። በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ወደ ታች መውረድ ሲጀምሩ፣ “በዚህ ግባ” ብላ ቅያስ አሳየችው። በውስጥ ልትንሸራሸር ፈልጋ እንጂ መልሰው ሲወጡ መደበኛውን የሀያ ሁለት ቦሌ መንገድ ያዙ።

መልሳ እነዛኑ የድምፅ ሀጢአት ዘፈኖችን ከፍታለች። በውስጥ መንገድ ከተንሸራሸሩ በኋላ የተበጠበጠው መንፈሷ ረግቷል፡፡ ሀቅታው፤ ስቅታው ቆሟል። መጠነ ቁራጭ ወጥቶላታል። ሾፌሩ ሊጠይቃት አልፈለገም። በጥቅሉ የሚሰማው የጉዳዩ አሳዛኝነት በዝርዝሩ ውስጥ ተራ ሊሆን የሚችል ነው፡፡ የተሰማውን ርህራሄ በግዴለሽነት ለብጦ ዝም ማለት ተሻለው፡፡
“ውይ ትራፊኩ እንዳይቀጣህ” ብላ በርህራሄ እጇን በደረቷ ላይ ጫነች። ቀጥሎ ደግሞ “እንዴት ትራፊክ እፈራለሁ መሰለህ!” ብላ እጇን ትከሻው ላይ ሳታስበው አሳረፈች። መስላ የምትታየውን እንዳልሆነች ያለ አንደበት መሰከረለት። በእጇ ንክኪ ውስጥ ባገኘው መልዕክት እርግጠኛ ሆነ። ቢያንስ ባል አላት ብሎ ትንሽ ከፍታ ሰጣት። መጀመሪያም ያልሆነችውን አባዝቶ ነበር የኮነናት። ወዲያው አሁን ደግሞ ትንንሽ ብልጭታዎችን አጋኖ ሊያዳንቃት ፈልጓል፡፡
451 viewsሳ² lizu, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 12:26:12
የዳምቢሳ ሞዮ " DEAD AID " የተሰኘው ዝነኛ መጽሐፍዋ " ገዳይ ተራድኦ " በሚል ርዕስ በአምላክ ጎዳና ተተርጉሞ ለንባብ በቃ ::

አፍሪካ በሙስና ብቻ ወደ 150 ቢልዮን ዶላር በዓመት ታጣለች ::

20 % የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ በጠኔ ምክንያት የሞት አፋፍ ላይ ነው :: 

31 % የሚሆኑ ከሠሃራ በታች የሚገኙ ህፃናት የተመጣጠነ ምግብ አጥተው ቀንጭረዋል ::

ግማሽ ቢልዮን የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ አሁንም በመብራት እጦት ዳፈና ውስጥ ይኳትናል ::

50% የሚሆነው አፍሪካዊ በኮሌራ እና ተቅማጥ የመያዝ እድሉ ሰፊ ነው ።

አንዲት አፍሪካዊ ሴት ከአሜሪካዊት ሴት ጋር ስትነፃፀር 231 እጥፍ በወሊድ ወቅት የመሞት እድል አላት ::

25 ሚልዮኑ አፍሪካዊ የ "HIV" ታማሚ ነው። 600 ሚልዮኑ አፍሪካዊ ማንበብ እና መጻፍ የማይችል መሃይም ነው።

እኛ አፍሪካውያን ያልተረዳነው ዋናውና ዋናው ነገር  አፍሪካ ወደከፍታ የምትሻገረው በእርዳታና በሌሎች ችሮታ  ሳይሆን በጠንካራ የሥራ ባህል  በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና በካፒታል ነው።

ቻይና 850 ሚልዮን ህዝቧን ከደህነት አረንቋ ያወጣችው በእርዳታ ሳይሆን በራሷ ስራ ነው!

በእርዳታ ያደገ ወይም የበለፀገ  አህጉር አይደለም ሃገር እንኳን የለችም :: የሚገርመው አሜሪካ ከቻይና ገንዘብ ትበደራለች ::  ከዛ የተበደረችውን ደግሞ ለአፍሪካ በእርዳታ መልክ ትሰጣለች! አሜሪካ ምን ያህል ብታስብልን ይሆን !?

ምንም ጥርጥር የለውም የአፍሪካ ሃብት የሚመዘበረው በእርዳታ መጋረጃ ነው።

በተጨማሪ ኢኮኖሚስት ዋሲሁን በላይ በመጽሐፉ ዙሪያ የሰራውን ትንተና  ተመልከቱት

ርዕስ - ገዳይ ተራድኦ
ደራሲ - ዳምቢሳ ሞዮ

Share -
@ethio_fiction

Comment -
@sam_lizu
152 viewsሳ² lizu, 09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 22:04:36 " ባይተዋር ሌሊቶች "
መጽሐፍ ለንባብ በቃ !

