Get Mystery Box with random crypto!

#የቀጠለ... ሁሉም ነገር ከአሽከርካሪው አንጻር ከታየ የመአት ጥርጣሬ ውስብስብ ክምችት ነው። ማረ | ልብወለድ Ethio_Fiction

#የቀጠለ...
ሁሉም ነገር ከአሽከርካሪው አንጻር ከታየ የመአት ጥርጣሬ ውስብስብ ክምችት ነው። ማረጋገጥም አይፈልግም። የሚረጋገጥም ነገር የለም። ሲደርሱ ሁሉም ግልጽ ሆኖ ይወጣል።
ስልክ ጠቃሚ ነገር ነው። በተለይ ከኋላ ከተሳፋሪ መቀመጫ ሲመጣ። ያ የሚያስጠላ የሁከት ሙዚቃ በስልኩ ጥሪ ምክንያት ተቋረጠ። ከወንድ ጋር ነው የምታወራው፤ የምትናገራቸው ቃላት ተደጋጋሚ ናቸው። ከድግምግሞሹ ጋር የለቅሶ ሳግ እና መቃተት እየተጨመረበት መጣ። ለቅሶዋ እና የምትናፈጠው ንፍጥ ተደጋጋሚ ቃላቶቿን ወደ ሌላ የጥልቀት ወንበር ወስደው አነገሱት።

አለቃቀሷ፣ በሳግ የሚቆራረጠው ድምጿ እና በድምጿ የሚናጠው አንድ ፍሬ ልጅነቷ፣ ሾፌሩ ወደ ኋላ በድጋሚ ዞሮ እንዲያያት ምክንያት ሆነው። መጠየቅም ሆነ ጣልቃ መግባት ግን አልፈለገም። ምድር የአሳር እና መከራ ቋት ናት። የስንቱ ታሪክ ተሰምቶ የስንቱ ይቀራል። ከተሰማ በኋላስ ከንፈር ከመምጠጥ ባሻገር ምን መፍትሄ ያስገኛል?
በስልክ የምታወራውን በፍጥነት በመገጣጠም ግርድፍ ነገሩ ገብቶታል።

“… እነ እሙጢ ጋር እየሄድኩ ነው… ብቻዬን ከበደኝ… አንተ ከጎኔ የለህም …. ባዶ ቤት ውስጥ ብቻዬን ከበደኝ… እነ እሙጢ ጋር እየሄድኩ ነው… በቃ ከሰው ጋር ማውራት ናፈቀኝ… አንተ ትናፍቀኛለህ… ጓደኞቼ ይናፍቁኛል… ብዙ ደስ የማይል ነገር እያሰብኩኝ ነው… ማታ አልተኛም… ቀን ይጨንቀኛል… ተቀየምከኝ?... እዛ ስለሄድኩ?... ምን ላድርግ ሰለቸኝ… እኔ ጩጬ ምናምን ነገር አይገባኝም… ግራ ገባኝ… አንተ የለህም… ማንም የለም… ትርሲት አንዴ ብቻ መጥታ በዛው ጠፋች… ስራ ትገባለች…. ብቻዬን አልችልም… አንተ የለህም… እኔ ባዶ ሰፊ ቤት ውስጥ መቀመጥ አልለመድኩም… ብታዝንም ምንም ማድረግ አልችልም… መጥፎ ነገር ነው ቀኑን ሙሉ የማስበው… ጩጬው ደህና ነው… እኔ ግን ከበደኝ…”
መልእክቱ ይሄው ነው።

ቅደም ተከተሉ ይለዋወጣል እንጂ አዲስ የሚጨመር መረጃ የለም። ከውጭ ስትታይ ቅርጿ የተሳዳቢ ዱርዬ ሴት ነው። ስትናገር ከአራዳ ቋንቋ ጋር ቀላቅላ የምትሳደብ። አፏን ያዝ ያደርጋታል። አማርኛ የመጀመሪያ ቋንቋዋ አይደለም። ግን ይህ የመጀመሪያ ጊዜዋ ነው፤ እናት ስትሆን። ሃያ አመት አይሞላትም። አጭሳና ስባ የማታውቀው ነገር ለም። ቀረብ  ብሎ የአፏን ጠረን ያሸተተ፣ በማስቲካው ሽታ ላይ የማስቲሹን ሊለየው ይችላል።
መኪናውን እየነዳ በአንድ እጁ ጭንቅላቱን አከከ። ግራ ሲገባው ሳይታወቀው የሚያደርገው ነገር ነው። አሁን በነጻ ቢወስዳትና ብትጽናና ደስ የሚለው መሰለው። የሴቶች ለቅሶ በሰውነቱ ላይ የሚፈጥርበት ነገር አለ። በዋና ሀገር ጥለህ … ባህር አቋርጠህ ሽሽ የሚለው ድንጋጤ ከውስጡ ይቀሰቀሳል።

#የመጨረሻው ክፍል ነገ ከ50 በኋላ