ከመፅሀፉ የወደድኩትን እነሆ

#ርዕስ:- #ሁለት_አንድ_ምስል

እሳት እየሞቁ
ዝምታ እየሳቁ
ወይን እያጣጣሙ
ትዝታ እየሰሙ…
በነገር መብሰልሰል፣
ጉርድ ጨረቃ ፊት
ያልሽኝን መመሰል…

ልንገርሽ… ልንገርሽ…
አንቺ የሌት ብርሃን፤ አንቺ የሌት ባለቤት፣
ግማሽ መሆንሽን የነገረሽ የለም
ሙሉ ነሽ ባንቺ ቤት፡፡

ልንገርሽ… ልንገርሽ…
እሳት ዳር ተቀምጠው
ትዝታን መሞቁ፣
ብርድ ልብስ አስጥተው
ፀሐይ መጠበቁ፣
በሚወርድ ዶፍ መሃል
ከማይደርቅ ብሶት፤ ቃል ብይን መጭመቁ…

ልንገርሽ… ልንገርሽ…
አንቺ ግማሽ ብርሃን
የአምና ባለቤት
ልቤን እንደሞላሽ
የነገረሽ የለም ሽርፍ ነሽ ባንቺ ቤት::
394 viewsሳ² lizu, 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 21:22:59 በመጨረሻም 4:00 አንድ ግጥም ከነመፅሀፉ(ገዝታችሁ እንድታነቡት) እለቅላችሁና እንሰነባበታለን
564 viewsሳ² lizu, 18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 21:15:53 #1.
ሚስት: ውዴ ዛሬ ምሽት ተኝተን ምን አሰብክ
ባል : አለምን አዞርሻለሁ

#2.
ከቴሌግራምህ ላይ ይቺን ልጅ delete አድርጋት ስታስጠላኝ

እሺ

ይሄን ልጅ delete አድርጊው አይመቸኝም

እ.. ግን እሱ ጎረቤት ነው ... ደሞ አንድ ክፍል አብረን ተምረናል ምርጥ ጓደኛዬ ነው እ...
አይ ቺኮች
#3.
የድሮ ቸከሴ : ስልኬን ማጥፋት ትችላለህ።
እኔ : ማን ልበል

#4. ብዙ ሰው ረዣዥም ሰዎች ብዙ ጥቅም እንደሚያገኙ ይናገራል ... ነገርግን አብዛኛውን የሸረሪት ድር የሚጠርጉልን እነሱ ናቸው

#5. አንዱ ያጎቴ ልጅ ከusa ቤታችን መጥቶ የቆየ የሰርግ ቪዲዮ እየተመለከተ በቪዲዮ ውስጥ ወደሚታዩት አያቴ እየጠቆመ "እቺ ሴትዮ አሁንም አለች..." ብሎ ሳይጨርስ አያቴ ዊልቸር ላይ ሆና
ና ግደለኝ ና እሱ ነው የቀረህ

Comment : @cr7_reunited

Share : @ethio_fiction
610 viewsሳ² lizu, 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 20:42:18 ስትጨርሱ ጠቅ እያደረጋችሁ
616 viewsሳ² lizu, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 20:36:40 #የቀጠለ...
ሁሉም ነገር ከአሽከርካሪው አንጻር ከታየ የመአት ጥርጣሬ ውስብስብ ክምችት ነው። ማረጋገጥም አይፈልግም። የሚረጋገጥም ነገር የለም። ሲደርሱ ሁሉም ግልጽ ሆኖ ይወጣል።
ስልክ ጠቃሚ ነገር ነው። በተለይ ከኋላ ከተሳፋሪ መቀመጫ ሲመጣ። ያ የሚያስጠላ የሁከት ሙዚቃ በስልኩ ጥሪ ምክንያት ተቋረጠ። ከወንድ ጋር ነው የምታወራው፤ የምትናገራቸው ቃላት ተደጋጋሚ ናቸው። ከድግምግሞሹ ጋር የለቅሶ ሳግ እና መቃተት እየተጨመረበት መጣ። ለቅሶዋ እና የምትናፈጠው ንፍጥ ተደጋጋሚ ቃላቶቿን ወደ ሌላ የጥልቀት ወንበር ወስደው አነገሱት።

አለቃቀሷ፣ በሳግ የሚቆራረጠው ድምጿ እና በድምጿ የሚናጠው አንድ ፍሬ ልጅነቷ፣ ሾፌሩ ወደ ኋላ በድጋሚ ዞሮ እንዲያያት ምክንያት ሆነው። መጠየቅም ሆነ ጣልቃ መግባት ግን አልፈለገም። ምድር የአሳር እና መከራ ቋት ናት። የስንቱ ታሪክ ተሰምቶ የስንቱ ይቀራል። ከተሰማ በኋላስ ከንፈር ከመምጠጥ ባሻገር ምን መፍትሄ ያስገኛል?
በስልክ የምታወራውን በፍጥነት በመገጣጠም ግርድፍ ነገሩ ገብቶታል።

“… እነ እሙጢ ጋር እየሄድኩ ነው… ብቻዬን ከበደኝ… አንተ ከጎኔ የለህም …. ባዶ ቤት ውስጥ ብቻዬን ከበደኝ… እነ እሙጢ ጋር እየሄድኩ ነው… በቃ ከሰው ጋር ማውራት ናፈቀኝ… አንተ ትናፍቀኛለህ… ጓደኞቼ ይናፍቁኛል… ብዙ ደስ የማይል ነገር እያሰብኩኝ ነው… ማታ አልተኛም… ቀን ይጨንቀኛል… ተቀየምከኝ?... እዛ ስለሄድኩ?... ምን ላድርግ ሰለቸኝ… እኔ ጩጬ ምናምን ነገር አይገባኝም… ግራ ገባኝ… አንተ የለህም… ማንም የለም… ትርሲት አንዴ ብቻ መጥታ በዛው ጠፋች… ስራ ትገባለች…. ብቻዬን አልችልም… አንተ የለህም… እኔ ባዶ ሰፊ ቤት ውስጥ መቀመጥ አልለመድኩም… ብታዝንም ምንም ማድረግ አልችልም… መጥፎ ነገር ነው ቀኑን ሙሉ የማስበው… ጩጬው ደህና ነው… እኔ ግን ከበደኝ…”
መልእክቱ ይሄው ነው።

ቅደም ተከተሉ ይለዋወጣል እንጂ አዲስ የሚጨመር መረጃ የለም። ከውጭ ስትታይ ቅርጿ የተሳዳቢ ዱርዬ ሴት ነው። ስትናገር ከአራዳ ቋንቋ ጋር ቀላቅላ የምትሳደብ። አፏን ያዝ ያደርጋታል። አማርኛ የመጀመሪያ ቋንቋዋ አይደለም። ግን ይህ የመጀመሪያ ጊዜዋ ነው፤ እናት ስትሆን። ሃያ አመት አይሞላትም። አጭሳና ስባ የማታውቀው ነገር ለም። ቀረብ  ብሎ የአፏን ጠረን ያሸተተ፣ በማስቲካው ሽታ ላይ የማስቲሹን ሊለየው ይችላል።
መኪናውን እየነዳ በአንድ እጁ ጭንቅላቱን አከከ። ግራ ሲገባው ሳይታወቀው የሚያደርገው ነገር ነው። አሁን በነጻ ቢወስዳትና ብትጽናና ደስ የሚለው መሰለው። የሴቶች ለቅሶ በሰውነቱ ላይ የሚፈጥርበት ነገር አለ። በዋና ሀገር ጥለህ … ባህር አቋርጠህ ሽሽ የሚለው ድንጋጤ ከውስጡ ይቀሰቀሳል።

#የመጨረሻው ክፍል ነገ ከ50 በኋላ
670 viewsሳ² lizu, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 20:36:27 #ርዕስ :- "እነ ሙጢ ጋ እየሄድኩኝ ነው"

#ክፍል :- ሁለት

...መሄድ የፈለገችው ወደ ሃያ ሁለት ስለሆነ፣ ቶሎ የሚገላገልበትን  መንገድ መርጦ መምዘግዘግ ጀመረ።
“አባቱ!... በሀያ አራት ልትሄድ ትችላለህ” ስትለው በድጋሚ ተበሳጨ። መጓዝ ከጀመሩ በኋላ አቅጣጫ የሚለዋውጡ ወይንም “እግረ መንገድህን እንትን ጋር  ቆም ታደርግልኛለህ” የሚሉትን አይወድም። ከሁሉ የሚጠላው ግን “ገንዘብ ይዘውልኝ እስኪመጡ…” ብለው ከደረሱ በኋላ የትዕግስቱን መንገድ እንደገና ወዳላሰበበት አቅጣጫ የሚነዱትን ነው። በራይድ ስራ ላይ ብዙ የሚገርሙት ነገሮች አሉ። ለግርምቱ መጠን ተወዳዳሪ የሚያጣለት ግን… ሁሉም ተሳፋሪ የሚሄድበትን አድራሻ ከስም በስተቀር ያለማወቁ ታኢብ ነው። የሚሄዱበትን እሱ እንዲያውቅላቸው የሚፈልጉት ነገር…።

ተሳፋሪዎቹ ይገቡታል። ወሬ የሚፈልጉ እና የማይፈልጉት ብሎ ይከፍላቸዋል። የወሬ መነሻው “ስራ እንዴት ነው?” የሚል ነው። እሱን ሲመልስ… “በቀን ስንት ታገኛለህ?” ይከተላል። ይከታተላል። “መኪናው ያንተ ነው ወይስ… ለገቢ ነው የምትሰራው?”
በተቻለው መጠን ፊቱን ቅጭም አድርጎ ገና ከመነሻው “ጥያቄ አልፈልግም” የሚል ማስታወቂያ ይሰራል። ግን ከፋይ ስለሆኑ የሱን ፊት መልዕክት ቢያውቁም፣ በራሳቸው ፍላጎት እሱን ባሪያ አድርገው የሚቀጥሉ ይበዛሉ። የሱን ያለማድመጥ ፍላጎት በራሳቸው የማውራት ፍላጎት ይገለብጡታል።  የባጥ የቋጡን አውርተው ተንፈስ ብለው ይወርዳሉ። እንደ ልብ ጓደኛ ሚስታቸውን የሚያሙለት አሉ። ልክ እመውረጃቸው ሲደርሱ በቅጽበት ባዳ ይሆናሉ።

በወሬ ያጋሉትን ጆሮውን መልሰው ባይተዋር አድርገው ፍሪጅ ይከቱታል። ያንን ሁሉ አውርተው “በቃ እዚህ ጋ” ብለው ሲያዙት ሌላ ሰው ሆነው ነው። “አላውቅህ አታውቀኝ” የሚለው የመለያያ ዜማ፣ ድምጽ አልባ ሆኖ የመኪናውን ድባብ ይቆጣጠረዋል።
መጀመሪያ ሰሞን…ገና ለሥራው አዲስ እያለ… ካደረሰው ሰው ሁሉ ጋር ዝምድና የመሰረተ ይመስለው ነበር። “ለስራ ከፈለጋችሁ ስልኬን ሴቭ አድርጉና ደውሉልኝ” ይል ነበር። ቲፕ የሰጠውን ከማመስገን አልፎ ይሳለም ነበር። በኋላ ቲፑን እየጠበቀ የመቋመጥ ልምድ ሲጠናወተው በራሱ አፈረ። ከተቻለ እቅጩን ለመቀበል እንጂ አልፎ የሚመጣውን በመጠበቅ መቁለጭለጭ እርም ብሎ ተወ። መጣ ቀረ ብዙ ለውጥ አያመጣም። ለማይረባ ነገር ሱሰኛ መሆን ነው ትርፉ። እንዲያውም አንዳንዴ ዝርዝር የለንም ሲሉ ይተውላቸዋል። ዝርዝር በመፈለግ የሚባክነው ጊዜ ይባስ ያበሽቀዋል። እስከ ሀያ ብር ድረስ የራሱን ጥቅም አሳልፎ ይሰጣል።

ከሀያ ብር በላይ ግን “አሁንስ በዛ” ብሎ ያበሳጨዋል። እሩብ  ጉዳይ ነገር ነው አቋሙ። እሩብ ጉዳይ ከሙሉው ክፍያ ቢጎድል ችግር የለውም። ግማሽ ካሉት ግን አሻፈረኝ ይላል።
እቺኛዋ ግን ግማሹን እንኳን ከሰጠችው አመስጋኝ ነው። ልክ አሮጊት አሳፍሮ እንደማድረስ በመሰለ አኳኋን። የሆነ በምድር ሳይሆን በሰማይ የሚከፈል አይነት ስሜት የሚሰጥ አገልግሎት አለ። እቺኛዋ ለሰማይ እድሜዋም ማንነቷም አያቀራርባትም። ምናልባት ያቀፈችው ህጻን ሌላ ሚዛን ላይ ካላስቀመጣት በስተቀር። ህጻን ታቅፈው እንደሚለምኑት የምስኪንነት ደረጃ ያስጠጋት ይሆናል። ጠቅልላ የታቀፈችው ህጻን መሆኑም ግን ያጠያይቃል። ህጻኑ ሽታም ለቅሶም የለውም።
679 viewsሳ² lizu, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 22:22:44 like ያልኳችሁ ... ዝግጅቱን እየተከታተላችሁ ለማወቅ ያህል ነው ... ከዛ አንፃር እዩትና ተጫኗት
778 viewsሳ² lizu, 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